U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የሠራተኞች መገለጫ፦ Daniel Liss፣ ዋና የበጀት ተንታኝ

2025 ኦገስት 28, ሐሙስ
" በCOVID ጊዜ PBን ለመቀጠል በሀገሪቷ የመጀመሪያው ማዘጋጃ ቤት ነበርን... እና እጅግ በጣም ጥሩ አፈጻጸም ከማሳየታቸው የተነሳ አሁንም እየተጠቀምን የቀጠልንባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዓይነቶች ማግኘት ችለናል። "

በከተማ አስተዳደሩ Budget Department (የበጀት መምሪያ) ዋና የበጀት ተንታኝ ለሆኑት Daniel Liss አስደሳች የሆኑት የሕዝብ አገልግሎት ሥራ ገጽታዎች የሚታዩት ከመጋረጃው ጀርባ ነው።

Liss ባላቸው የሥራ ሚና ከሌሎች የበጀት ተንታኞች፣ የአጠቃላይ ፋይናንስ ቡድን እና በመላው ከተማ ከሚገኙ መምሪያዎች ጋር የCambridgeን በጀት ለመቅረጽ፣ ለመከታተል እና ለማጥናት በትብብር ይሠራሉ። በተለይ በጀቶቻቸውን ሲያቅዱ ከመምሪያዎች ጋር መሥራት እና እያንዳንዱ መምሪያ ለነዋሪዎች ስለሚያቀርባቸው ልዩ አገልግሎቶች ማወቅ ያስደስታቸዋል።

“[ከመምሪያዎች ጋር በጋራ] ካልተሠራ አዕምሯዊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው። አለ አደል፣ እንደ የሒሳብ ችግር ነው” ሲሉ Liss ተናግረዋል። "ሆኖም ከDHSP (Department of Human Service Programs) ወይም Community Safety (የማኅበረሰብ ደኅንነት) ወይም ሌሎች መምሪያዎች በሙሉ ጋር የምሠራው ሥራ ለማኅበረሰቡ ማድረግ የሚችሉት ነገር ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ማወቁ በየዕለቱ ወደ ሥራ ለመምጣት እንድጓጓ የሚያደርገኝ ነገር ነው።"

Liss የCambridge ከተማ አስተዳደርን ከመቀላቀላቸው በፊት የአካባቢ መስተዳድር አገልግሎትን የሚያበረታታ ድርጅት ውስጥ ጨምሮ ለትርፍ ባልተቋቋሙ የፋይናንስ እና የአስተዳደር ተቋማት አገልግለዋል። ትውልዳቸው የሕዝብ አገልግሎት ጽንሰ ሃሳብን የሚረዱበትን መንገድ ከመንግሥት ሥራ አርቀው ለትርፍ ላልተቋቋሙ ድርጅቶች መሥራት ላይ ያተኮሩበትን መንገድ የሚዳስስ ሪፖርት አለቃቸው ካሳያቸው በኋላ በወቅቱ ይኖሩበት በነበረው Boston ውስጥ የአካባቢ መስተዳድር አገልግሎቶችን ሁኔታ እንዲዳስሱ አነሳስቷቸዋል።

"ወደ Boston ከተማ አስተዳደር ድር ጣቢያ ሄድኩኝ እና የተዘረዘሩትን መምሪያዎች ስመለከት እና ስለፕሮግራሞቹ ሳነብ በሕይወቴ ውስጥ ከአካባቢ መስተዳድር አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሆንኩባቸውን መንገዶች ሁሉ እያሰብኩ ነበር። ከዚህም በላይ እንደመታደል ሆኖ ለእኔ አስፈላጊ ስላልሆኑት አገልግሎቶች ሁሉ እያነበብኩ ነበር" ሲሉ Liss ተናግረዋል።

ከዚያ ዕድሉን ቢያገኙ ለአካባቢ መስተዳድር የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ወሰኑ እና ከጊዜ በኋላም Cambridge በሚገኘው የBudget Department ይህን ዕድል አገኙ።

የማዘጋጃ ቤት በጀት በሚታቀድበት ጊዜ ከተማ አስተዳደሩ ረጅም ጊዜ ለሚዘልቅ የፋይናንስ መረጋጋት እና ስኬት የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥን እና በአሁኑ ወቅት ላሉ ነዋሪዎች አስፈላጊ አገልግሎቶች ማቅረብን ማመዛዘን አስፈላጊ መሆኑን Liss ይናገራሉ። ይህ አካሄድ የከተማ አስተዳደሩ የወረርሽኙን ተጽዕኖዎች ተቋቁሞ ማለፍ እንዲችል ያገዘ ሲሆን፣ ከሌሎች ከተሞች እና አነስተኛ ከተሞች በተለየ መልኩ COVID ሲመጣ Cambridge ማንንም ከሥራ ለማባረር እንዳልተገደደ Liss ይጠቅሳሉ።

