U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

A rat peeks out from beneath a wooden structure.
በCambridge’s Rodent Control ፕሮግራም የአይጥ ችግሮችን ይከላከሉ
የCambridge ከተማ አስተዳደር Inspectional Services Department በPrivate Property Rodent Control ፕሮግራም አማካኝነት የቤት ውጪ የአይጥ ቁጥጥር አገልግሎቶችን በነፃ ያቀርባል። 2021 ላይ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ይህ ፕሮግራም የባለሙያ ፍተሻዎች፣ መፍትሔዎች እና የክትትል ጉብኝቶች በማቅረብ ከ900 በላይ ብቁ የሆኑ መኖሪያ ንብረቶችን ረድቷል። ነዋሪዎችም ውጤታማ የአይጥ መከላከል ዘዴዎች ላይም ትምህርት ያገኛሉ። መኖሪያ ሰፈሩን ከአይጥ የጸዳ ለማድረግ የንፅሕና አጠባበቅ እና የጋራ ኃላፊነት ወሳኝ እንደመሆናቸው መጠን የከተማ አስተዳደሩ ማኅበረሰብ አቀፍ ተሳትፎን ያበረታታል።
Close-up of multiple graduation caps with orange tassels during an outdoor ceremony.
Bridge to College፦ ወደ የከፍተኛ ትምህርት ስኬት የሚያመራ መንገድ
በCambridge Community Learning Center የሚተዳደረው Bridge to College ፕሮግራም በማንበብ፣ መጻፍ፣ ሒሳብ እና የማጥናት ክህሎቶች ዙሪያ የማታ ትምህርት ክፍሎችን በነፃ በማቅረብ አዋቂዎችን ለኮሌጅ እንዲዘጋጁ ይረዳል። ለCambridge ነዋሪዎች እና በአቅራቢያው ለሚገኙ የተመረጡ ማኅበረሰቦች ክፍት የሆነው ፕሮግራም ተማሪዎችን እና በተለይም ስደተኛ እና አዋቂ ተማሪዎችን በከፍተኛ ትምህርት ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈሉትን ክህሎቶች እና በራስ መተማመን እንዲያዳብሩ ይረዳል።
A safety officer carefully inspects a child safety car seat to ensure it is properly installed in the vehicle.
በነፃ በሚቀርቡ ፍተሻዎች እና የመግጠም ሥራዎች ቀላል የተደረገ የልጅ የመኪና መቀመጫ ደኅንነት
የልጅ የመኪና መቀመጫዎች፣ ልጁን ከፍ የሚያደርጉ የመኪና መቀመጫዎች እና የደኅንነት ቀበቶዎችን ነዋሪዎች በአግባቡ እንዲገጥሙ ለመርዳት የልጅ የደኅንነት መቀመጫ ገጠማ እና ፍተሻ አገልግሎት በነፃ ያቀርባል። ሁሉም ልጆች ደኅንነታቸው በተጠበቀ እና የMassachusetts ሕግን ባከበረ መልኩ እየተጓዙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሠለጠኑ መኮንኖች መቀመጫዎችን ይፈትሻሉ፣ መመሪያ ይሰጣሉ እና ለተቸገሩ ቤተሰቦችም የልጅ የመኪና መቀመጫዎችን በነፃ ሊያቀርቡ ይችላሉ።
An open register book displaying a list of members with names and details written in cursive handwriting, set on a purple textured background.
የቤተሰብዎን ያለፈ ታሪክ ይወቁ፦ በCambridge Public Library የሚገኙ የዘር ሐረግ ግብዓቶች
የCambridge Public Library ለታሪካዊ መዝገቦች፣ የዘር ሐረግ መረጃ ቋቶች እና የባለሙያ መመሪያ ከክፍያ ነፃ የሆነ ተደራሽነት በመስጠት እንዴት የዘር ሐረግዎን እንዲያውቁ ሊረዳዎት እንደሚችል ይወቁ። ገና እየጀመሩ ወይም ጠለቅ ያለ ምርመራ እያደረጉ ቢሆንም፣ በአካባቢያዊ መዝገብ ቤቶች፣ የከተማ አስተዳደር የመረጃ ማውጫዎች እና የሕዝብ ቆጠራ መረጃዎች አማካኝነት ከታሪክዎ ጋር ግንኙነት ይፍጠሩ።
Visitors observing paintings, with some seated on brown leather benches and others standing close to the artworks.
በሙዚየሞች ላይ ይቆጥቡ፦ ነፃ ወይም ቅናሽ የተደረገበት መግቢያ ያስይዙ
የCambridge Public Library የMuseum Pass ፕሮግራም ለ11 ሙዚየሞች እና ባህላዊ መስህቦች ነፃ ወይም ቅናሽ ያላቸው መግቢያዎችን በማቅረብ ለነዋሪዎች የባህል ዳሰሳ ይበልጥ ተመጣጣኝ ዋጋ እንዲኖረው ያደርጋል። የቤተ መጻሕፍት ካርድዎ ምስጋና ይግባውና እንዴት መግቢያ ማስያዝ እንደሚችሉ ይወቁ እንዲሁም ተግባራዊ ይዘት ባለው ትምህርት፣ ሥነ-ጥበብ፣ ታሪክ እና ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች ይደሰቱ።
Person holding a vial of water against a freshwater pH color chart to test the water.
ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንጹህ ውሃ ማቅረብ
የCambridge Water Department ንጹሕ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጥሩ ጣዕም ያለው ውኃ ለማቅረብ በትጋት ይሠራል። ለነዋሪዎች የሚቀርቡ ነፃ የእርሳስ እና የመዳብ መመርመሪያ ጥቅሎችን ጨምሮ በየዕለቱ በሚከናወን ጥብቅ ምርመራ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የሕዝብ ትምህርት አማካኝነት የውኃ ጥራት ከፈተኛ የሚባሉትን ስታንዳርዶች እንደሚያሟላ እና ከሚጠበቀው በላይ ሆኖ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ ያረጋግጣል።
A person reviews energy bills while holding a phone next to a window.
የኃይል አቅርቦት ሒሳቦችዎን ለመቀነስ እርዳታ ያግኙ
የCambridge ከተማ አስተዳደር የኃይል አቅርቦት ሒሳባቸውን መቀነስ ለሚፈልጉ ነዋሪዎች አንድ ለአንድ የሚሰጥ እገዛ በነፃ ያቀርባል። በCambridge Energy Helpline (617-430-6230) በኩል የሚደውሉ ሰዎች ከነዳጅ ድጎማ እና ቅናሽ ያላቸው የመገልገያ ተመኖች ጀምሮ እስከ የፀሐይ ኃይል ክሬዲቶች እና ከወጪ ነፃ የኃይል አቅርቦት ግምገማዎች ድረስ የወጪ ቆጣቢ ፕሮግራሞችን ሊያብራሩ ከሚችሉ የሠለጠኑ አማካሪ ጋር ይገናኛሉ። የሕንፃው ዓይነት ምንም ይሁን ምን ተከራዮች፣ የቤት ባለቤቶች እና አከራዮች በተመሳሳይ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።
Person composting kitchen waste in a large wooden bin at a community garden.
ምግብ ነክ ቆሻሻን ወደ ንጹሕ የኃይል ምንጭ ይለውጡ
የCambridge ብስባሽ የማዳበር ፕሮግራም በዘመናዊ የብስባሽ ማዳበሪያ ሂደት አማካኝነት የምግብ ትርፍራፊዎችን ወደ ንጹሕ የኃይል ምንጭ እና የአትክልት ማዳበሪያ ይለውጣል። ብስባሽ ማዳበር ወደ ቆሻሻ መጣያ የሚሄደውን ቆሻሻ በመቀነስ፣ ወጪ በመቀነስ፣ የአየር ንብረት ግቦችን በመደገፍ እና የአይጥ እንቅስቃሴንም ዝቅ በማድረግ ከአንድ የሙዝ ልጣጭ ጀምሮ ይበልጥ ጤናማ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆነች Cambridge ለመገንባት እየረዳ ነው።
Exterior view of a three-story residential building with multiple windows and two entrances, each marked by construction warnings and surrounded by orange cones. A bicycle is parked on the street in front of the building.
በከተማ አስተዳደሩ ነፃ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ፕሮግራሞች ተጠቃሚ ይሁኑ
የCambridge ከተማ አስተዳደር በተረጋጋ መኖሪያ ቤት እና የቤት ባለቤትነት ረገድ ነዋሪዎችን ለመርዳት የተለያዩ የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞችን በነፃ ያቀርባል። አገልግሎቶቹ የቤት ዕቃ የማስገባት እና ከይዞታ ማስለቀቂያን የመከላከል እርዳታ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ገዢዎች የሚያገለግል የቅድሚያ ክፍያ እና የመዝጊያ ክፍያ ወጪ ድጋፍ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ግዢ ሂደት ዙሪያ ትምህርት ማግኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ክፍት የሆነ ለአራት ሳምንት የሚዘልቅ ሁሉን አቀፍ የመጀመሪያ ጊዜ ቤት ገዢ ወርክሾፕን ያካትታሉ። የገንዘብ ድጋፍ ፈልገውም ሆነ የመጀመሪያ መኖሪያ ቤትዎን ለመግዛት የከተማ አስተዳደሩ እርዳታ ለመስጠት ይገኛል።
A family of five, a mother and four children, sit closely together on a sofa, engaged in reading books. The room appears cozy, illuminated by natural light.
በBaby University በኩል ከአዲስ ወላጆች ጋር ይገናኙ
Baby University (Baby U) ከ0–3 ዓመት እድሜ ያሉ ልጆች ያሏቸውን የCambridge ቤተሰቦች የሚደግፍ ነፃ የ14-ሳምንት ፕሮግራም ነው። ቅዳሜ በሚካሄዱ ወርክሾፖች፣ አንድ ለአንድ ጉብኝቶች እና የማኅበረሰብ ግንኙነቶች አማካኝነት Baby U ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እና እርስ በእርስም ጠንከር ያሉ ግንኙነቶችን እንዲገነቡ እየረዳ በተመሳሳይ ሰዓት በBaby U Alumni Association አማካኝነት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ድጋፍ ያቀርባል።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here