U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የከተማ አስተዳደሩ እግረኛ ተኮር ፖሊሲዎች እና መሠረተ ልማት

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024
" ለእግረኛ ይበልጥ ተስማሚ የሆነች Cambridgeን ለመቅረጽ በትብብር የሚሠራ ኃይል። "

የከተማ አስተዳደሩ ተደራሽነትን እና ለእግር ጉዞ አመቺነትን ለማሻሻል በያዘው ተልዕኮ ውስጥ የCambridge Pedestrian Committee (የCambridge የእግረኞች ኮሚቴ) ቁልፍ ሚና የሚጫወት ግብዓት ነው። ከDepartment of Public Works (DPW) (የሕዝብ ሥራዎች መምሪያ)፣ ከPolice Department (የፖሊስ አገልግሎት መምሪያ)፣ እና ከTraffic, Parking, and Transportation Department (TPT) (የትራፊክ፣ የመኪና ማቆሚያ እና የትራንስፖርት አገልግሎት መምሪያ) የተውጣጡ ተወካዮችን ጨምሮ 23 አባላትን የያዘው ኮሚቴ ይበልጥ ለእግረኞች ተስማሚ የሆነች Cambridgeን ለመቅረጽ በትብብር የሚሠራ ኃይል ነው። በCity Manager የሚሾሙት አባላት በከተማዋ ውስጥ በእግር ከመንቀሳቀስ ጋር የተያያዙትን ልዩ ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚረዱ የተለያዩ አመለካከቶችን በአንድ ቦታ ያሰባስባሉ።

ኮሚቴው በመንገድ ዲዛይን ላይ ከመምከር ጀምሮ ለእግረኛ ደኅንነት ቅድሚያ የሚሰጡ ፖሊሲዎችን እስከማውጣት ድረስ የሚደርስ ሰፊ ኃላፊነት አለው። የኮሚቴው ኃላፊነት የትራፊክ ምልክት ቀለም መቀያየሪያ የጊዜ ሰሌዳ፣ የእግረኛ መንገድ ስታንዳርዶች እና የትራፊክ ሕጎች አፈፃፀምን የመሳሰሉ ወሳኝ ገጽታዎችን ያካትታል። በተጨማሪም ኮሚቴው በእግር መጓዝ አስቸጋሪ የሆነባቸውን በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ቦታዎች በመለየት እነዚህን ቦታዎች ለማሻሻል ምክረ ሃሳቦችን ያቀርባል። ይህ አርቆ አሳቢ አቀራረብ የከተማ ዕቅድ አወጣጥ እና ልማት ላይ የእግረኛ ፍላጎቶች ማዕከላዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል።

ኮሚቴው የሚያደርገው ጥረት በአብዛኛው በመላው ከተማ ተደራሽነትን ለማሻሻል ከሚያልም የCambridge Five-Year Plan የተሰኘ ሁለገብ የጎዳናዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተነሳሽነት ጋር የተጣጣመ ነው። ከሌሎች የከተማ አስተዳደር መምሪያዎች ጋር በመተባበር በDPW የሚመራው ዕቅድ የእግረኛ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ወሳኝ ማሻሻያዎችን ያካትታል። የእግረኛ መሻገሪያዎችን እና የአካል ጉዳተኛ መገልገያ ሸርታቴዎችን ከማሻሻል ጀምሮ የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት ለመቀነስ እና የመኪና መንገድ መሻገሪያን ለሁሉም ሰው ይበልጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እንዲረዱ ከፍ ያሉ የእግረኛ መሻገሪያዎችን እስከመግጠም ድረስ የሚደርሱ ማሻሻያዎች ይደረጋሉ። እነዚህን የመሳሰሉ ፕሮጀክቶች የግለሰቡ የአካላዊ እንቅስቃሴ አቅም ምንም ይሁን ምን ለሁሉም ነዋሪዎቿ ይበልጥ ተደራሽ የሆነ አካባቢን ለመፍጠር Cambridge ያላትን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃሉ።

የPedestrian Committee ለሕዝብ ክፍት ከሆኑት ወርሃዊ ስብሰባዎቹ በተጨማሪ አብዛኛውን ጊዜ ልዩ ጉዳዮችን በጥልቀት መመልከት እንዲቻል አነስ ያሉ ንዑስ ኮሚቴዎችን ያዋቅራል። እነዚህ ልዩ ትኩረት ያላቸው ቡድኖች ጥልቅ ውይይቶችን እና ዝርዝር ትንታኔዎችን የሚያስችሉ በመሆኑ ውስብስብ ርዕሰ ጉዳዮች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ያደርጋሉ።

የCambridge Pedestrian Committee የሚሠራው ሥራ ለሰፊው የከተማ አስተዳደሩ የአካታችነት እና የተደራሽነት ራዕይ ወሳኝ ነው። እግረኛ ተኮር ፖሊሲዎችን እና መሠረተ ልማቶችን በማስተዋወቅ እና ተግባራዊ በማድረግ ኮሚቴው Cambridgeን ለሁሉም ሰው ጤና ተስማሚ የሆነች እና ይበልጥ ደማቅ የሆነ ማኅበረሰብ የሚኖርባት ከተማ እንድትሆን ያደርጋል። Cambridgeን ለእግር ጉዞ ተስማሚ የሆነ የከተማ ኑሮ ተምሳሌት ለማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ ቀጣይነት ያላቸው ተነሳሽነቶች ጎን ለጎን የኮሚቴው ጥረቶች ወሳኝ ናቸው።

A street sign emphasizes the presence of a crosswalk to vehicles driving by
አንድ የመንገድ ምልክት ወደ መጪ ተሽከርካሪዎች የመሻገር መንገድ መኖሩን ያጎላል
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here