U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ከከተማ አስተዳዳሪ የተላከ መልእክት

ሐሙስ ፣18 ኤፕሪል 2024

ውድ የCambridge ማህበረሰብ፣

ባለፈው ክረምት Cambridge የአለም የአየር ንብረት ለውጥን እንዴት እየፈታ እንደሆነ ለማጋራት ሙሉ ዜናመፅሄት ለዚሁ ታሳቢ አድርገናል። ዛሬ ይህን ዜናመፅሄት እየተጋፈጥን ላለነው የመኖሪያ ቤት ችግር ታሳቢ አድርገናል።

የመኖሪያ ቤት ወጪ መጨመር በከተማችን ውስጥ ላሉ ሰዎች ሁሉ፣ በአካባቢያችን ህይወትን ከሚገነቡ ወጣቶች ጀምሮ፣ እስከ ለህፃናት ተጨማሪ ቦታ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች እና ከቤተሰቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር ለመቀራረብ ለሚጥሩ አዛውንቶች ድረስ ሁሌም ያለ ወቅታዊ ፈተና ሆኗል። በ2023 የነዋሪዎች ዳሰሳ ጥናታችን፣ ከተማችን እየተገጠመው ያለው ብቸኛው በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ምንድነው ብለን ጠየቅን? 39% ያህላችሁ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት ብላቹሀል፣ ይህም ውጤት ከአመት አመት ተደጋግሟል። እና ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ዋጋ ቢወርድርም፣ ከ2020 ጀምሮ የቤት ኪራይ ከ10 በመቶ በላይ ጨምሯል እና በታላቋ ቦስተን ውስጥ ካሉት ከፍተኛዎቹ ውስጥ ገብቶ ቀርቷል። የሚያስደንቅ ማህበረሰብ አለን ነገር ግን በጣም ውድ፣ የማይደረስ እና ርትዓዊ ያልሆነ እየሆነ ነው።

አሁን የመኖሪያ ቤት ችግር ቀውስ ለመሆኑ ሰፊ እውቅና አግኝቷል። ፕሬዘዳንት ባይደን የመኖሪያ ቤት ከፍተኛ ወጪ መላ ሊባል እንደሚገባ እና ስለ "መገንባት፣ መገንባት፣ መገንባት" አስፈላጊነት በተመለከተ በየጊዜው ይናገራሉ። ገዢ ሄሊ መኖሪያ ቤት ለአስተዳደሯ ቁጥር አንድ ችግር እንደሆነ በቀላሉ ገልጻለች። Cambridge እነዚህን ትላልቅ ጥረቶች በመደገፍ ላይ በንቃት እየሰራ ቆይቷል። የከተማው ምክር ቤት የአካባቢያዊ ዝውውር ክፍያ አማራጭን የሚደግፉ በርካታ የፖሊሲ ትዕዛዞችን አሳልፏል እና ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ለመደገፍ በስቴት ሀውስ ብዙ ጊዜ ለከንቲባው የተመጣጣኝ ቤቶች አዋጅን በመደገፍ ቃሌን ሰጥቼያለው፣ ይህም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት የሚሰጥ እና የአካባቢያችንን ጥረት የሚደግፉ ቁልፍ የፖሊሲ ለውጦችን የሚሰጥ ነው። የመኖሪያ ቤቶች ችግሮችን ብቻችንን መፍታት አንችልም እና አዳዲስ የፖሊሲ መፍትሄዎችን ለማምጣት ከክልላችን ልዑካን ጋር በቅርበት መስራታችንን እንቀጥላለን።

Cambridgeም መሪ ሆኖ በከተማ ደረጃ ጠቃሚ እርምጃዎችን ወስዷል። የከተማው ምክር ቤት በግዛቱ ውስጥ አንዳንድ በጣም ተራማጅ የሆኑ የቤቶች ፖሊሲዎችን አሳልፏል፣ ከእነዚህም ውስጥ እንደ ጥቅጥቅ ጉርሻዎችን እና "እንደ-ትክክለኛ" ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት እድገቶች የዞን ክፍፍል፣ የመኪና ማቆሚያ አነስተኛ ዋጋን ማስወገድ እና ለገቢያ ዋጋ መኖሪያ ቤት ጉልህ የሆኑ አካታቻዊ ቤቶች ያሉት ይገኙበታል። በቅርቡ የተካሄደው የAlewife ወረዳ መልሶ ማካለል ለመኖሪያ ቤቶች ቅድሚያ የሰጠ ነበር እና የንግድ ልማት ብቻ ሳይሆን እስከ 700 የሚደርሱ የገቢ ገደብ ያላቸው ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ቤቶች ጨምሮ እስከ 3,500 የሚደርሱ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን ያካትታል።