"በዚያን ጊዜ ለከተማ አስተዳደሩ የሚሠራውን ሥራ አጓጊ ያደርገው የነበረው ነገር አብዛኛዎቹ ሌሎች ቦታዎችም ሲጠይቁ የነበረው 'መዝገቦቹን እንዴት ማመዛዘን እንችላለን? ይህን እንዴት እንዲሠራ ማድረግ እንችላለን?' የሚሉት ጥያቄዎች መሆናቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል። "በእንደዚያ ዓይነት ቀውስ ውስጥ ሰፋ ያሉ ፍላጎቶችን ማሟላት እንድንችል 'ነገሮችን እንዴት እንቀጥላለን ወይም አብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም ከምናደርገው ባለፈ እንዴት አገልግሎቶችን ማስፋፋት እንችላለን?' የሚለውን ጥያቄ እየዳሰስን ነበር።"

Liss ከመምሪያዎች ጋር ከመሥራት እና የከተማ አስተዳደሩን በጀት ለማዘጋጀት ከመርዳት በተጨማሪ Participatory Budgeting (PB) እና የCommunity Preservation Act (የማኅበረሰብ ጥበቃ አዋጅ) ኮሚቴ ውስጥም ተሳትፎ ያደርጋሉ። በአሁኑ ወቅት የሥራቸው ትልቅ አካል መሆን ያቆመ ቢሆንም 2020 ዓ.ም ላይ ጊዜያዊ የPB አስተባባሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ በወረርሽኙ ወቅት Cambridge ሂደቱን መቀጠል ብቻ ሳይሆን ማሻሻልም በቻለችበት መንገድ ኩራት ይሰማቸዋል።

“በCOVID ጊዜ PBን ለማስቀጠል እና ወደ ሥራ የሚገባበትን መንገድ ለማግኘት የመጀመሪያው ማዘጋጃ ቤት የነበርን ሲሆን፣ ከወረርሽኙ ውጪ ተቀባይነት ከሚኖራቸው ሂደቶች አንፃር ተመሳሳይ ጥራት እና ደረጃ ያልነበረው ቢሆንም ... ማድረግ ግን ችለናል፣ ብዙ ሰዎች ጋር መድረስ የሚችሉ እና ከሰዎች ጋር ፊት ለፊት ወደ መነጋገር ሁኔታ ከተመለስን በኃላም ቢሆን እጅግ በጣም ጥሩ ውጤት ከማሳየታቸው የተነሳ ከወረርሽኙ በኋላ የቀጠልንባቸውም የግንዛቤ ማስጨበጫ ዓይነቶችን ማግኘት ችለናል" ሲሉ Liss ተናግረዋል።

ከሥራ ውጪ Liss የክላሲካል ሙዚቃ ወዳጅ፣ ትጉህ የሲዲ ሰብሳቢ እና የረጅም ጊዜ የRed Sox አድናቂ ናቸው። 2009 ዓ.ም ላይ Cambridge መኖር የጀመሩ ሲሆን፣ 2013 ዓ.ም ላይም Cambridge ውስጥ በሚገኘው እያንዳንዱ የፒዛ ሬስቶራንት በመመገብ የከተማዋን ሰፈሮች በሙሉ አስሰዋል።

Liss Cambridge ውስጥ በሚገኘው ጠንካራ የማኅበረሰብ ስሜት፣ የትራንስፖርት ቀላልነት እና ከCharles River እና በርካታ የድሮ የትምህርት ተቋማት አቅራቢያ በሆነው መገኛው እጅግ ይደሰታሉ። ከዚህ በተጨማሪም ለመጀመሪያ ጊዜ የአካባቢ መስተዳድር የሥራ ዕድሎችን ከመረመሩበት ጊዜ አንስቶ ለረጅም ጊዜ ለመሳተፍ በተመኙበት ሕዝባዊ አገልግሎቶች አማካኝነት ይህንን ማኅበረሰብ ለመደገፍ የከተማ አስተዳደሩ በሚያሳየው ቁርጠኝነት ይደነቃሉ።

“ያንን የረጅም ጊዜ ግብ ማሳካት በመቻሌ አመስጋኝ ስሆን፣ በመላው ከተማ የሚገኙ የሥራ ባልደረቦቼ እያንዳንዳቸው ለሚመለከታቸው የሥራ ጉዳይ ምን ያህል እንደሚያስቡ፣ ለነዋሪዎች ምን ያህል እንደሚያስቡ እና በተቻለ መጠን ከፍተኛ ጥራት ያላቸው አገልግሎቶች ማቅረብ መቻላችንን ለማረጋገጥ ምን ያህል እንደሚጨነቁ ስመለከት ተስፋ ካደረኩት በላይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" በማለት Liss ተናግረዋል።

Daniel Liss posing with former Deputy City Manager Owen O’Riordan, Mayor E. Denise Simmons, and City Manager Yi-An Huang (left-to-right) at the 2024 Employee Awards in Cambridge City Hall.
በ2024 ዓ.ም የሠራተኛ ሽልማቶች ላይ Daniel Liss ከቀድሞው Deputy City Manager Owen O’Riordan፣ Mayor E. Denise Simmons እና City Manager Yi-An Huang (ከግራ ወደ ቀኝ) ጋር ፎቶ እየተነሱ።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here