U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ለ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት የተቀመጡ ቁልፍ የከተማ አስተዳደር ተነሳሽነቶች ጥልቅ ዳሰሳ

2025 ኦገስት 28, ሐሙስ

ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶች

 

የከተማ አስተዳደሩ የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ City Council ቅድሚያ የሚሰጠው ቁልፍ ነገር በሆነው ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ይቀጥላል። የአዲስ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ አካታች የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ጥረቶች እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው መኖሪያ ቤት ባለቤትነት ፕሮግራሞችን ጨምሮ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶች ጋር ለተያያዙ ተነሳሽነቶች ከ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት እና ሌሎች የገንዘብ ድጋፍ ምንጮች ከ$48 ሚሊዮን በላይ ተመድቧል።

Affordable Housing Overlay (የተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶች ተጨማሪ ሕግ፣ AHO) የተሰኘው Zoning Ordinance (የዞን አወቃቀር ድንጋጌ) ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ከ680 በላይ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶች የAHOን የግምገማ ሂደት አጠናቅቀዋል ወይም በአሁኑ ወቅት እያካሄዱ ነው። በተለይም በ2025 ዓ.ም በጀት ዓመት 116 Norfolk Street ላይ 62 አዲስ ቋሚ ድጋፍ ሰጪ የኪራይ መኖሪያ ቤቶች ለአገልግሎት የተከፈቱ ሲሆን፣ በ2026 ዓ.ም በጀት ዓመትም 52 New Street እና የJefferson Park Federal መንግሥት መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ቦታዎች ላይ ግንባታ ይቀጥላል። የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በ1627 Massachusetts Avenue / 4 Mellon Street የሚገኘው የቀድሞው የLesley University ንብረት ላይ ጨምሮ በአሁኑ ወቅት በዕቅድ አወጣጥ ምዕራፍ ላይ ያሉ ወይም በቅርቡ ግንባታ ለመጀመር የተዘጋጁ የተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት ፕሮጀክቶች የተመደበ የገንዘብ ድጋፍን ያካትታል።

በተጨማሪም ከ100 በላይ አካታች የኪራይ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ ይቀጥላል። በ2023 ዓ.ም በጀት ዓመት የተጠናቀቀው Resident Experiences of Inclusion and Bias in Inclusionary Housing (የአካታች መኖሪያ ቤቶች የነዋሪዎች የአካታችነት እና የመድልዎ ተሞክሮ) ጥናት ላይ ለተጠቀሱት ጉዳዮች

ምላሽ ለመስጠት የከተማ አስተዳደሩ የአካታች መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎችን በማሳተፍ እና በመደገፍ መሥራቱን ይቀጥላል።

Department of Human Service Programs (የሰብዓዊ አገልግሎት ፕሮግራሞች መምሪያ፣ DHSP) የቤት አልባነት ያጋጠማቸው የማኅበረሰብ አባላትን ለመደገፍ ከውስጣዊ እና ውጫዊ አጋሮች ጋር በቅርበት ይሠራል። ለMunicipal Supportive Housing Vouchers ከሚውለው $1 ሚሊዮን በተጨማሪ DHSP የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ ለእነዚህ አገልግሎቶች $497,250 የሚያበረክት ሲሆን፣ እነሱም የመኖሪያ ቤት ፍለጋ እና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ማመልከቻ እርዳታን እና በFirst Church መጠለያ ለሚቀርበው የማኅበረሰብ ማዕድ እና የሻወር ፕሮግራም የሚውል የገንዘብ ድጋፍን ያካትታሉ። በ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት የከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪዎች የቤት ባለቤትነት ትምህርት እና በገቢ ብቁ ለሆኑ የመኖሪያ ቤት ገዢዎች የገንዘብ ድጋፍ እየሰጠ ይቀጥላል።

 

የፀረ-ዘረኝነት እና እኩልነት ተነሳሽነቶች

 

የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ የከተማ አስተዳደሩ ተግባራዊ ባደረገው ባለው የፀረ-ዘረኝነት፣ ብዝሐነት፣ እኩልነት እና አካታችነት (ADEI) ስትራቴጂ አማካኝነት መድልዎን እየተከላከለ እና አካታች አካባቢን እየገነባ ለመቀጠል አሁንም ቁርጠኛ ነው። እነዚህ ጥረቶች Office of Equity and Inclusion (የእኩልነት እና አካታችነት ጽሕፈት ቤት፣ OEI) እና በመላው ከተማ የሚገኙ ተነሳሽነቶችን ጨምሮ ነገር ግን በእነዚህ ሳይገደብ በመላው ከተማ የሚገኙ መምሪያዎችን ሥራ እና ትብብር የሚጠይቁ ሲሆን፣ የሚከናወኑትም በADEI መነጽር አማካኝነት ነው።

የሠራተኛ ተሳትፎ እና አስገዳጅ የሠራተኛ ሥልጠናዎችን ጨምሮ OEI በከተማ አስተዳደር ሠራተኞች ዙሪያ በርካታ ተነሳሽነቶችን ይመራል። የ2025 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ የዕቅድ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ብዝሐነት ያላቸው አመለካከቶችን በማካተት እና የCambridge ሠራተኞች እና ነዋሪዎችን ጨምሮ ከ2,500 በላይ ተሳታፊዎችን በመሳብ ለJuneteenth፣ የሂስፓኒክ/ላቲን ቅርስ ወር እና ሌሎች ብሔራዊ በዓላት የጤንነት ዝግጅቶች እና ባህላዊ ዝግጅቶችን አሰናድተዋል። በተጨማሪም OEI በCambridge የመጀመሪያውን የመድልዎ፣ ትንኮሳ እና የአጸፋ ምላሽ ፖሊሲ ለመፍጠር እና የምክንያታዊ ማመቻቻ ፖሊሲን ለማሻሻል ከከተማ አስተዳደር መምሪያዎች ጋር ሠርቷል። ይህ ጥረት በግልጽ ቋንቋ የተጻፉት እነዚህ ፖሊሲዎች በሥራ ቦታ ውስጥ ደኅንነት እና አካታችነትን እያበረታቱ እና የፌደራል ሕግን እያከበሩ መቀጠላቸውን ያረጋግጣል። የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት በOEI ቁጥጥር ሥር ለሚገኘው $100,000 ወይም ከዚያ በላይ የሚሆን ዋጋ የሚያወጡ የግንባታ ኮንትራቶች ላይ ከጠቅላላ ጨረታ ዋጋ ወይም የቁሳ ቁሶች ወጪ ውስጥ ቢያንስ አስር በመቶው እውቅና ካላቸው የአናሳ ማኅበረሰብ ንግድ ሥራዎች እንዲገኝ የሚያስገድደው Minority Business Enterprise ፕሮግራም የሚቀርብ ተጨማሪ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን፣ ይህም City Council ቅድሚያ የሚሰጠውን ቁልፍ የሆነ የኢኮኖሚያዊ ዕድል እና እኩልነት ጉዳይ ይደግፋል።

