U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንጹህ ውሃ ማቅረብ

ረቡዕ ፣18 ጁን 2025
Person holding a vial of water against a freshwater pH color chart to test the water.
አንድ ግለሰብ ውኃ ለመመርመር ውኃ የያዘ ብልቃጥ የመጠጥ ውኃ pH የቀለም ሠንጠርዥ ላይ አስደግፈው ይዘው።
" ምርት እንደምናመርት ነው የሚቆጠረው፤ እና Cambridge ውስጥ ጥሩ ጣዕም እንዲኖረው እንፈልጋለን — Julie Greenwood-Torelli፣ የውኃ ሥራዎች ዳይሬክተር "
Cambridge ውስጥ ቧንቧዎን ሲከፍቱ በሀገሪቷ ከፍተኛ የሚባሉትን የጥራት ደረጃዎች የሚያሟላ ውኃ ያገኛሉ። ውኃው ንጹሕ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጣፋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ቀላል ሥራ አይደለም፤ በከተማ አስተዳደሩ Water Department (የውኃ መምሪያ) የሚከናወን ዕለታዊ ጥረት፣ የማያቋርጥ ምርመራ እና ጠንቃቃ ክትትል ይጠይቃል።

United States ውስጥ የውኃ ጥራት ስታንዳርዶች በጥብቅ የፌደራል እና የስቴት ደንቦች ይተዳደራሉ። Environmental Protection Agency (የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ፣ EPA) ውኃ ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረታት እና የሰው ልጅ ጤንነትን ለመጠበቅ እንዲሁም የመጠጥ ውኃ ለሁሉም ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ብሔራዊ መስፈርቶችን ያስቀምጣል። Massachusettsን ጨምሮ ስቴቶች የራሳቸውን ስታንዳርዶች ማውጣት ወይም ለአካባቢያዊ ሁኔታዎች ለማመቻቸት የEPAን ምክረ ሃሳቦች ማሻሻልም ይችላሉ። የEPA የWater Quality Standards መመሪያ መጽሐፍ ለክልሎች፣ ጎሳዎች እና የውኃ ሥርዓቶች እነዚህን ስታንዳርዶች ለመገምገም፣ ለማዳበር እና ተግባራዊ ለማድረግ ዋነኛ መመሪያ ሆኖ ያገለግላል።

የመጠጥ ውኃን የሚጠብቀው አንዱ ዋነኛ ሕግ መጀመሪያ በ1974 በኮን
ግረስ የጸደቀው እና በ1986 እና 1996 የተሻሻለው Safe Drinking Water አዋጅ (SDWA) ነው። SDWA ከተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ በካዮች ለመከላከል ጤናን መሠረት ያደረጉ የመጠጥ ውኃ ስታንዳርዶችን እንዲያስቀምጥ ለEPA ሥልጣን ይሠጣል። ቀጣይነት ያለው ተገዢነትን ለማረጋገጥ በEPA፣ ስቴቶች እና የውኃ ሥርዓቶች መካከል የትብብር ጥረት እንዲኖርም ያስገድዳል። ነገር ግን በቁጥር ከ25 ያነሱ ሰዎችን የሚያገለግሉ የግል የውኃ ጉድጓዶች በSDWA ሥር ቁጥጥር አይደረግባቸውም።

Cambridge ውስጥ የውኃ ጥራትን ማረጋገጥ መሠረታዊ ስታንዳርዶችን ከማሟላት ባሻገር ይሄዳል፤ ዓላማው ከሚጠበቀው በላይ የላቀ መሆን ነው። "ምርት እንደምናመርት ነው የሚቆጠረው፤ እና Cambridge ውስጥ ጥሩ ጣዕም እንዲኖረው እንፈልጋለን" ሲሉ የውኃ ሥራዎች ዳይሬክተር Julie Greenwood-Torelli ይናገራሉ።

የCambridge Water Department በየሳምንቱ በመላው ከተማ ከሚገኙ በርካታ ቦታዎች የተወሰዱ ናሙናዎችን ይመረምራል። የpH ደረጃዎች፣ ቀለም፣ ባክቴሪያ እና ሌሎች ነገሮችንም ይፈትሻሉ። አጠቃላይ የኦርጋኒክ ካርቦን ይዘት (TOC) በየወሩ ይመረመራል። ከእነዚህ መደበኛ ፍተሻዎች ባሻገር Cambridge እዳዲስ የሚመጡ በካዮችን ቀድሞ ለመመርመር ቅድሚያ በመስጠት የነዋሪዎች ጤና በአዲስ መልክ ከተለዩ ስጋቶችም ቢሆን የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል።

