U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

Bridge to College፦ ወደ የከፍተኛ ትምህርት ስኬት የሚያመራ መንገድ

ረቡዕ ፣18 ጁን 2025
Close-up of multiple graduation caps with orange tassels during an outdoor ceremony.
ከቤት ውጪ የሚደረግ ሥነ-ሥርዓት ላይ ብርቱካናማ ቀለም መነሳንስ ያላቸውን በርካታ የምርቃት ኮፍያዎች የሚያሳይ።
Bridge to College ፕሮግራም የኮሌጅ እና ከፍተኛ ትምህርት የመከታተል ፍላጎት ላላቸው ሰዎች የኮሌጅ ክሬዲት ማግኘት የሚችሉበት እና በኮሌጅ ደረጃ ላሉ የትምህርት ሥራዎች የሚዘጋጁበት ነፃ ዕድል ያቀርባል። ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች የማንበብ፣ የመጻፍ እና የሂሳብ ክህሎቶቻቸውን እንዲያሳድጉ እና በተመሳሳይ ሰዓት አስፈላጊ የኮምፒውተር እና የጥናት ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ተማሪዎች በዚህ ፕሮግራም ውስጥ በመሳተፍ በከፍተኛ ትምህርት እና ከዚያም ባሻገር ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጓቸውን መሳሪያዎች ያገኛሉ።

ተማሪዎች Bridge to College ፕሮግራም ውስጥ ለመሳተፍ አንዳንድ የብቁነት መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል። ተሳታፊዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ዲፕሎማ ወይም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጋር የሚመጣጠን ዲግሪ ያላቸው፣ ከፍተኛ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃት ያላቸው እና ከሴፕቴምበር እስከ ጁን ወር ባለው ጊዜ ውስጥ በመደበኛነት የማታ ትምህርት ለመከታተል ቁርጠኝነት ያላቸው መሆን አለባቸው። ይህ ፕሮግራም ለCambridge ነዋሪዎች እና በአቅራቢያው የሚገኙ የተመረጡ ከተማዎች ውስጥ ላሉ ግለሰቦች ክፍት ነው።

የትምህርት ክፍሎች በየሳምንቱ ሰኞ እና እሮብ ከ6:15 እስከ 9:15 ፒ.ኤም ድረስ በአካል እና ኦንላይን ይዘቶችን በመጠቀም ይሰጣሉ። ከትምህርት ሥራው ጥብቅ ተፈጥሮ አንፃር በየጊዜው አምስት አንቀጾች የያዙ ጽሑፎችን እንዲጽፉ የሚጠየቁ በመሆኑ ተማሪዎች ጠንካራ የእንግሊዘኛ ሰዋሰው እና የቃላት አጠቃቀም ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል። ተማሪዎች መስመር እንዳይስቱ እና ስኬታማ እንዲሆኑ ለመርዳት ፕሮግራሙ አነስተኛ የትምህርት ክፍሎች፣ ለግለሰብ የተቀረጸ የአስጠኚ ድጋፍ እና ትምህርታዊ እና ሙያዊ የምክር አገልግሎቶችን ያካትታል።

የBridge to College ፕሮግራም በ2025 ስፕሪንግ ወቅት ለ2025-26 የተማሪዎች ቡድን ምልመላ ማድረግ ይጀምራል። የመቀላቀል ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች መጀመሪያ ፕሮግራሙ ለእነሱ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለማየት የመረጃ ክፍለ ጊዜ መታደም አለባቸው። ከክፍለ ጊዜው በኋላ ብቁነታቸውን ለማረጋገጥ በሒሳብ፣ ማንበብ እና መጻፍ ዙሪያ ፈተናዎች ይወስዳሉ። በተጨማሪም ከCommunity Learning Center (የማኅበረሰብ ትምህርት ማዕከል፣ CLC) የፕሮግራም ሠራተኞች ጋር ቃለ መጠይቅ ማድረግ ያስፈልጋል። አመልካቾች ተቀባይነት ማግኘት ወይም አለማግኘታቸውን እስከ ኦገስት ወር አጋማሽ ድረስ ይነገራቸዋል።

አንድ ተማሪ ቀድሞውኑ በሌላ ሀገር ዲግሪያቸውን ያገኙ ከሆነ ድጋሚ ዩኒቨርሲቲ መግባት ላያስፈልጋቸው ይችላል። ዲግሪያቸው U.S. ውስጥ የሚኖረው አንፃራዊ ተቀባይነት ዙሪያ እርግጠኛ ያልሆኑ ሰዎች የምስክር ወረቀቶቻቸው በምን ደረጃ ተቀባይነት አላቸው የሚለውን ለማወቅ በነፃ የሚቀርበውን ኦንላይን የዲግሪ ማነጻጸሪያ መሣሪያ መጠቀም ይችላሉ።

The Community Learning Center (CLC) ከCLC እና መሰል የትምህርት ዳራዎች ወደ ኮሌጅ የሚሸጋገሩ ተማሪዎችን ለመደገፍ በ1998 Bridge to College ፕሮግራምን አቋቋመ። በርካታ ተሳታፊዎች የU.S.ን የትምህርት ሥርዓት የማያውቁ ስደተኞች ናቸው እና ይህ ፕሮግራም በኮሌጅ ደረጃ ለሚኖረው የትምህርት ሥራ ጠቃሚ ልምድ ያቀርብላቸዋል።