በመላው ከተማ የሚገኙ ሌሎች መምሪያዎችም በመምሪያው ውስጥ እና የቤተ መጻሕፍት ፀረ ዘረኝነት፣ እኩልነት እና አካታችነት ኮሚቴን በመሠረተው Cambridge Public Library (የCambridge የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት፣ CPL) ውስጥ ዘረኝነትን ለማጥፋት Drop Everything and Learn ተነሳሽነትን እያካሄደ የሚገኘውን Human Service (የሰብዓዊ አገልግሎት) ፕሮግራም ጨምሮ የፀረ-ዘረኝነት እና እኩልነት ተነሳሽነቶችን በመምራት ላይ ይገኛሉ። CPL እኩል በሆነ የቴክኖሎጂ ተደራሽነት አማካኝነት በኢኮኖሚ እና ኅብረተሰብ ውስጥ ተሳትፎን ለመደገፍ ከ230 በላይ ክሮምቡኮች እና 95 ሞባይል ሆትስፖቶችን በማዳረስ የDigital Equity Initiativeን እያስፋፋ ይገኛል። ወደ ሥራ ከገባው የፍትሕ ሥርዓት ዳሽቦርድ እና የBody Worn Cameras ፕሮግራም ትግበራ ጀምሮ ወጣቶች፣ በዕድሜ ከፍ የሚሉ አዋቂዎች እና የእምነት ማኅበረሰቡ ዘንድ እስካለው ተጨማሪ የነዋሪዎች የማኅበረሰብ ተሳትፎ ድረስ በPolice Department (የፖሊስ መምሪያ) ውስጥም ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ እኩልነትን እውን ለማድረግ የሚሠራውን ሥራ ወደፊት የሚያራምዱ እና ለከተማ አስተዳደሩ ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ሆኖ እንዲቀጥል OEIን የሚያማክሩ ከተለያዩ መምሪያዎች የተውጣጡ 12 ሠራተኞች የያዘውን በዓይነቱ የመጀመሪያ የADEI ምክር ቤት መሥርቷል። ይህ ምክር ቤት በ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት እና ከዚያም ባሻገር ለወደፊት የADEI ጥረቶች ሞዴል ሆኖ ያገለግላል።

 

ክፍት ቦታዎች እና የማኅበረሰብ ኮሪደሮች እና አደባባዮች

 

የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ የከተማ አስተዳደሩ በመላው Cambridge በሚገኙ የክፍት ቦታ ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት እያደረገ ይቀጥላል። እነዚህም በPeabody ትምህርት ቤት መጫወቻ ሜዳ እና Gold Star Mother’s Park ያሉትን ግንባታዎች ማጠናቀቅ እንዲሁም በCambridge Highlands በሚገኘው Rafferty Park እና Neighborhood Nine በሚገኘው Raymond Park እድሳቶች ማስጀመርን ያካትታሉ። በተጨማሪም የDanehy Park የካፒታል ማሻሻያዎች እቅድ በዚህ በጀት ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የከተማ አስተዳደሩም Hoyt Field እና mid-Cambridge ፓርኮች ላይ ለሚደረጉት ማሻሻዎች እቅድ ለማውጣት የማኅበረሰብ ተሳትፎ ጥረቶችን ይጀምራል።

ከዚህ ባለፈ አካባቢ ተኮር ዕቅድ አወጣጥ ላይ ለመሳተፍ በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የከተማ አስተዳደሩ በCambridge ባለብዙ አገልግሎት ኮሪደሮች እና አደባባዮች እንዲሁም ከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የኢኮኖሚ እና የማኅበረሰብ ማዕከሎች ውስጥ የያዛቸውን የዕቅድ አወጣጥ እና የዞን አወቃቀር ተነሳሽነቶች ይቀጥላል። እነዚህ እቅዶች በCambridge Street ኮሪደር እና Central Square ለሚደረጉ የዞን አወቃቀር ለውጦች የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን፣ በCambridge Common እና Alewife Brook Parkway መካከል የሚገኘው Massachusetts Avenue ኮሪደር ላይ የሚሠሩ ተጨማሪ የልማት ሥራዎችን እና Alewife MBTA ጣቢያ እና አጠገቡ የሚገኘው የገበያ ማዕከል ዙሪያ በድጋሚ የሚዋቀረውን ዞን እና የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ልማት ያካትታል። የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ጣቢያዎችን መገኛ ከግምት ውስጥ ያስገቡ መኖሪያ ቤቶች፣ የእግረኛ እና ብስክሌተኛ ደኅንነት እና በእነዚህ ቦታዎች ውስጥ ያለውን ለአካባቢ ተስማሚነት የሚመለከቱ ሰፊ ግቦችን ለማሳካት በሚሠራበት ጊዜ የሠራተኛ ቡድኖች በአካባቢው የሚገኘውን ማኅበረሰብ በእያንዳንዱ መስክ እያሳተፉ ይቀጥላሉ።

 

