U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

በሕዝብ ማመላለሻ ለሚደረጉ ጉዞዎች ቅድሚያ መስጠት

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024

የከተማ አስተዳደሩ ለእያንዳንዱ የጎዳና ማሻሻያ ፕሮጀክት የ

ጎዳና ንድፍ በሚያወጣበት ጊዜ የአውቶቡስ መንገዶችን እና ለሕዝብ ማመላለሻ አማራጮች ቅድሚያ የሚሰጡ ስትራቴጂዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባል። የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች እና መምሪያዎች በሕዝብ ማመላለሻ አማራጮች ለሚደረጉ ጉዞዎች ቅድሚያ የሚሰጡ ለውጦችን እንዲተገብሩ በከተማ አስተዳደሩ ፖሊሲዎች እና ዕቅዶች በኩል መመሪያ ይሰጣቸዋል።

እ.ኤ.አ በ2014፣ 2018 እና 2022 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ Cambridge ውስጥ በሚገኙት አብዛኛዎቹ የአውቶቡስ መስመሮች እየተፈጠረ የነበረው የአውቶቡስ መዘግየት እና ተዓማኒነት ማጣት ላይ ጥናት አካሂዷል። እ.ኤ.አ በ2018 ዓ.ም በተደረገ ጥናት የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች የአውቶቡስ መዘግየት እና ተዓማኒነት ማጣት ከፍተኛ ደረጃ የደረሱባቸውን አሳሳቢ ቦታዎች መለየት ችለዋል። እ.ኤ.አ በ2022 ዓ.ም በተደረገው ጥናት የMBTA Better Bus Project (የMBTA የተሻለ የአውቶቡስ አገልግሎት ፕሮጀክት) የአውቶቡስ መስመሮች ላይ ለውጥ ካደረገ በኋላ የቀሩ አሳሳቢ ቦታዎች መኖር ወይም አለመኖራቸውን መለየት ተችሏል።

የከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች አሳሳቢ በሆኑ ቦታዎች ላይ ሊተገበሩ የሚችሉ የአውቶቡስ መንገዶችን እና ለአውቶቡሶች ቅድሚያ የሚሰጡ የትራፊክ አስተዳደር ሥርዓቶችን ይገመግማሉ። ይህንን ለማድረግ የሚከተሉትን ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፦

  • በቀን ለተወሰኑ ሰዓታት ወይም ሙሉ ቀን መኪና ማቆምን እና መጫን እና ማውረድን ማገድ
  • የመኪና መንገድን ለአውቶቡሶች ጥቅም ብቻ መመደብ
  • አውቶቡሶች የትራፊክ ምልክቶች በተቀመጡባቸው መስቀለኛ መንገዶች ውስጥ በፍጥነት ማለፍ እንዲችሉ የአውቶቡስ ፌርማታዎችን ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር
  • በተለይ አውቶቡሶች በሚዘገዩበት ጊዜ አውቶቡሶቹ በሚጓዙባቸው አቅጣጫዎች የተቀመጡ የትራፊክ ምልክቶች ሥር አውቶቡሶች እንዲያልፉ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት።

የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ለአውቶቡሶች ቅድሚያ መስጠት የሚያስችሉ ተጨማሪ ዘዴዎችን እየመረመሩ ነው።

MBTA እና የሕዝብ ማመላለሻ ሥርዓቱ ላይ ተመሳሳይ አካሄድ ተግባራዊ ተደርጓል። የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች የተሻለ ደኅንነትን፣ አጠቃላይ አስተማማኝነትን እና ፍትሐዊነትን እያረጋገጡ በRed Line እና Green Line ላይ ከሚደረጉት ማሻሻያዎች ጋር በቅርበት ይሠራሉ እንዲሁም ማሻሻያዎቹን ያስተዋውቃሉ።

An MBTA green line train travels towards Lechmere station
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here