ምግብ ነክ ቆሻሻን ወደ ንጹሕ የኃይል ምንጭ ይለውጡ
ረቡዕ ፣18 ጁን 2025
Cambridge ለአስርት ዓመታት ብስባሽ በማዳበር መሪ ሆኖ ቆይቷል። ከተማ አስተዳደሩ በዚህ ረገድ ሥራ የጀመረው በ1950 ሲሆን፣ ያኔ የምግብ ትርፍራፊዎች ተሰብስበው ዓሳማዎችን እንዲመግቡ ወደ ቆሻሻ መጣያዎች ይላኩ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የCambridge ብስባሽ የማዳበር ፕሮግራም በአካባቢው እጅግ በጣም ዘመናዊ እና ለአካባቢ ተስማሚ ከሚባሉት ተነሳሽነቶች መካከል አንዱ መሆን ችሏል።
ዛሬ Department of Public Works (የሕዝብ ሥራዎች መምሪያ፣ DPW) በየሳምንቱ ወደ 45 ቶን ምግብ ነክ ቆሻሻ ይሰበስባል። ተፅዕኖው ዝምብሎ ቆሻሻን ከመቀነስ ባሻገር ይሄዳል፦ ብስባሽ ማዳበር የከተማ አስተዳደሩን የአየር ንብረት ግቦች ይደግፋል፣ ወጪዎችን ይቀንሳል እንዲሁም በመኖሪያ ሰፈሮች ውስጥ የሚኖረውን የአይጥ እንቅስቃሴም ዝቅ ያደርጋል።
"ብስባሽ ማዳበር ለአካባቢው፣ ለነዋሪዎች እና ለንግድ ሥራዎች የጋራ ጥቅም ያስገኛል" ሲሉ የCambridge Department of Public Works ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ሥራ ዳይሬክተር Michael Orr ተናግረዋል።
ምግብ ነክ ብስባሾችን ማዳበር ለCambridge የአየር ንብረት ጥበቃ ጥረቶች ወሳኝ ሚና ይጫወታል። መጀመሪያ ምግብ ነክ ቆሻሻው ተለይቶ ይወጣ እና እንደ ፕላስቲኮች ወይም የማይበሰብሱ ቁሳቁሶች ያሉ የማይፈለጉ ነገሮች ይወገዳሉ። በመቀጠል የጸዳው ምግብ ነክ ቆሻሻ ከፍሳሽ ቆሻሻዎች ጋር ተደባልቆ ብስባሽ ማዳበሪያ ውስጥ ይጨመራል። ብስባሽ ማዳበሪያው ውስጥ የሚገኙት ተፈጥሯዊ ባክቴያዎች ካርቦናማ ቁሳቁሶቹን ተመግበው ሚቴን ጋዝ ያመነጫሉ። ይህ ሚቴን ወደ ከባቢ አየር እንዲያመልጥ ከመፍቀድ ይልቅ የከተማ አስተዳደሩ ይይዘው እና ንጹሕ ኃይል ለማመንጨት ይጠቀምበታል።
ብስባሽ ማዳበሪያው ውስጥ ያለው ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ የሚቀረው ጠጣር ቁሳቁስም አይባክንም፤ አብዛኛውን ጊዜ በንጥረ ነገሮች ወደበለጸገ የአትክልት ማዳበሪያ ይቀየራል። ይህ የዝግ ዑደት ሥርዓት ከከርሰ ምድር የሚወጡ የማይታደሱ (ፎሲል) ነዳጆች ላይ የማይተማመን ሲሆን፣ ምግብ ነክ ቆሻሻዎች ለአካባቢ ብክለት የሚያበረክቱትን አስተዋጽዖ በመቀነስ Cambridge ለወደፊቱ ይበልጥ ለአካባቢ ተስማሚ የሆነች ከተማ እንድትሆን ይረዳል።
ብስባሽን በማዳበር የሚገኘው ሌላ ከፍተኛ ጥቅም ለሕዝብ ጤንነት የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ነው። ምግብ ነክ ቆሻሻዎች ተለይተው በአግባቡ ሲወገዱ በመደበኛ ቆሻሻ መጣያ በርሜሎች ውስጥ የሚኖረውን የምግብ ቁሳቁስ ይቀንሳል። ይህ ደግሞ ወደ የመኖሪያ ቤት እና የንግድ ቤት ቆሻሻ መጣያዎች ሊሳቡ የሚችሉትን አይጦች ይቀንሳል።