ለጤንነት በሚፈጥሩት ስጋት በ2020 አካባቢ ሰፊ ትኩረት ማግኘት የጀመሩት per- እና polyfluoroalkyl ንጥረ ነገሮች የተሰኙት PFAS ኬሚካሎች ዙሪያ Cambridge ያደረገው ክትትል ለዚህ አርቆ አሳቢ አቀራረብ አንደ ምሳሌ ይጠቀሳል። Cambridge ግን ከ2019 ጀምሮ PFAS ለማግኘት ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል። "ከመጠን በላይ ናሙና ልንወስድ እና ወጪውም ትንሽ ከፍ ሊል የሚችል ቢሆንም፣ እነዚህን አዲስ መጪ በካዮች ቀደም ብሎ ለመለየት ስለሚያስችል ከንቱ ጥረት አይደለም" ሲሉ Greenwood-Torelli ያብራራሉ።

የውኃ ናሙና ላይ አደገኛ የሆነ የብክለት ደረጃ ከታየ Water Department ወዲያውኑ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው። ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንደ ውኃ እንዲፈላ ትዕዛዝ ያሉ የሕዝብ ጤና ምክሮችን ያስተላልፋሉ። በMassachusetts Department of Environmental Protection (የMassachusetts የአካባቢ ጥበቃ መምሪያ፣ MassDEP) የሚሰጡት መሰል ማስጠንቀቂያዎች ነዋሪዎች የቧንቧ ውኃ ከመጠጣታቸው በፊት ጎጂ ተሕዋሲያንን ለማጥፋት ውኃውን እንዲያፈሉ ያስገድዳሉ።

ነዋሪዎች እንደ የእርሳስ ወይም የመዳብ ብክለት ያሉ ነገሮችን ከተጠራጠሩም የWater Departmentን እንዲያነጋግሩ ጥሪ ይቀርብላቸዋል። በእነዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ ችግሩን ለመመርመር እና ለመፍታት መምሪያው ፈጣን እርምጃ ይወስዳል።

የውኃ ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በመምሪያው ጥቅም ላይ የሚውል ማንኛውም መሣሪያ ወይም ቴክኖሎጂ መጀመሪያ ከስቴቱ ፈቃድ እና እውቅና ማግኘት አለበት። በምርመራ የሚገኙ መረጃዎች እና መዝገቦች በኤሌክትሮኒክ መንገዶች የሚተዳደሩ ሲሆን፣ ይህም መረጃን ለመከታተል፣ ለማግኘት እና ለማረጋገጥ ከተለመዱ የወረቀት መዝገቦች አንፃር ቀለል ያለ ሂደት እንደሚፈጥር Greenwood-Torelli ይናገራሉ።

የኤሌክትሮኒክስ ሥርዓቶች አጠቃቀም መምሪያው በጊዜ ሂደት የሚታዩ አዝማሚያዎችን በተሻለ መልኩ መተንተን፣ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ቀደም ብሎ መለየት እና ሁሉም የቁጥጥር ሪፖርት አደራረግ መስፈርቶች ያለ ስህተት የሚሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሚችልበት ሁኔታ ይፈጥራሉ።

የCambridgeን የላቀ የውኃ ጥራት ማስጠበቅ የውስጣዊ ትጋት ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ከሰፊው ሕዝብ ጋር የሚደረግ ተሳትፎንም ያካትታል። Water Department ለትምህርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በየወሩ የመጀመሪያው ሳምንት ላይ በውኃ ማጣሪያ ጣቢያ እና ላብራቶሪው የሚደረጉ ነፃ ጉብኝቶችን ያቀርባል። እነዚህ ጉብኝቶች ላይ ነዋሪዎች፣ ተማሪዎች እና የማኅበረሰብ ቡድኖች የCambridge የመጠጥ ውኃ የሚጣራበት እና ክትትል የሚደረግበት መንገድ ዙሪያ ከመጋረጃ ጀርባ የሚሠራውን ሥራ ይመለከታሉ። ጉብኝቶቹ ቀጣዩን የአካባቢ እና የሕዝብ ጤና ጥበቃ ባለሙያዎች ትውልድ ለማነሳሳትም ይረዳሉ።