የBridge to College አማካሪ የሆኑት Ava Kiem ለሁለት ዓመታት ያህል ከፕሮግራሙ ጋር የሠሩ ሲሆን፣ ተማሪዎችን ወደ ኮሌጅ በሚያደርጉት ሽግግር በመምራት ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። ለBunker Hill Community College (BHCC) እንዲያመለክቱ እና ለትምህርት ክፍሎች እንዲመዘገቡ የሚረዷቸው ሲሆን፣ በተመሳሳይ ሰዓት እድገታቸውን ለማረጋገጥ ወርሃዊ ክትትሎች ያደርጋሉ። ፕሮግራሙ ከBHCC ጋር የተያያዘ ነው፤ ተማሪዎችም Bridge ፕሮግራምን ካጠናቀቁ በኋላ እዚያ የትምህርት ክፍሎች መውሰድ የሚችሉ ቢሆንም፣ የትምህርት ክፍያውን ግን በራሳቸው የመሸፈን ኃላፊነት ይኖርባቸዋል።

የBridge to College ፕሮግራም ቁልፍ አካል ጠንካራ የድጋፍ ሥርዓቱ ነው። ተማሪዎች ወደ ኮሌጅ የሚደረገውን ሽግግር በተሳካ ሁኔታ ማለፍ ከቻሉ የቀድሞ የBridge ተማሪዎች በነፃ የሚቀርቡ የአስጠኚ አገልግሎቶች እና መካሪ ማግኘት ይችላሉ። በርካታ ተሳታፊዎች የሥራ እና የቤተሰብ ኃላፊነቶች ያሉባቸው አዋቂ ተማሪዎች እንደመሆናቸው መጠን የትምህርት እና የሕይወት ግዴታዎችን በአንድ ላይ ማስኬድ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ፕሮግራሙ እነዚህን እንቅፋቶች ለማሸነፍ ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማቅረብ የተቀረጸ ነው።

እንደ Kiem ገለጻ፣ ፕሮግራሙ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደር በራስ መተማመን እንዲገነቡ እና ምኞታቸውን በግልጽ ማብራራት እንዲችሉ ረድቷቸዋል። "ይህ ፕሮግራም በርካታ ተማሪዎች በራስ መተማመን እንዲያገኙ ረድቷል" ሲሉ Kiem አጋርተዋል። አሁን እነዚህ ተማሪዎች ስለ ተስፋዎቸው እና ህልሞቻቸው መናገር እና እውን ለማድረግ መሥራት ይችላሉ።

የBridge to College ፕሮግራም የተማሪ ስኬት ታሪኮችን አጉልቶ የሚያሳይ የዜና መጽሔትም የሚያቀርብ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች ግቦቻቸውን ለማሳካት እንዲጥሩ ተጨማሪ ተነሳሽነት ይሰጣል። ብዙዎቹ ተማሪዎች እና በተለይም ስደተኞች ይህን ፕሮግራም ትምህርታዊ እና ሙያዊ ምኞቶቻቸውን ለማሳካት አስፈላጊ መሠረት አድርገው ይመለከቱታል።

Kiem በተስፋፋ ተደራሽነት እና ተጨማሪ ግንዛቤ ማስጨበጫዎች ፕሮግራሙ ሲያድግ እና አሁንም ይበልጥ ተማሪዎች ስኬታማ መሆን እንዲችሉ ለመርዳት ተጨማሪ ግብዓቶች ሲያገኝ የማየት ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። "ግቦቻቸውን እና መከተል የሚፈልጉትን የሙያ ዘርፍ ማለም የሚጀምሩ ሲሆን፣ ይህም ለብዙ ሰዎች ተስፋ ይሰጣል" ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይ የገንዘብ ችግሮች ስጋት በሚሆኑበት ጊዜ ከፍተኛ ትምህርት መከታተል አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ለግላዊ እና ለሙያዊ እድገት ወሳኝ እርምጃ ነው። እንደ Bridge to College ያሉ ፕሮግራሞች ተማሪዎች በትምህርት ሥርዓቱ ለማለፍ እና የረዥም ጊዜ ግቦቻቸውን ለማሳካት አስፈላጊ የሆኑትን ክህሎቶች እና በራስ መተማመን እንዲያዳብሩ ይረዳሉ። ፕሮግራሙ ደጋፊ እና መዋቅራዊ የሆነ የትምህርት አካባቢ በማቅረብ የወደፊት ሕይወታቸውን መቆጣጠር እና ከከፍተኛ ትምህርት ጋር የሚመጡ ዕድሎችን ተቀብለው መጠቀም እንዲችሉ ተማሪዎችን ያጎለብታል።

https://www.cambridgema.gov/DHSP/programsforadults/communitylearningcenter/bridgetocollege ላይ ስለ Bridge to College የበለጠ ይወቁ።
" ግቦቻቸውን እና መከተል የሚፈልጉትን የሙያ ዘርፍ ማለም የሚጀምሩ ሲሆን፣ ይህም ለብዙ ሰዎች ተስፋ ይሰጣል። — Ava Kiem፣ የBridge to College አማካሪ "
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here