ቅድመ መደበኛ ትምህርት እና ከትምህርት ሰዓት ውጪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች

 

ሴፕቴምበር ወር 2024 ዓ.ም ላይ Cambridge Public Schools እና የCambridge Office of Early Childhood (የCambridge የቅድመ ልጅነት ጽሕፈት ቤት፣ OEC) ባደረጉት የጋራ ጥረት እና City Council ለረጅም ጊዜ ቅድሚያ ሰጥቶ በያዘው ጉዳይ የCambridge Preschool ፕሮግራም (CPP) ሥር የሚገኙ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ውስጥ ምዝገባ ተጀምሯል። ከ800 በላይ የCambridge ቅድመ መደበኛ ትምህርት ተማሪዎች Cambridge ውስጥ ወደሚገኙት ከCPP ጋር ግንኙነት ያላቸው 23 ቅድመ መደበኛ ትምህርት አቅራቢዎች ይገባሉ። OEC የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ ለCambridge ልጆች ጥራት ያለው ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ፣ የቅድመ ልጅነት ትምህርት ሰጪዎችን ለመደገፍ እና ለመጪው የCPP ማመልከቻ ዙር የቤተሰብ ግብረ መልስን ለማካተት ይህንን የተዋሃደ አቅርቦት ፕሮግራም ለማስፋፋት ይሠራል።

ከዚህ በተጨማሪም Department of Human Service Programs (DHSP) ለCambridge ቤተሰቦች በዋጋ ተመጣጣኝ እና ተደራሽ የሆኑ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ከትምህርት በኋላ የሚደረጉ ፕሮግራሞችን ጨምሮ ከትምህርት ሰዓት ውጪ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችን ተደራሽነት ለማሳደግ ጠንክሮ እየሠራ ይቀጥላል። የ2025 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ የተከናወነው የOut-of-School Time Expansion ጥናት ቦታ መጋራት፣ ልዩ ፍላጎቶች ያላቸው ልጆችን ማካተት እና የሠራተኛ ኃይልን ማረጋጋት እነዚህ ፕሮግራሞች ሊያተኩሩባቸው የሚገቡ ወሳኝ አካባቢዎች መሆናቸውን ለይቷል።

ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ DHSP ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጡ ፕሮግራሞች ላይ ተጨማሪ 246 ቦታዎችን በመጨመር ለእነዚህ ፕሮግራሞች ያለውን የተጠባባቂዎች ዝርዝር ርዝመት መቀነስ ችሏል። የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ DHSP በመላው ከተማ የሚገኙ ፕሮግራሞች ውስጥ ያሉትን ቦታዎች የሚጨምር ሲሆን፣ ተጨማሪ የሙሉ ጊዜ ሠራተኞችን እና የሙሉ ጊዜ የአካታችነት ስፔሻሊስቶችን ይጨምራል። DHSP ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ጨምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጥረቶችን ለማስፋፋትም ቅድሚያ ሰጥቶ ይሠራል።

 

የአካባቢ ተስማሚነት እና የአየር ንብረት ጥበቃ እርምጃ

 

አሁንም ቢሆን ከካርቦን ልቀት ነፃ ለመሆን የሚደረገው ግስጋሴ የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ተስማሚነት ማዕቀፍ ወሳኝ አካል ነው። የ2025 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ የተቋቋመው Office of Sustainability (የአካባቢ ተስማሚነት ጽሕፈት ቤት፣ OoS) ከከተማ አስተዳደሩ የNet Zero Action Plan (ምንም በካይ የማያመነጭ ለመሆን የድርጊት መርሐ ግብር) እና Building Energy Use Disclosure Ordinance (የህንፃ የኃይል አጠቃቀም ማሳወቂያ ድንጋጌ፣ BEUDO) ጋር የሚጣጣሙትን እነዚህን ጥረቶች ይመራል። የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ OoS ኃይል የመቆጠብ እና የፎሲል ነዳጆች ላይ ጥገኝነትን የመቀነስ ግቦች በመያዝ ለነዋሪዎች እና የንግድ ሥራዎች የማኅበረሰብ የኃይል አቅርቦት ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ እና የBEUDO ደንቦችን እያጠናቀቀ እና ተግባራዊ እያደረገ ይቀጥላል።