በተጨማሪም ብስባሽ ማዳበር ወጪ ቆጣቢ ነው። ምግብ ነክ ቆሻሻዎችን ከመደበኛ ቆሻሻ መጣያ በርሜሎች ማስወገድ የቆሻሻ መጣያ ወጪዎችን የሚቀንስ ሲሆን፣ ለከተማ አስተዳደሩ እና ለተሳትፊ የንግድ ሥራዎች ገንዘብ ይቆጥባል። ስኬታማነቱ እያደገ የሚገኘው የCambridge ብስባሽ የማዳበር ፕሮግራም ወደ ሁሉም የCambridge Public Schools፣ በርካታ አካባቢያዊ ነፃ ምግብ ማከፋፈያዎች እና ወደ 80 እስከ 90 የሚሆኑ የንግድ ሥራዎች ተስፋፍቷል።
“ገንዘብ ይቆጥባል እና አካባቢን ለመጠበቅ ይረዳል፤ ስለዚህ ለሁሉም የጋራ ጠቀሜታ ያስገኛል” ሲሉ Orr ያብራራሉ።
Cambridge ውስጥ ብስባሽ ማዳበር ለመጀመር ቀላል እና ከክፍያ ነፃ ነው። ነዋሪዎች ሊበሰብሱ ከሚችሉ የቆሻሻ ፌስታሎች እና ምግብ ነክ ቆሻሻ እንዴት እንደሚለይ የሚያብራሩ ግልጽ መመሪያዎች ጋር የሚመጣውን በነፃ የሚቀርብ የኩሽና ብስባሽ መጣያ ባልዲ ለማዘዝ በ147 Hampshire Street የሚገኘውን Department of Public Works መጎብኘት ወይም ወደ DPW ድር-ጣቢያ መግባት ይችላሉ።
የሚኖሩበት ህንፃ የከተማ አስተዳደሩ በመንገድ ዳር ብስባሽ ማዳበሪያ ፕሮግራም ውስጥ መሳተፍ አለመሳተፉን እርግጠኛ ካልሆኑ አከራይዎን መጠየቅ ወይም DPWን ማነጋገር ይችላሉ። የከተማ አስተዳደሩ የብስባሽ ማዳበሪያ ተደራሽነትን ለማስፋት በሚል አከራዮች እና ንብረት አስተዳዳሪዎችን ለማነጋገርም ፈቃደኛ ነው።
ብዙ ሰዎች የማይገነዘቡት ነገር ተቀባይነት ያላቸውን ዕቃዎች ብዛት ነው። የCambridge ፕሮግራም የበሰበሰ ምግብን ጨምሮ እንደ የወተት ተዋጽዖዎች፣ ስጋ፣ የሻይ ቅጠል፣ የወረቀት ፎጣዎች (በላያቸው ላይ ምግብ ካለ) እና የተፈጩ አበባዎችም ጭምር ያሉ ሁሉንም ዓይነት ምግብ ነክ ቆሻሻዎች ይቀበላል። ይህ የተቀባይነት ያላቸው ቁሳቁሶች ብዛት ሁሉም ነዋሪ እንዲሳተፍ እና ትልቅ አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ።
የCambridge ብስባሽ የማዳበር ጥረቶች በፍጥነት እያደጉ ሲሆን፣ የከተማ አስተዳደሩም ለወደፊት ሰፊ ዕቅዶች ይዟል። DPW በሚቀጥለው ዓመት ውስጥ ብስባሽ ማዳበርን ለሁሉም የCambridge ነዋሪዎች አስገዳጅ ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው። ይህ እርምጃ ብስባሽ ማዳበር የሚያስገኛቸው የአካባቢ ጥበቃ ጠቀሜታዎች ለማሳደግ የሚረዳ ሲሆን፣ የዜሮ-ቆሻሻ እና የአየር ንብረት እርምጃ ግቦቹን በመምታት ረገድ የከተማ አስተዳደሩን ወደፊት ያራምዳሉ።
Cambridge ለነዋሪዎቹ እና የንግድ ሥራዎቹ ብስባሽ ማዳበርን የዕለተ ዕለት ተግባር አድርጎ የትናንትናን ትራፊዎች ወደ የነገ ንጹሕ የኃይል ምንጭ በመለወጥ እና ይበልጥ ጤናማ፣ ለአካባቢ ተስማሚ ማኅበረሰብ በመፍጠር ተምሳሌት ሆኖ እየመራ ይገኛል።
ከከተማ አስተዳደሩ በመንገድ ዳር ብስባሽ ማዳበሪያ ፕሮግራም ጋር በትብብር የመሥራት ፍላጎት ያላቸው የንግድ ሥራዎች የበለጠ ለማወቅ ወደ recycle@cambridgema.gov ኢሜይል መላክ ይችላሉ።
"
ገንዘብ ይቆጥባል እና አካባቢን ለመጠበቅ ይረዳል፤ ስለዚህ ለሁሉም የጋራ ጠቀሜታ ያስገኛል። — Michael Orr፣ የCambridge Department of Public Works ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ሥራ ዳይሬክተር
"