U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

እ.ኤ.አ ለ2024 ዓ.ም የነዋሪዎች መኪና ማቆሚያ ፈቃድ ስቲከር የተመረጠ የGraffiti Alley ፎቶ

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024

እ.ኤ.አ የ2024 ዓ.ም የነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ፎቶ ውድድር አሸናፊ ይፋ ተደርጓል። ከ200 በላይ ሰዎች ለዘንድሮው ውድድር ፎቶግራፎችን እና የሥነ-ጥበብ ሥራዎችን ካቀረቡ በኋላ የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች እ.ኤ.አ የ2025 ዓ.ም የነዋሪዎች መኪና ማቆሚያ ፈቃድ ስቲከር ሆኖ እንዲያገለግል Central Square ውስጥ የሚገኘውን Graffiti Alley የሚያሳይ አስደናቂ ፎቶ መርጠዋል። በMary Leno የተነሳው ፎቶ በየጊዜው የሚቀያየር ግራፊቲ፣ የጎዳና ላይ ሥነ-ጥበብ እና ማስታወቂያዎች የሚታዩበትን 80-ጫማ ርዝመት ያለው ቦታ ያሳያል። በይፋዊ ስሙ Richard B. “Rico” Modica Way ተብሎ የሚጠራው ስላች መንገድ የCentral Square እና የCambridge ከተማ መለያ ሆኗል። ወቅታዊ ማኅበራዊ ጉዳዮችን እና ሁነቶችን የሚዳስሱ የተለያዩ ጥበባዊ ቅጦችን በሚያሳዩት በየጊዜው የሚለዋወጡ ግራፊቲዎች እና የግድግዳ ሥዕሎች የታወቀ ነው። እ.ኤ.አ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በቀለማት ባሸበረቀ የፕላስቲክ መስታዎት መጠለያ የተሸነፈው ይህ ቦታ 24 ሰዓት እንደሚያገለግል ውጪ የሚገኝ የሥነ-ጥበብ አዳራሽ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል።

Graffiti Alley የተፈጠረው Geoff Hargadon በተባሉ በአካባቢው የሚኖሩ የሥነ-ጥበብ ባለሙያ እና በምግብ ቤት ሥራ ላይ በተሰማሩት Gary Strack ነው። በምስረታው ላይ እስከ Canada ድረስ ርቀው የሚገኙ 30 የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ጋብዘዋል። በጊዜ ሂደት እንደ Shepard Fairey፣ Momo እና Enzo & Nio ያሉ ታዋቂ አርቲስቶችን ጨምሮ በክልሉ እና ከዚያም ባሻገር የሚገኙ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችን መሳብ ችሏል።

በCambridge ውስጥ የሚገኙ ትዕይንቶችን ወይም ቦታዎችን የሚያሳዩ ዲጂታል ፎቶግራፎችን እና የሥነ-ጥበብ ሥራዎችን ለውድድሩ እንዲያቀርቡ በሁሉም የልምድ ደረጃ ላይ ያሉ ፎቶግራፍ አንሺዎች እና የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች ተጋብዘው ነበር። በCambridge Crossing የሚገኘውን ኩሬ፣ Cambridge Rindge እና የLatin ትምህርት ቤት ምልክትን፣ የCambridge Fire Department (የCambridge እሳት አደጋ መከላከያ) ዋና መሥሪያ ቤትን እና Cambridge City Hallን የሚያሳዩ ፎቶዎች ቀደምት ፈቃዶች ላይ ታይተው ነበር።

"የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ላላቸው ብቻ" ተብለው በተሰየሙ ሁሉም ቦታዎች ላይ መኪና ለማቆም የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ያስፈልጋል። ነዋሪዎች ቤታቸውን የሚጎበኙ ሰዎች ለሚጠቀሟቸው ሰውን ብቻ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች እና የሞተር ብስክሌቶች የሚያገለግሉ የነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ እና/ወይም የጎብኝዎች የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ። ፈቃዶች በየዓመቱ እ.ኤ.አ ማርች 31 ቀን ላይ መታደስ አለባቸው።

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here