በCambridge ውስጥ እና ከዚያም ባሻገር የሚገኙ የማኅበረሰብ አባላትን በተሻለ መልኩ ከእነዚህ ጥረቶች ጋር ለማገናኘት OoS ኤፕሪል ወር 2025 ዓ.ም ላይ በwww.cambridgema.gov/sustainable የሚገኘውን Sustainable Cambridge ድረ ገጽ በሥራ ላይ አውሏል። ድረ ገጹ የአካባቢ ተስማሚነት ዳሽቦርድ፣ ለSustainable Cambridge የወቅታዊ መረጃ ኢሜይሎች መመዝገቢያ አገናኝ እና ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል/ብስባሽ ማዳበር፣ ኃይል መቆጠብ እና ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን የሚመለከቱ መረጃዎች ይይዛል።

በተጨማሪም በ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ሞቃታማ የሰመር (በጋ) ወቅቶች እና ለመገመት የሚያዳግቱ ዊንተር (ክረምት) ወቅቶችን ጨምሮ ይበልጥ ተለዋዋጭ እየሆኑ ለመጡት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ለመዘጋጀት በመላው ከተማ የሚገኙ መምሪያዎች በአንድ ላይ እየሠሩ ይገኛሉ። OoS ለድጋፍ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ሰዎች እና ቦታዎች ግብዓቶችን ለመለየት እና ለማድረስ እየሠራ ነው።

 

የትራንስፖርት አገልግሎት እና ደኅንነታቸው የተጠበቀ ጎዳናዎች

 

የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት the Port ውስጥ፣ በCentral Square የሚገኘው Massachusetts Avenue እና ከHarvard Square ጀምሮ በሰሜን አቅጣጫ እስከ Cambridge-Arlington line ድረስ የተዘረጋው Massachusetts Avenueን ጨምሮ የCambrige ጎዳናዎች ላይ እየተካሄዱ ያሉ በርካታ የDepartment of Public Works (የመንግሥት ሥራዎች መምሪያ፣ DPW) የግንባታ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ይደግፋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች ዕድሜ እና ችሎታ ምንም ይሁን ምን እግረኞች፣ ብስክሌተኞች፣ የሞተር ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ጨምሮ ሁሉንም ተጠቃሚዎች ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ የሚያገለግሉ ጎዳናዎች ለመገንባት የተነደፈውን Complete Streets እና የከተማ አስተዳደሩ የትራፊክ አደጋ ሞቶችን እና ከፍተኛ ጉዳቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የነደፈውን Vision Zero ተነሳሽነቶች ወደፊት ለማራመድ የከተማ አስተዳደሩ ባለው ቁርጠኝነት የሚመሩ ናቸው። የከተማ አስተዳደሩ በመላው Cambridge የተለዩ የብስክሌት መስመሮች አውታረ መረብ እንዲገነባ በሚያስገድደው የCity Council Cycling Safety Ordinance (የብስክሌት ደኅንነት ድንጋጌ) ሥርም የDPW ፕሮጀክቶች ለብስክሌት ደኅንነት አጽንዖት ሰጥተው ይሠራሉ።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ Linear Park፣ የGrand Junction ባለብዙ አገልግሎት መንገድ እና Fresh Pond እና Danehy Parkን የሚያገናኝ አዲስ መንገድን ጨምሮ ከመኪና ነፃ የሆኑ የእግረኛ እና የብስክሌተኛ መገልገያዎችን እያስፋፋ ይገኛል። እነዚህ ፕሮጀክቶች በአንድ ላይ 2.8 ማይሎች የሚሆኑ ከትራፊክ የተለዩ በተፈጥሮ የተዋቡ መንገዶችን በመፍጠር ለአካባቢ ተስማሚ ትራንስፖርት ደኅንነት እና ተደራሽነትን ያሳድጋሉ። የከተማ አስተዳደሩ በዋነኝነት እንደ ትምህርት ቤቶች እና የንግድ ሥራ ዲስትሪክቶች ባሉ ቁልፍ ቦታዎች ላይ እና በመላው Cambridge 150 የብስክሌት ማቆሚያዎች እና ሌሎች መገልገያዎችን ይገነባል። ለCambridge ተማሪዎች የብስክሌት ደኅንነት ትምህርት እና ሥልጠና ከሚያቀርበው በሂደት ላይ ያለው Safe Routes to School ፕሮግራም በተጨማሪ የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ የከተማ አስተዳደሩ በቀላል የግል መጓጓዣዎች ዙሪያ አዲስ የትምህርት ክፍል ያስጀምራል።

