እ.ኤ.አ በሜይ ወር 2023 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የተሻሻለውን የእግረኛ መንገድ እና የተሽከርካሪ መንገድ መልሶ ግንባታ Five Year Plan ይፋ አድርጓል። ይህ ሁሉን አቀፍ ዕቅድ በሁሉም የዕድሜ ክልል እና የአቅም ደረጃ ላይ የሚገኙ እግረኞችን፣ ብስክሌት ነጂዎችን፣ የሞተር ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችን እና የሕዝብ ማመላለሻ ተጠቃሚዎችን ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ የሚያገለግሉ መንገዶችን በመንደፍ ለመርዳት የታሰበ ነው። ዕቅዱ የሚከተሉትን የተወሰኑ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችን ታሳቢ በማድረግ ተዘጋጅቷል፦
- የጎዳናዎች እና የእግረኛ መንገዶች ሁኔታ
- ቦታ - ለፓርኮች ፣ ለዋና አደባባዮች ፣ ለቤተ-መጻሕፍት፣ ለወጣት ማዕከሎች፣ ለአረጋውያን መኖሪያ ቤቶች እና ለአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከሎች እንዲሁም ለአውቶብስ መንገዶች ቅርብ የሆኑ ወይም ለከባድ ትራፊክ የተጋለጡ አካባቢዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
- በBicycle Vision Network (የብስክሌት ራዕይ አውታር) መስፈርቶች መሠረት ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አካባቢዎች
- የሕዝብ ማመላለሻ መገኛዎች
- ከከተማ አስተዳደሩ እና ከስቴቱ የሚገኙ የገንዘብ ድልደላዎች
በየዓመቱ የሚገመገመው Five-Year Plan ከጎዳና እና ከእግረኛ መንገድ ግንባታዎች በፊት ሥራቸውን ማቀድ እንዲችሉ የፍጆታ ኩባንያዎችን ማስተባበር የሚያስችል በመሆኑ ተደጋጋሚ የጎዳና እና የእግረኛ መንገድ ምርቃቶች አስፈላጊነትን ያስቀራል።
እ.ኤ.አ በ2025 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከከተማ አስተዳደሩ የሚገኝ 13 ሚሊዮን ዶላር እና ከስቴቱ የሚገኝ 4 ሚሊዮን ዶላር ተደባልቆ በአጠቃላይ 17 ሚሊዮን ዶላር ለComplete Streets ፕሮግራም ይውላል። ከከተማ አስተዳደሩ ከሚገኘው 13 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 5 ሚሊዮን ዶላር የተነጣጠሉ የብስክሌት መስመሮችን ማስፋፋት ላይ እንዲውል ይመደባል። ይህም በCentral Square፣ Inman Square፣ The Port እና River Street ላይ የፕሮጀክት ማሻሻያዎች ለማከናወን በተደረጉ ሌሎች የካፒታል ኢንቬስትመንቶች የተደገፈ ነው።