ባለፉት ጥቂት አመታት እየሞቀ የመጣው የአየር ሁኔታ New England ውስጥ ቀለል ያሉ የዊንተር ወቅቶችን አስከትሏል። በቅርብ ያለፈው ግን ለተወሰነ ጊዜ ከታዩት የሙቀት ደረጃዎች በጣም የቀዘቀዘ በመሆን የድሮውን የሚያስታውስ ነበር። ያም የሙቀት ማመንጫ ዋጋዎች በመላው ስቴት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምሩ ከፊል አስተዋጽዖ አድርጓል። ቁጥራቸው እየጨመረ ያሉ ነዋሪዎች ወደላይ እየተተኮሱ የሚገኙ ወጪዎችን ለመቋቋም እርዳታ እየፈለጉ እንደመሆናቸው መጠን የCambridge ከተማ አስተዳደር ሒሳቦችን ለመረዳት፣ መኖሪያ ቤቶችን ይበልጥ ኃይል ቆጣቢ ለማድረግ እና የኃይል አቅርቦት ወጪዎችን ለመቀነስ አንድ ለአንድ የሚሰጥ እርዳታ በነፃ ማቅረብ በመቻሉ ኩራት ይሰማዋል።
ነዋሪዎች ወደሚከተለው ቁጥር መደወል ይችላሉ፦ Cambridge Energy Helpline፣ 617-430-6230። የሚደውሉ ሰዎችን የከተማ አስተዳደሩ የሚያቀርባቸውን በርካታ የኃይል አቅርቦት ፕሮግራሞች ከሚያብራራ አማካሪ ጋር ያገናኛል።
"የCambridge Energy Helpline ለግለሰብ የተቀረጸ ድጋፍ እና ለእርስዎ ተስማሚ የሆኑ ፕሮግራሞችን ለማግኘት ቀላል የሆነ መንገድ ያቀርባል" ሲሉ የCambridge ከተማ አስተዳደር የኃይል አቅርቦት ተሳትፎ ተባባሪ የዕቅድ አወጣጥ ባለሙያ Brad Pillen ተናግረዋል። "ቤት ተከራይም ሆኑ የቤት ባለቤት ወይም የሚኖሩበት ህንፃ ዓይነት ምንም ይሁን ምን የጋዝ ወይም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሒሳብ የሚከፍሉ ከሆነ ለእርስዎ የሚሆን ፕሮግራም አለ።"
የእገዛ የስልክ መስመሩ በCambridge Office of Sustainability (የCambridge የአካባቢ ተስማሚነት ጽሕፈት ቤት) የሚቀርብ እና በAll in Energy የሚደገፍ ሲሆን፣ ከ50 በላይ የMassachusetts ማኅበረሰቦች ውስጥ የሚሠራ ለትርፍ ያልተቋቋመ አገልግሎት ነው። ባለፈው ዓመት የእገዛ ስልክ መስመሩ አማካሪዎች በCambridge ውስጥ የስልክ ጥሪ ያደረጉ ከ100 በላይ ነዋሪዎችን ረድተዋል።
ከእነዚህ ነዋሪዎች ብዙዎቹ በገቢ ብቁ የሚኮንባቸው የቅናሽ ፕሮግራሞች ውስጥ ምዝገባን ለሚያረጋግጠው Energy Bill Checkups ያለምንም ክፍያ ተመዝግበዋል። ፍተሻዎቹ በ2017 ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለደንበኞች $36 ሚሊዮን መቆጠብ በቻለው Cambridge Community Electricity (CCE) ፕሮግራም ነዋሪዎች መመዝገባቸውን የሚያረጋግጡ ሲሆን፣ የከተማ አስተዳደሩ ግን ለወደፊት የወጪ ቅነሳዎች ማረጋገጫ ሊሰጥ አይችልም። ባለፈው ዓመት ነዋሪዎች በማንኛውም ሰዓት ሊቀላቀሉ የሚችሉትን Economy Green የተሰኘ ዝቅ ያለ ወጪ የሚያስወጣ አዲስ የCCE አማራጭ Cambridge አስተዋውቋል።
አማካሪዎች የማሞቂያ አገልግሎት ሒሳቦችን ለመክፈል እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ከFuel Assistance ፕሮግራም ጋር ያገናኛሉ። በተጨማሪም ደንበኞች በመገልገያ ሒሳቦቻቸው ክሬዲት ለማግኘት ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ለሚገኙ የፀሐይ ኃይል ሥርዓቶች በመመዝገብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ወጪዎቻቸውን እስከ 20% እንዲቀንሱ ከሚያስችለው Community Solar ጋር ነዋሪዎችን አገናኝተዋል።
የነጠላ ቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች፣ አፓርታማዎች ወይም ኮንዶሚኒየሞች ተከራዮች፣ ባለቤቶች እና አከራዮች መኖሪያ ቤትን ኃይል ቆጣቢ ማድረግ የሚቻልባቸው ቴክኒኮችን ጨምሮ ኃይል መቆጠቢያ መንገዶች ዙሪያ በነፃ የተበጀ ምክር ከሚያቀርበው Home Energy Assessments ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን መገልገያዎች እና ማሞቂያ እና ማቀዝቀዣ መሳሪያዎች መግጠም ለሚፈልጉ አካላት የከተማ አስተዳደሩ Electrify Cambridge ፕሮግራም እንዴት የመጀመሪያ ወጪዎችን መሸፈን እንደሚቻል ለመረዳት ነዋሪዎችን የሚያግዝ ሲሆን፣ የገንዘብ ድጋፍም ያቀርባል።
የCambridge የኃይል አቅርቦት ፕሮግራሞች ድርብ ዓላማዎችን ያሳካሉ፦ የቤተሰቡን ጤንነት እና ደኅንነት እያሻሻሉ በተመሳሳይ ሰዓት የምድርን ሙቀት የሚጨምሩ ግሪንሃውስ ጋዞችን ከሚፈጥሩት ከከርሰ ምድር የሚገኙ የማይታደሱ ነዳጆች ማኅበረሰቡን ያሸጋግራሉ። የከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪዎች ራሳቸውን እና ዓለምን መርዳት የሚችሉበት መሣሪያዎች በማቅረብ በሁሉም ቦታ ለሚገኝ ሁሉም ሰው የተሻለ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለማረጋገጥ ይሠራል።