ከዚህም ባሻገር MBTA ወደ የBus Network Redesign ፕሮጀክቱ ቀጣይ ምዕራፍ ሲገባ የCommunity Development Department (የማኀበረሰብ ልማት መምሪያ) በCambridge ሰፈሮች ውስጥ የመተላለፍያዎችን ተደራሽነት ለማሻሻል ከMBTA ጋር በቅርበት እየሠራ ይቀጥላል። የከተማ አስተዳደሩ በ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት Cambridge ውስጥ የሚገኙት የመጓጓዣ አገልግሎቶች ዙሪያ አዲስ ጥናትም ያካሂዳል።

 

የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት እየተቀየረ ባለ የኢኮኖሚ አካባቢ ውስጥ ለፋይናንስ ተለዋዋጭነት ቅድሚያ ይሰጣል

 

የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት እየተቀየሩ ያሉ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ አዝማሚያዎች እና በፌደራል ደረጃ እያደገ የመጣ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ባለበት አውድ ውስጥ የተዘጋጀ ነበር። ይህም ከAmerican Rescue Plan (ARPA) የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ ጋር ተዳምሮ የበጀት አወጣጥ ሂደቱ ተጋላጭ ነዋሪዎችን እየጠበቀ የፋይናንስ መረጋጋትን ለመጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጥ እንዲሆን አድርጓል። የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት የከተማ አስተዳደሩን የሥራ ማስኬጃ ፍላጎቶች በመደገፍ እየቀጠለ በተመሳሳይ ሰዓት ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ቢፈጠሩ የፋይናንስ ተለዋዋጭነትን ያረጋግጣል።

