U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ለCambridge የትራንስፖርት አገልግሎት ግቦች ማዕከላዊ የሆኑት ፍትሐዊነት እና ተደራሽነት

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024
" የተለያዩ የCambridge ኮሚቴዎች ማለትም Pedestrian፣ Bicycle and Transit Committees (የእግረኛ፣ የብስክሌት እና የሕዝብ ማመላለሻ ኮሚቴዎች) በከተማዋ የመጓጓዝ ቀላልነትን እና የከተማዋን ተደራሽነት ለሁሉም ሰው አስደሳች ለማድረግ የተያዘውን ጥረት ከፊት እየመሩ ናቸው። "

እግርን ለማፍታታትም ሆነ ለመላላክ ወይም ወደ ሥራ ለመሄድ በእንቅስቃሴ የተሞሉት የCambridge ጎዳናዎች ላይ መጓዝ ለሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስደሳች የሆነ ተሞክሮ መሆን አለበት። ለሁሉም ሰው ምቾት ያላቸው መሆንም አለባቸው። ስለዚህ ፍትሐዊነት እና ተደራሽነት የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ትኩረት የሚያደርግባቸው ነገሮች ናቸው።

እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር ወር 2024 ዓ.ም ላይ ለincome-eligible የMBTA ተሳፋሪዎች የትራንስፖርት ዋጋ ቅናሽ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። የፕሮግራሙ ቀደምት ተጠቃሚዎች አሁን በmbta.com/income-eligible በኩል ኦንላይን ማመልከት ይችላሉ። የታሪፍ ፍትሐዊነትን እውን ለማድረግ ትርጉም ያለው ማሻሻያ ተደርጎ የሚወሰደው አዲሱ ፕሮግራም ዕድሜያቸው ከ18-64 የሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተሳፋሪዎች በሁሉም የMBTA አውቶቡሶች፣ የከርሰ ምድር ባቡሮች፣ Commuter Rail እና ለአካል ጉዳተኞች የሚያገለግሉ ማመላለሻዎች (The RIDE) ለሚያደርጉት ጉዞ የሚከፍሉት የአንድ ጉዞ ታሪፍ ላይ የ50 በመቶ ቅናሽ ያቀርባል።

ይህ በመላው MBTA አገልግሎት የሚሰጥበት አካባቢ ውስጥ ላሉ ነዋሪዎች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ክፍያ ያቀርባል። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተሳፋሪዎች ማመልከቻዎቸውን በበርካታ ቋንቋዎች ኦንላይን ማስገባት እና MBTA አገልግሎት የሚሰጥበት አካባቢ ውስጥ በሚገኙ አምስት በአካል መቅረብ የሚቻልባቸው ቦታዎች ተገኝተው ማቅረብ ይችላሉ።

የከተማ አስተዳደሩ ብስክሌት መንዳትን እንደ ለአካባቢ ተስማሚ እና ፍትሃዊ የጉዞ አይነት ያስተዋውቃል። Bluebikes ይህንን በመደገፍ ለተደራሽነት እና ተመጣጣኝ ዋጋ ቅድሚያ ሰጥቶ አዲስ የመጡት ኤሌክትሮኒክ ብስክሌቶቹን ጨምሮ ሌሎች ብስክሌቶቹን ማግኘት እንዲችሉ በBluebikes’ Income-Eligible ፕሮግራም የተመዘገቡ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች የሚከፍሉት ወርሃዊ እና ዓመታዊ ክፍያዎች ላይ ቅናሽ አድርጓል።

የCambridge Door2Door Transportation ፕሮግራም ድንገተኛ ላልሆኑ የሕክምና ቀጠሮዎች እና ለሳምንታዊ የአስቤዛ ግዢ ጉዞዎች በበጎ ፈቃደኝነት ብቻ ክፍያ በሚፈፀምበት ሥርዓት ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች መሳፈሪያ ያቀርባል። በተጨማሪም የMassHealth Transportation ፕሮግራም ዶክተሮቻቸው PT-1 ቅፅ ላስገቡላቸው ብቁ አባላት ወደ የሕክምና ቀጠሮዎች መሳፈሪያ የሚያቀርብ ሲሆን፣ The RIDE ደግሞ ከሕክምና ጋር ተያያዥ ላልሆኑ ጉዞዎች አካል ጉዳተኞችን ያሳፍራል። እነዚህን አገልግሎቶች ከማግኘት ጋር የተያያዘ ተጨማሪ መረጃ በhttps://camb.ma/ccpdtransport ላይ ይገኛል።

ከተማዋ ለሁሉም ነዋሪዎቿ ተደራሽ ሆና መቀጠሏን ማረጋገጥ ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ አወጣጥ እና ቁርጠኛ የሆነ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ይጠይቃል። የተለያዩ የCambridge ኮሚቴዎች ማለትም Pedestrian፣ Bicycle and Transit Committees (የእግረኛ፣ የብስክሌት እና የሕዝብ ማመላለሻ ኮሚቴዎች) ወሳኝ ሚና የሚጫወቱት እዚህ ላይ ነው። እነዚህ በከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች የሚደገፉ እና በበጎ ፈቃደኛ ነዋሪዎች የተዋቀሩ ቡድኖች በCambridge የመጓጓዝ ቀላልነትን እና የከተማዋን ተደራሽነት ለሁሉም ሰው አመርኪ ለማድረግ የተያዘውን ጥረት ከፊት እየመሩ ናቸው።

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here