የከተማ አስተዳደሩ የሰፊው ሕዝብ አባላት እና City Council የሚሰጡትን ግብረ መልስ በበጀት አወጣጥ ሂደቱ ውስጥ እና ከዚያም ባሻገር ለማካተት ይሠራል። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተነሱት በሀገራችን ያለውን ያልተረጋጋ ሁኔታ እና የፌደራል የገንዘብ ድጋፍ የሚመለከቱ ስጋቶች በCity Manager የቀረበውን የመጀመሪያው የ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ የተደረገ ማሻሻያ እና የትርፍ በጀት ድልደላን ቀርጸዋል።
በአዲሱ Municipal Supportive Housing Vouchers (MSHV) ፕሮግራም አማካኝነት መኖሪያ ቤት ለሌላቸው ግለሰቦች የማዘጋጃ ቤት ቫውቸሮች ለማዘጋጀት ተጨማሪ $1 ሚሊዮን ተመድቧል። የመኖሪያ ቤት ተደራሽነትን ማሻሻል ለረጅም ጊዜ የቆየ የCity Council እና የCity Manager ግብ ነው። ለMSHV ፕሮግራም የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የከተማ አስተዳደር ሀብቶችን ይበልጥ ድጋፍ ወደሚያስፈልጋቸው ነዋሪዎች ለመምራት ይረዳል። ወደ ቋሚ መኖሪያ ቤት በሚደረገው ሽግግር በኩል 25 መኖሪያ ቤት የሌላቸው ግለሰቦችን ይደግፋል። በተጨማሪም እነዚህ ግለሰቦች ይህንን ሽግግር ማለፍ እንዲችሉ የሚረዱ ቀጣይነት ያላቸው የድጋፍ አገልግሎቶች ይቀርቡላቸዋል። ይህም የDepartment of Human Service Programs የሥራ ማስኬጃ በጀት ላይ ከተደረገው የ$1 ሚሊዮን ጭማሪ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛል።
እስከ የ2025 ዓ.ም ኦገስት ወር መጨረሻ ወይም ሴፕቴምበር ወር ድረስ ቀደም ብሎ እንደሚጀምር የሚጠበቀው የMSHV ፕሮግራም በCambridge Housing Authority (CHA) ይተዳደራል። ለፕሮግራሙ ትግበራ ለመዘጋጀት የከተማ አስተዳደሩ እና CHA በዚህ ሰመር (በጋ) ወቅት ተከራዮች ለመምረጥ የሚያስችለውን የቅድሚያ አሰጣጥ ሂደት ለመንደፍ በጋራ ይሠራሉ። ፕሮግራሙ ለረጅም ጊዜ ቤት አልባ ሆነው ለቆዩ እና ቀጣይነት ያላቸው ደጋፊ አገልግሎቶች ለሚያስፈልጋቸው ግለሰቦች ቅድሚያ ይሰጣል።
ከተረጋጋ መኖሪያ ቤት፣ የምግብ እጥረት፣ የአዕምሮ ጤና ድጋፍ እና የማሞቂያ ነዳጅ እርዳታ ጋር የተያያዙትን ጨምሮ ተጋላጭ ነዋሪዎችን የሚያገለግሉ በርካታ የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶች የፌደራል የገንዘብ ድጋፍ ላይ የሚተማመኑ ናቸው። የከተማ አስተዳደሩ በ2026 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ$12 ሚሊዮን በላይ የፌደራል የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኝ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ በአስፈጻሚ ትዕዛዞች፣ የፌደራል በጀት ለውጦች ወይም ከከተማ አስተዳደር ፖሊሲዎች እና እሴቶች ጋር የማይጣጣሙ የድጎማ ገንዘብ ቅድመ ሁኔታዎች ዙሪያ በሚኖሩ ተግዳሮቶች ምክንያት አንዳንድ የሚጠበቁ የገንዘብ ድጋፎች ስጋት ላይ ሊሆኑ ይችላሉ።
ከትርፍ በጀት በተመደበው የ$5 ሚሊዮን የፌደራል የድጎማ ገንዘብ ማረጋጊያ ፈንድ አማካኝነት የከተማ አስተዳደሩ ሊከሰቱ ለሚችሉ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳዎች ምላሽ የመስጠት እና የረጅም ጊዜ መረጋጋትን የመደገፍ አቅም ይኖረዋል።
ይህ ጠቃሚ ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳዎች ቢከሰቱም ለከተማ አስተዳደር ፕሮግራሞች አማራጭ የረጅም ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ምንጮች እስኪገኙ ድረስ ለተጋላጭ ነዋሪዎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን ማስቀጠል እንዲቻል የከተማ አስተዳደሩን ይረዳል። የፌደራል የድጎማ ገንዘቦች ከታጡ፣ እነዚህን ክፍተቶች ለማጥበብ የፌደራል የድጎማ ገንዘብ ማረጋጊያ ፈንድ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ይህ እርምጃ በፌደራል ደረጃ የሚወሰዱ የፋይናንስ ውሳኔዎች ዙሪያ እየጨመረ የመጣውን አለመተማመን እና የCambridge ነዋሪዎች ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ተጽዕኖ ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩን ያግዛል።
በተጨማሪም፣ በመጨረሻም ዓመታዊ በጀቱ ላይ የተደረጉት ማሻሻያዎች እና የትርፍ በጀት ድልድል የከተማ አስተዳደሩ የገንዘብ አቅም ሕዝቡ እና City Council ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች ምላሽ መስጠት የሚችል ሆኖ መቀጠሉን በማረጋገጥ፣ አለመረጋጋት በሚታይባቸው ጊዜያት ውስጥ መረጋጋትን ይጠብቃሉ።