በአሁኑ ወቅት አመቺ ያልሆኑ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ አዝማሚያዎች የአካባቢያዊ እና ብሔራዊ ኢኮኖሚው ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው። በ2025 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የU.S. ኢኮኖሚ አፈግፍጓል፣ የሸማች እምነት ቀንሷል እና ታሪፎች በፈጠሩት ስጋት ምክንያት ኢንቨስትመንት ተቀዛቅዟል። Cambridge ለዓመታት ጠንካራ የንግድ ዘርፍ እድገት እና እየጨመሩ የነበሩ የንብረት ዋጋዎችን እያስመዘገበች የቆየች ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማ አስተዳደሩ የሪል እስቴት ገበያ መቀዛቀዝ አሳይቷል። እነዚህ አዝማሚያዎች የከተማ አስተዳደሩ ገቢውን ለማሰባሰብ የንብረት ግብሮች ላይ ይበልጥ ጥገኛ እንዲሆን ሊያደርጉ ይችላሉ። በእነዚህ ምክንያቶች የከተማ አስተዳደሩን ፕሮግራሞች እና ተነሳሽነቶች ለማስቀጠል እና ወደፊት ለሚመጡ የማኅበረሰብ ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት የፋይናንስ ተለዋዋጭነትን መጠበቅ እጅግ ወሳኝ ነው። በዚህ ርዕስ ላይ የተደረጉ ተከታታይ ስብሰባዎችን ተከትሎ City Manager ከFinance Committee (ፋይናንስ ኮሚቴው) እና City Council ጋር በመሆን አስፈላጊ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ሳይቋረጡ የፋይናንስ ተለዋዋጭነትን ለመጠበቅ የከተማ አስተዳደሩን የበጀት እድገት የሚቆጣጠር ዕቅድ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የARPA የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ በመካሄድ ላይ ባሉ የማኅበረሰብ ፕሮግራሞች ውስጥ የከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል። ከCOVID-19 ወረርሽኝ በኢኮኖሚ እንዲያገግሙ ማኅበረሰቦችን ለመርዳት ታልሞ የተዘጋጀው የARPA የገንዘብ ድጋፍ ከአነስተኛ ንግድ ሥራዎች ድጋፍ ጀምሮ እስከ የቤት አልባ ግለሰቦች ድጋፍ ፕሮግራሞች ድረስ በርካታ ወሳኝ የከተማ አስተዳደር ፕሮግራሞችን በገንዘብ ደግፏል። ያለው ነባር የARPA ገንዘብ እስከ 2026 ዓ.ም ድረስ ወጪ ተደርጎ ማለቅ ያለበት ሲሆን፣ ምንም ተጨማሪ ገንዘብ አይመደብም። ከARPA የገንዘብ ድጋፍ ባሻገር ቀደም ሲል ተመድበው ነገር ግን በፌደራል የበጀት ለውጦች፣ በአስፈፃሚ አካል ትዕዛዞች ወይም ከከተማ አስተዳደር ፖሊሲዎች እና እሴቶች ጋር የማይጣጣሙ የድጎማ ገንዘብ ቅድመ ሁኔታዎች ዙሪያ በተነሱ የሕግ ክርክሮች ምክንያት ተጽዕኖ ሊያድርባቸው የሚችሉ ሌሎች የፌደራል የገንዘብ ድጋፎች ላይ ስጋቶች አሉ።

በፌደራል የገንዘብ ድጋፍ ዙሪያ ላሉት እነዚህ ስጋቶች እና እየተለወጡ ላሉ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ምላሽ ለመስጠት መጀመሪያ የቀረበው የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት ለMunicipal Supportive Housing Voucher ፕሮግራም የሚውል ተጨማሪ $1 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያካትት ተደርጎ ተሻሽሏል። ከ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት የተነጠለ ቢሆንም፣ የገንዘብ ድጋፎች ቢቋረጡ የሚያገለግል በጠቅላላው $5 ሚሊዮን ለፌደራል የድጎማ ገንዘብ ማረጋጊያ ፈንድ ተመድቧል።

በመላው ዓመት እና የበጀት ሂደቱ ውስጥ የBudget Office (የበጀት ጽሕፈት ቤት) ያለማቋረጥ ወደፊት አምስት ዓመታት የሚመለከቱ ትንበያዎችን ያቀርባል እንዲሁም ይከልሳል። በዚህ መንገድ የከተማ አስተዳደሩ በኢኮኖሚያዊ አካባቢው ላይ ለሚፈጠሩ ለውጦች እና ሊነሱ ለሚችሉ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ለመዘጋጀት ጥረት ያደርጋል። በተጨማሪም የከተማዋ ኢኮኖሚያዊ አቋም የCambridge ማኅበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች እየተደረጉ በተመሳሳይ ሰዓት ላልተጠበቁ ሁኔታዎች ለመዘጋጀት ሲከናወኑ በነበሩ ዓመታትን የዘለቁ የመጠባበቂያ ዕቅዶች እና ጥረቶች የጎለበተ ነው።

ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው፣ የከተማ አስተዳደሩ ለCambridge ማኅበረሰብ ወሳኝ አገልግሎቶች እና ፕሮግራሞችን ለማቅረብ በቁርጠኝነት እየሠራ ይቀጥላል። የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት በጀት ይህንን ቁርጠኝነት በማንፀባረቅ ያልተረጋጋ ኢኮኖሚ የሚኖርባቸውን ጊዜያት ተቋቁሞ ለማለፍ አስፈላጊ የሆነውን የፋይናንስ አቅም ይገነባል።

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here