ከተማው በAffordable Housing Trust ላይ በየአመቱ 40 ሚሊዮን ዶላር በመመደብ ከተማው በተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ የፋይናንስ ኢንቨስትመንት አድርጓል። ይህ ባለፉት አምስት ዓመታት በሦስት እጥፍ አድጓል እና በዓመታዊ የሥራ ማስኬጃ በጀታችን ውስጥ ትልቁን የበጀት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱን ይወክላል። ከተማው በቅርቡ በከተማ ባለቤትነት የተያዙ ንብረቶች ቆጠራ በማውጣት ከከተማው ምክር ቤት ጋር እንዴት ለህብረተሰቡ ጥቅም እንደሚውሉ በተለይም በተመጣጣኝ ዋጋ መኖሪያ ቤት ላይ ውይይት ጀምሯል። በመጨረሻም በገበያ ላይ ያሉ ንብረቶችን በመገምገም ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርገናል እና በተመጣጣኝ ዋጋ አዲስ መኖሪያ ቤት ለመገንባት በማሰብ በተመጣጣኝ የቤት አቅራቢዎች ለሚደረጉ ግዢዎች የገንዘብ ድጋፍ አድርገናል።

ይህ ቁርጠኝነት ከፖሊሲ፣ ከኢንቨስትመንት እና ከልማት በላይ የሚዘልቅ ነው። ተግባራችን በሰዎች ዙሪያ ያተኮረ ነው። Cambridgeን አዲሱ ቤታቸው ለማድረግ የሚመኙ እና Cambridge ቤት ብለው ሲጠሩ ኩራት ለሚሰማቸው። ሰፊው ከመኖሪያ ቤት ጋር የተያያዙ ግብዓቶች እና አገልግሎቶች፣ ለቤቶች ማረጋጊያ የገንዘብ ድጎማ እና ድጋፍ፣ ተመጣጣኝ የቤት እድሎችን ማግኘት፣ እና ከቤት ማስወጣት እና የተከራይ መፈናቀልን ለመከላከል እርዳታ ማግኘትን ያካትታል። እንዲሁም ቤቶችን ለመግዛት ለሚፈልጉ ነዋሪዎች የተሟላ ድጋፍ እናቀርባለን፣ ይህም የከተማውን የገንዘብ ድጋፍ በገበያ ላይ ቤቶችን የሚገዙ ብቁ ነዋሪዎችን ለመርዳት፣ እንዲሁም የቤት ባለቤቶችን አስፈላጊውን የቤት ጥገና እና ማሻሻያ ማድረግን ያካትታል።
ይህ እትም ስለ ቁልፍ ቃል ኪዳኖቻችን፣ ተነሳሽኖቻችን እና ኢንቨስትመንቶቻችን ሰፋ ያለ መግለጫ ይሰጣል። የምክር ቤቱ እና የከተማው ሰራተኞች ባለፉት አመታት ባከናወኗቸው አስደናቂ ጥረቶች ሁሉ ኩራት ተሰምቶኛል። እና ግን ይህ ሁሉ ቢሆንም፣ ዋጋዎች መጨመራቸውን እንደቀጠሉ ነው እና ብዙ መደረግ ያሉባቸው ነገሮች አሉ - በከፍተኛ ደረጃ እና በአስቸኳይነት።

እንደማንኛውም ሥራችን፣ እንደ ማኅበረሰብ አብረን ወደፊት እንጓዛለን።

ከሰላምታ ጋር
ዪ-አን ሁዋንግ

City Manager Yi-An Huang swearing in at a podium in City Hall.
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here