PeopleforBikes ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚሠሩትን ሥራ በማኅበረሰቦቻቸው ውስጥ ብስክሌት መንዳትን ይበልጥ አመቺ ለማድረግ እያዋሉ ላሉ ከተሞች እውቅና ለመስጠት ዓመታዊ የከተማ ደረጃ አሰጣጦችን ያከናውናል። በቅርቡ በሰጡት ደረጃ መሠረት Cambridge ከ604 መካከለኛ መጠን (ከ50ሺህ እስከ 300ሺህ የሕዝብ ብዛት) ያላቸው የU.S. ከተሞች መካከል ብስክሌት ለመንዳት ባላት አመቺነት ከDavis፣ California ቀጥሎ 2ኛ ደረጃን ይዛለች።
እንደ PeopleforBikes ገለፃ፣ "በቅርብ ዓመታት ውስጥ ትልቅ የሚባል የከተማ ደረጃ ውጤት መሻሻል ካሳዩት ከተማዎች መካከል የCambridge ከተማ ተጠቃሽ ነች። እ.ኤ.አ በ2019 ዓ.ም Cambridge በሀገሪቷ ውስጥ ጠንካራ ከሚባሉት የComplete Streets ድንጋጌዎች መካከል አንዱ የሆነውን እና ደኅንነታቸው የተጠበቁ የብስክሌት መንገዶች እንዲፈጠሩ የሚያስገድደውን Cycling Safety Ordinance (CSO) አፅድቃለች። እ.ኤ.አ በ2020 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ 25 ማይሎችን የሚሸፍን የብስክሌት መስመር እ.ኤ.አ ከ2026 ዓ.ም በፊት ለመዘርጋት መርሃ ግብር አስቀምጧል። Cambridge የተነጠለ የብስክሌት መሠረተ ልማት ለመገንባት ጠንካራ (ቦላርድ) እና ተጣጣፊ መከለያ ምሰሶዎችን በመጠቀም እና በፈጣን ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ በመተማመን በCSO የተቀመጡትን ግቦች ከመምታት አንፃር ጉልህ እድገት አሳይታለች።"
Cambridge ከPeopleForBikes እውቅና ስታገኝ ይህ የመጀመሪያ ጊዜዋ አይደለም። እ.ኤ.አ በ2023 ዓ.ም Inman Square ላይ የተደረገው የንድፍ ለውጥ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ምርጥ አዲስ የብስክሌት መስመሮች አንዱ ተብሎ በድርጅቱ እውቅና ተሰጥቶታል። እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም Western Avenue በአሜሪካ ከሚገኙ 10 ምርጥ አዲስ የብስክሌት መስመሮች ውስጥ 1ኛው ተብሎ ተሰይሟል። በድር-ጣቢያቸው ላይ እንደተገለፀው፣ በUnited States ውስጥ መልሶ ግንባታ የሚከናወንበት ጎዳና ሁሉ Westernን ቢመስል እያንዳንዱ አሜሪካዊ ውስጥ በመደበኛነት ብስክሌት የመጠቀም ፍላጎት በመቀስቀስ ረገድ ትልቅ እርምጃ ወደፊት እንራመዳለን።"