U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

በCambridge ውስጥ ያሉት የትራንስፖርት አገልግሎቶች አጠቃላይ እይታ

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024
" Cambridge 'የእግረኞች ገነት' እና 'የብስክሌት ነጂዎች ገነት' ተብላ እውቅና ተሰጥቷታል "

Cambridgeን ደማቅ እና በእንቅስቃሴ የተሞላች ከተማ ለማድረግ ጉልህ ሚና ከሚጫወቱት ነገሮች መካከል የትራንስፖርት አገልግሎት አንዱ ነው፤ ከተማው ለእግር ጉዞ አመቺ፣ ለመጓጓዝ ምቹ እና በውስጡም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ የያዘ በመሆኑ እዚህ ያሉ ነዋሪዎች፣ የንግድ ሥራዎች እና ጎብኝዎች በሙሉ ይደሰቱበታል። ከበፊቱ የበለጠ ብዙ የትራንስፖርት አገልግሎት አማራጮች አሉ እናም ቁጥራቸው እየጨመረ ያሉ ሰዎች በእግር መጓዝ፣ ብስክሌት መንዳት እና የሕዝብ ማመላለሻ መጠቀምን እየመረጡ ነው።

Cambridge በU.S. ለእግር ጉዞ እጅግ ምቹ የሆነችው ከተማ ተብላ ተሰይማለች። Walk Score ከዚህም አልፎ በእያንዳንዱ ምድብ ከMassachusetts ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበች "የእግረኞች ገነት” እና “የብስክሌት ነጂዎች ገነት” በማለት ለCambridge እውቅና ሰጥቷል። በPeopleforBikes የቅርብ ጊዜ ደረጃዎች መሠረት Cambridge ከ604 መካከለኛ መጠን (ከ50ሺህ እስከ 300ሺህ የሕዝብ ብዛት) ያላቸው የU.S. ከተሞች መካከል ብስክሌት ለመንዳት ባላት አመቺነት ከDavis፣ California ቀጥሎ 2ኛ ደረጃን ይዛለች።

አብዛኛው የCambridge አካባቢ አምስት የRed Line ማቆሚያዎችን፣ እንደ አዲስ የታደሰው በLechmere የሚገኘውን Green Line ጣቢያ፣ Commuter Rail፣ 26 የMBTA አውቶቡስ መስመሮችን እና በርካታ ለሕዝብ ተደራሽ የሆኑ ማመላለሻዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የሕዝብ ማመላለሻ አማራጮች በአጭር የእግር ጉዞ ርቀት ይገኛል። እ.ኤ.አ ከ2023 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ቀናት ላይ 80,000 የred line ጉዞዎችን፣ 3,500 የgreen line ጉዞዎችን እና 18,200 የአውቶቡስ ጉዞዎችን ጨምሮ ከ100,000 በላይ የሕዝብ ማመላለሻ ጉዞዎች በCambridge ውስጥ ይደረጋሉ።

በአሁኑ ወቅት ብስክሌት መንዳት ሙሉ በሙሉ አዋጭ የሆነ የትራንስፖርት ዘዴ ተደርጎ እየታየ ሲሆን ከፍተኛ እድገትም ታይቶበታል። በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ በብስክሌት መሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በCambridge ያሉትን የብስክሌት መገልገያዎች (ለምሳሌ የብስክሌት መንገዶች፣ የብስክሌት መንገድ መስመሮች፣ የጋራ መንገድ አመላካቾች) አጠቃላይ ርቀት እ.ኤ.አ 2004 ዓ.ም ከነበረበት 46.92 አጠቃላይ ማይል እ.ኤ.አ በ2023 ዓ.ም ወደ 105.3 አጠቃላይ ማይል አሳድጓል። በተጨማሪም በCambridge፣ Boston፣ Brookline፣ Somerville እና ከዚያም ባሻገር በሥራ ላይ እየዋለ ያለው Bluebikes የተሰኘ የብስክሌት መጋሪያ ሥርዓት በCambridge ባለቤትነት የተያዘ ነው። እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ከዚያ አንስቶ በመላው ሥርዓቱ ተሳፋሪዎች ከ23 ሚሊዮን በላይ ጉዞዎችን አድርገዋል። በMIT (Mass Ave./Amherst Street) የሚገኘውን እጅግ ተወዳጅ ጣቢያ ጨምሮ ሁሉም ተወዳጅ ጣቢያዎች የሚገኙት Cambridge ውስጥ ነው።

A rendering of Aberdeen Avenue and how it supports many modes of transportation.
Aberdeen Avenueን እና የተለያዩ የትራንስፖርት ዘዴዎችን የሚያስተናግድበትን መንገድ የሚያሳይ ምስል።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here