U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

A rat peeks out from beneath a wooden structure.
በCambridge’s Rodent Control ፕሮግራም የአይጥ ችግሮችን ይከላከሉ
የCambridge ከተማ አስተዳደር Inspectional Services Department በPrivate Property Rodent Control ፕሮግራም አማካኝነት የቤት ውጪ የአይጥ ቁጥጥር አገልግሎቶችን በነፃ ያቀርባል። 2021 ላይ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ይህ ፕሮግራም የባለሙያ ፍተሻዎች፣ መፍትሔዎች እና የክትትል ጉብኝቶች በማቅረብ ከ900 በላይ ብቁ የሆኑ መኖሪያ ንብረቶችን ረድቷል። ነዋሪዎችም ውጤታማ የአይጥ መከላከል ዘዴዎች ላይም ትምህርት ያገኛሉ። መኖሪያ ሰፈሩን ከአይጥ የጸዳ ለማድረግ የንፅሕና አጠባበቅ እና የጋራ ኃላፊነት ወሳኝ እንደመሆናቸው መጠን የከተማ አስተዳደሩ ማኅበረሰብ አቀፍ ተሳትፎን ያበረታታል።
Close-up of multiple graduation caps with orange tassels during an outdoor ceremony.
Bridge to College፦ ወደ የከፍተኛ ትምህርት ስኬት የሚያመራ መንገድ
በCambridge Community Learning Center የሚተዳደረው Bridge to College ፕሮግራም በማንበብ፣ መጻፍ፣ ሒሳብ እና የማጥናት ክህሎቶች ዙሪያ የማታ ትምህርት ክፍሎችን በነፃ በማቅረብ አዋቂዎችን ለኮሌጅ እንዲዘጋጁ ይረዳል። ለCambridge ነዋሪዎች እና በአቅራቢያው ለሚገኙ የተመረጡ ማኅበረሰቦች ክፍት የሆነው ፕሮግራም ተማሪዎችን እና በተለይም ስደተኛ እና አዋቂ ተማሪዎችን በከፍተኛ ትምህርት ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈሉትን ክህሎቶች እና በራስ መተማመን እንዲያዳብሩ ይረዳል።
A safety officer carefully inspects a child safety car seat to ensure it is properly installed in the vehicle.
በነፃ በሚቀርቡ ፍተሻዎች እና የመግጠም ሥራዎች ቀላል የተደረገ የልጅ የመኪና መቀመጫ ደኅንነት
የልጅ የመኪና መቀመጫዎች፣ ልጁን ከፍ የሚያደርጉ የመኪና መቀመጫዎች እና የደኅንነት ቀበቶዎችን ነዋሪዎች በአግባቡ እንዲገጥሙ ለመርዳት የልጅ የደኅንነት መቀመጫ ገጠማ እና ፍተሻ አገልግሎት በነፃ ያቀርባል። ሁሉም ልጆች ደኅንነታቸው በተጠበቀ እና የMassachusetts ሕግን ባከበረ መልኩ እየተጓዙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሠለጠኑ መኮንኖች መቀመጫዎችን ይፈትሻሉ፣ መመሪያ ይሰጣሉ እና ለተቸገሩ ቤተሰቦችም የልጅ የመኪና መቀመጫዎችን በነፃ ሊያቀርቡ ይችላሉ።
An open register book displaying a list of members with names and details written in cursive handwriting, set on a purple textured background.
የቤተሰብዎን ያለፈ ታሪክ ይወቁ፦ በCambridge Public Library የሚገኙ የዘር ሐረግ ግብዓቶች
የCambridge Public Library ለታሪካዊ መዝገቦች፣ የዘር ሐረግ መረጃ ቋቶች እና የባለሙያ መመሪያ ከክፍያ ነፃ የሆነ ተደራሽነት በመስጠት እንዴት የዘር ሐረግዎን እንዲያውቁ ሊረዳዎት እንደሚችል ይወቁ። ገና እየጀመሩ ወይም ጠለቅ ያለ ምርመራ እያደረጉ ቢሆንም፣ በአካባቢያዊ መዝገብ ቤቶች፣ የከተማ አስተዳደር የመረጃ ማውጫዎች እና የሕዝብ ቆጠራ መረጃዎች አማካኝነት ከታሪክዎ ጋር ግንኙነት ይፍጠሩ።
Profile Photo of Alyssa Pacy
የሠራተኛ መረጃ ማጠቃለያ፦ የማኅደረ አያያዝ ባለሙያዋ ለCambridge ታሪክ ሕይወት ሰጡ
ለቤተ መጻሕፍቱ የመጀመሪያ በሆነው የማኅደር ክፍል ውስጥ የሚሠሩት ባለሞያ የቤተ መጻሕፍቱን ማኅደር ሀ ብለው ከመጀመሪያው የማዘጋጀቱን ፈታኝ ሥራ ሲሠሩ ቆይተዋል።
Dr. James G. Barrett
የሠራተኛ መረጃ ማጠቃለያ፦ የሕክምና ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ሲሆኑ በAmerican Medical Association Network Open ጆርናል ላይም ጽሑፋቸው ታትሟል
Police Department ውስጥ እያገለገለ በሚገኝ አንድ ሐኪም የሚመሩ ተመራማሪዎች ታስረው በተፈቱ አዋቂዎች መካከል ያለውን የሞት ምጣኔ ከ10 ጥናቶች ካገኙት መረጃዎች አሰናድተው አቅርበዋል።
: Sergeant Lowe (center) and Officer Grassi (left) and Gutoski (right) patrol Harvard Square.
የሠራተኛ መረጃ ማጠቃለያ፦ የፖሊስ መኮንኖች በHarvard and Central Square ግንኙነቶችን እየገነቡ የሚገኙ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የCambridge Police ስትራቴጂ ትልቅ አካል ነው
Police Department ከንግድ ሥራዎች፣ ከነዋሪዎች እና ከማኅበራት ጋር በቅርበት በመሥራት፣ ችግሮችን ለመለየት እና ለመፍታት በከተማው አደባባዩች ላይ የፖሊስ መኮንኖችን ያሠማራል።
Public Works’ Environmental Engineer Diane Stokes stands in front of a construction site and one of her many projects.
የትራንስፖርት ተጠቃሚ እና የአካባቢ ጥበቃ መሐንዲስ ሲዋሃዱ፦ የPublic Works ሠራተኛ Diane Stokes ታሪክ
ከአካባቢ ትራንስፖርት ተጠቃሚነታቸው ባገኙት አመለካከት እና ሁለገብ በሆኑ ትላልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ባላቸው ልምድ ምክንያት ተመራጭ እጩ ስለሆኑት የCambridge የአካባቢ ጥበቃ መሐንዲስ Diane Stokes ተጨማሪ ይወቁ።
Active Transportation Coordinator for the Community Development Department, Tenzin Choephel, stands with a Bluebike in front of Broadway Bicycle School.
የCambridgeን Bluebikes እና Bike Education ፕሮግራሞች የሚመሩት የቀድሞ መምህር፦ የCommunity Development (የማኅበረሰብ ልማት) ሠራተኛ Tenzin Choephel ታሪክ
የBluebikes ሥራዎችን፣ ለCambridge ታዳጊዎች የሚሰጡ የብስክሌት ግንዛቤ ማስጨበጫዎችን እና የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ ለማቅረብ የሚገቡ ጽሑፎችን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን የሚሸፍን ሚና ስለሚጫወቱት የCommunity Development ሠራተኛ Tenzin Choephel ተጨማሪ ይወቁ።  
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here