ከሕዝብ ትምህርት በተጨማሪ የመምሪያው ሠራተኞች የሙያ ፈቃዳቸውን ይዘው ለመቀጠል በየዓመቱ የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። ለሙያዊ እድገት የሚሰጠው ይህ ትኩረት ሠራተኞች በአዳዲስ የውኃ ደኅንነት ልምዶች፣ ቴክኖሎጂዎች እና የቁጥጥር መስፈርቶች ዙሪያ ወቅታዊ ግንዛቤ ያላቸው መሆናቸውን ያረጋግጣል።

የCambridge Water Department በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የሚገኘውን ውኃ መመርመር ለሚፈልጉ ነዋሪዎች የምርመራ ጥቅሎችን በነፃ ያቀርባል። ጥቅሎቹን በመምሪያው የራስ አገልግሎት ዴስክ መውሰድ የሚቻል ሲሆን፣ በመጠጥ ውኃ ዙሪያ እጅግ አሳሳቢ የሆኑትን ሁለት ንጥረ ነገሮች ማለትም እርሳስ እና መዳብን ለመመርመር የተቀረጹ ናቸው። እያንዳንዱ ጥቅል ናሙናዎችን ለመውሰድ እና ገቢ ለማድረግ ከሚረዱ በቀላሉ ሊከተሉ የሚችሏቸው መመሪያዎች ጋር የሚያገናኝ QR ኮድ ይኖረዋል።

ነዋሪዎች ሪፖርት ከሚያደርጓቸው እጅግ የተለመዱ ችግሮች መካከል ጣዕም እና ሽታ ይጠቀሳሉ። በውኃዎ ላይ ያልተለመደ ነገር ካስተዋሉ እርዳታ ለማግኘት በ617-349-4780 ወደ የWater Department ላብራቶሪ እንዲደውሉ ይበረታታሉ።

ግልጽነት የCambridge’s Water Department ቁልፍ እሴት ነው። መምሪያው በየዓመቱ ዓመታዊ የውኃ ጥራት ሪፖርት የሚያሳትም ሲሆን፣ ይህም የከተማዋ የመጠጥ ውኃ ጥራት፣ የምርመራ ውጤቶች እና ማንኛቸውንም ጥሰቶች ወይም አስፈላጊ ማስተካከያ እርምጃዎች በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ያቀርባል።

ለሕዝብ መረጃ የመስጠትን አስፈላጊነት በመገንዘብ መምሪያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተጨማሪ ድግግሞሽ ለመወያየት የሚያደርገውን ጥረት ጨምሯል። ከዚህ ዓመት ጀምሮ Water Department በየዓመቱ ሁለት ሪፖርቶችን ያሳትማል፤አንዱ ጁላይ ወር ላይ እና ሌላኛው ዲሴምበር ወር ላይ። እነዚህ ሪፖርቶች ነዋሪዎች የCambridge የውኃ ጥራት እና ብቅ እያሉ ያሉ ማንኛቸውም ችግሮች ዙሪያ ወቅታዊ መረጃ ያላቸው መሆኑን ያረጋግጣሉ።

ከምንም በላይ የCambridge Water Department ተልዕኮውን ለማሳካት በቁርጠኝነት ይሠራል፦ ለሁሉም ነዋሪ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ንጹሕ እና ጥሩ ጣዕም ያለው ውኃ ማቅረብ። ለምርመራ ያላቸው አርቆ አሳቢ አቀራረብ፣ ለሚፈጠሩ ችግሮች የሚሰጡት ፈጣን ምላሽ፣ በቴክኖሎጂ ላይ የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት፣ ለሕዝብ ትምህርት ያላቸው ትኩረት እና በየጊዜው የሚደረጉት ሪፖርቶች ለሕዝብ ጤና ያላቸውን ጥልቅ ቁርጠኝነት ያሳያል።
A gloved hand holding a clear beaker filled with water in a laboratory setting with scientific equipment in the background.
በላብራቶሪ ክፍል ሳይንሳዊ መሣሪያዎች የሚታዩበት ዳራ መካከል ውስጡ በግልጽ የሚታይ በውኃ የተሞላ ብርጭቆ የያዘ ጓንት የለበሰ እጅ።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here