U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ለከተማ አስተዳደሩ የካሳ ይገባኛል ጥያቄ ያቅርቡ

Law

በሚከተሉት የጽሑፍ ደብዳቤ ወይም ኢሜይል በመላክ የይገባኛል ጥያቄዎን ለCity Clerk’s office (የከተማ አስተዳደሩ ጸሐፊ ቢሮ) ማቅረብ ይችላሉ፦

Paula Crane, Acting City Clerk
City Clerk’s Office
795 Mass. Ave, 1st Floor
Cambridge, MA 02139
cityclerk@cambridgema.gov

 የይገባኛል ጥያቄው የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፦

  1. የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢው ስም፣ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር፤
  2. ክስተቱ የተፈጠረበት ቀን፣ ሰዓት እና ትክክለኛ ቦታ፤ እንዲሁም
  3. የክስተቱን መግለጫ።

 የይገባኛል ጥያቄው የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦

  1. ፎቶግራፎችን፤
  2. የጥገና ወጪ ግምቶችን ወይም የሒሳብ መግለጫዎችን።

ከመኪና መንገድ እና ከእግረኛ መንገድ ጉድለት ጋር የተያያዙ የካሳ ይገባኛል ጥያቄዎች ክስተቱ ከተፈጠረበት ዕለት አንስቶ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ መቅረብ እንዳለባቸው እና ሌሎች የካሳ ይገባኛል ጥያቄዎች ደግሞ በአጠቃላይ ክስተቱ ከተፈጠረበት ዕለት አንስቶ ባሉት 2 ዓመታት ውስጥ መቅረብ እንዳለባቸው ልብ ይበሉ።

የደረሰው የአካል ጉዳት እና/ወይም የንብረት ውድመት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚሠራ ሥራ ተቋራጭ (ኮንትራክተር) ከወሰዳቸው እርምጃዎች ጋር የተያያዘ ከሆነ፣ የካሳ ይገባኛል ጥያቄዎን ለሥራ ተቋራጩ ማቅረብ ይኖርብዎታል።

በቦታው ላይ ተሳታፊ የነበረ ሥራ ተቋራጭ ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን ካልቻሉ፣ የካሳ ይገባኛል ጥያቄውን ለከተማ አስተዳደሩ ማቅረብ ይችላሉ፤ ሆኖም ግን ጥያቄዎን ለሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርቡ ሊመሩ ይችላሉ።

የይገባኛል ጥያቄዎን ሁኔታ በተመለከተ ጥያቄዎች ካሉዎት የLaw Departmentን በ 617-349-4121 ደውለው ያነጋግሩ፤ ነገር ግን የይገባኛል ጥያቄዎን ሁኔታ የሚመለከት ጥያቄ ከማቅረብዎ በፊት ቢያንስ ከ6 እስከ 8 ሳምንታት መጠበቅ ይኖርብዎታል። Law Department የሚያከናውነውን ምርመራ ለማጠናቀቅ በቂ ጊዜ እንደሚያስፈልገው እና ምርመራውን ካጠናቀቀ በኋላም በጽሑፍ ለእርስዎ ምላሽ እንደሚሰጥ እባክዎ ይገንዘቡ።

ይህ የሕግ ምክር እንዲሆን የታሰበ ወይም በከተማ አስተዳደሩ ዘንድ ተጠያቂነት መኖሩን የሚያምን አይደለም። የከተማ አስተዳደሩ ይህንን መረጃ ሲያቀርብ በምንም መልኩ የገዛ መከላከያ ነጥቦቹን ወይም መብቶቹን ትቷል ማለት አይደለም፤ በተመሳሳይ ይህ መረጃ በአሁኑ ወቅት ከተማ አስተዳደሩ ያለውን ወይም ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ማንኛውም ተጨባጭ ወይም ሕጋዊ መከላከያ ለማስቀረት አይሠራም። ማንኛውም ከሕግ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ካለዎት እባክዎ ሕጋዊ ጠበቃ ያነጋግሩ።

እንዴት መጀመር እንደሚቻል ማሳያ

የይገባኛል ጥያቄው የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፦

  1. የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢው ስም፣ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር፤
  2. ክስተቱ የተፈጠረበት ቀን፣ ሰዓት እና ትክክለኛ ቦታ፤ እንዲሁም
  3. የክስተቱ መግለጫ
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here