U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ለVision Zero ያለን የማይናወጥ ቁርጠኝነት

ረቡዕ ፣4 ዲሴምበር 2024
" የፍጥነት ገደቦችን መቀነስ፣ ቀይ የትራፊክ መብራት እየበራ መታጠፍን መከልከል፣ የከተማዋን የተነጣጠሉ የብስክሌት መስመሮች አውታር ማስፋፋት እና የCambridge Truck Safety Ordinanceን መተግበር ከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል ይጠቀሳሉ። "

እ.ኤ.አ ማርች 21 ቀን 2016 ዓ.ም ላይ City Manager የComplete Streets እና Vision Zero ፖሊሲዎችን በይፋ ተግባራዊ ለማድረግ ያስተላለፉትን ውስኔ የCambridge City Council (የCambridge ከተማ ምክር ቤት) በአንድ ድምፅ በማፅደቁ፣ እነዚህን ግቦች በማሳካት ለሁሉም ተጠቃሚዎች ደኅንነቱ የተጠበቀ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የከተማ አስተዳደሩ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየት ተችሏል። Vision Zero በትራፊክ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰቱ ሞቶችን እና ከባድ ጉዳቶችን ለማስቀረት ጥሪ የሚያቀርብ ሲሆን እነዚህን አደጋዎች መከላከል እንደሚቻል እና መከላከልም እንደሚገባ አስረግጦ ይናገራል። የCambridge ከተማ አስተዳደር የVision Zero ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ ከአሜሪካ 17ኛው የከተማ አስተዳደር ነበር።

ከተማ አስተዳደሩ ለትራፊክ አደጋዎች፣ አካል ጉዳት እና ሞት መንስዔ የሆኑትን ነገሮች ለመለየት፣ እነዚህን ክስተቶች ለመከላከል አዲስ እና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መፍትሄዎችን ለመፍጠር እና ወደፊት የተሻለ ሥራ መሥራት እንድንችል ስኬቶቻችንን እና ቀሪ ተግዳሮቶችን ለመገምገም እየሠራ እንደመሆኑ መጠን፣ የድርጊት መርሃ ግብሩ መሠረት የሚሆነው መረጃን መሠረት ያደረገ የውሳኔ አሰጣጥ አሠራር ይሆናል።

የCambridge ከተማ አስተዳደር የVision Zero መርሆችን በሥራ ላይ በማዋል የሚከተሉትን ጨምሮ ሌሎች ተከታታይ እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርጓል፦

  • እንደ የትራፊክ ማረጋጊያ እና የደኅንነት መጠበቂያ ሰፊ ስትራቴጂ አካል በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመላው ከተማ የሚገኙ የፍጥነት ገደቦች ተቀንሰዋል።

እ.ኤ.አ በዲሴምበር ወር 2016 ዓ.ም ላይ ከተማ አስተዳደሩ በመላው ከተማ በሥራ ላይ የሚውለውን መነሻ የፍጥነት ገደብ ከ30 MPH ወደ 25 MPH ዝቅ አድርጓል። ከዚያም እ.ኤ.አ ማርች ወር 2018 ዓ.ም ላይ ከተማ አስተዳደሩ በSafer Squares ተነሳሽነት በኩል ከፍ ያለ የሕዝብ ብዛት እና ነቃ ያለ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ በሚታይባቸው "አደባባዮች(squares)" ተብለው በሚጠሩት አካባቢዎች ያሉትን የፍጥነት ገደቦች ከ25 MPH ወደ 20 MPH ቀንሷል።

በተጨማሪም እ.ኤ.አ በ2019 እና 2021 ዓ.ም መካከል የከተማ አስተዳደሩ Residential Safety Zonesን (የመኖሪያ አካባቢ ደኅንነት ዞኖችን) በሥራ ላይ በማዋል በአብዛኛዎቹ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥቅም ላይ የሚውሉ የሰፈር ውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ የፍጥነት ገደቡን ከ25 MPH ወደ 20 MPH ቀንሷል።

  • በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ባለቤትነት ሥር ያሉ የትራፊክ መብራቶች ላይ ቀይ መብራት እየበራ መታጠፍ ተከልክሏል። በCity Council (የከተማው ምክር ቤት) የጸደቀው እና እ.ኤ.አ በኖቬምበር ወር 2022 ዓ.ም በሁሉም መስቀለኛ መንገዶች ተግባራዊ የተደረገው ይህ እርምጃ ደኅንነትን ቀዳሚ ለማድረግ፣ አደጋዎችን ለመቀነስ፣ እና የከተማዋን የትራንስፖርት አውታር አጠቃላይ ቅልጥፍና ለማሻሻል የገባነውን ቃል ለማስፈጸም የወሰድናቸው እርምጃዎች አካል ነው። እ.ኤ.አ በ2023 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች የVision Zeroን መርሆች እውን ለማድረግ 225 "ቀይ በርቶ መታጠፍ አይቻልም" የሚሉ የመንገድ ምልክቶችን በማዘጋጀት በመላው ከተማዋ የሚገኙ በከተማ አስተዳደሩ ባለቤትነት ሥራ ያሉ መስቀለኛ መንገዶች ላይ መሰል የመንገድ ምልክቶችን ተከላ አጠናቅቀዋል። ቀይ መብራት ላይ መታጠፍ የሚፈቀድ በሚሆንበት ጊዜ አሽከርካሪዎች ዙሪያቸው ካሉት ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ይልቅ ትኩረታቸው ከመስቀለኛ መንገዱ በፍጥነት ለመውጣት የሚያስችላቸውን መንገድ ማግኘት ላይ ይሆናል። አሽከርካሪዎች ቀይ መብራት እየበራ ወደ ቀኝ የመታጠፍ አማራጭ ሳይኖራቸው ሲቀር ከተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጣ ትራፊክ፣ ከብስክሌት ነጂዎች እና ከእግረኞች ጋር ግጭት የመፈጠር ዕድሉ ይቀንሳል።
  • በከተማዋ አደባባዮች (City Squares) ለሚገኙ ለሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች ደኅንነትን ማሻሻል የCambridge አደባባዮች በከተማዋ ውስጥ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ማዕከሎችን ይወክላሉ። በመሆኑም ለሁሉም የአደባባዮቹ ተጠቃሚዎች በተለይም በእግር ለሚጓዙ፣ ብስክሌት ለሚነዱ እና የሕዝብ ማመላለሻ ለሚጠቀሙ ሰዎች ደኅንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ለመፍጠር እና የተሻሻሉ አሠራሮችን ለመተግበር ቅድሚያ ሰጥተን ሠርተናል። ይህም Inman Squareን የተሻሻለ እና ይበልጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የተሠራውን የዲዛይን እና ኮንስትራክሽን ሥራ ያካትታል። የተቃለሉ የመንገድ ምልክት ሥርዓቶች ተከላ፣ በግራ ወደ Somerville Avenue ለሚታጣፉ የብስክሌት ነጂዎች የሚያገለግለውን መዞሪያ መስመር የማቀላጠፍ ሥራ፣ እና የተሻሉ የእግረኛ መሻገሪያዎች ዝርጋታ በPorter Square ተከናውኗል። በKendall Square እና Lechmereም የደኅንነት ማሻሻያዎች በቀርብ ጊዜ ተጠናቅቀዋል (እንደ የGreen Line Extension እና የNorth Point District ልማት ተነሳሽነት አካል)።

በአሁኑ ወቅት በHarvard Square ላይ እየታካሄዱ ያሉት የደኅንነት ማሻሻያዎች ወደ ሰሜን ለሚጓዙ ብስክሌት ነጂዎች የሚያገለግል የተጠበቀ የብስክሌት መስመርን፣ ይበልጥ ግልፅ የሆኑ የእግረኛ መሻገሪያ መለያዎችን The በKiosk The Coop መካከል የሚዘረጋ አጠር ያለ የእግረኛ መሻገሪያን ያካትታሉ። ተጨማሪ ለውጦች በእያንዳንዱ አቅጣጫ ያለውን የተሽከርካሪ ትራፊክ ወደ አንድ የመንገድ መስመር መገደብ እና በPorter Square አቅራቢያ የሚፈጠረውን የብስክሌት ነጂ እና የአሽከርካሪ ውህደት ማስቀረትን ያካትታሉ።

በአሁኑ ወቅት በCentral Square ተጨማሪ ማሻሻያዎች በመካሄድ ላይ ናቸው።

  • የከተማዋን የተነጣጠሉ የብስክሌት መስመሮች አውታር የማስፋፋት ሥራ ተሠርቷል። Cambridge’s Cycling Safety Ordinance (የCambridge የብስክሌት ደኅንነት ድንጋጌ) በዓይነቱ የመጀመሪያው ድንጋጌ ሲሆን፣ ወደ 25 ማይል ርቀት ያላቸው የተነጣጠሉ የብስክሌት መስመሮች ዝርጋታን እንደ መስፈርት አስቀምጧል።
  • ከ10,000 ዶላር በላይ የሚገመት ውል ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተፈራርሞ እየሠራ ባለ ከተማዋ ውስጥ የሚገኝ ኩባንያ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ እና ደረጃ 3 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ፣ በጠቅላላ የተሽከርካሪ ክብደት ደረጃቸው ከ10,000 ፓውንድ በላይ የሚመዝኑ እና ከ15 MPH በላይ ፍጥነት መጓዝ የሚችሉ የሞተር ተሽከርካሪዎች፣ ተጎታቾች፣ ባለ ሁለት ጎማ ተጎታቾች ወይም ተሳቢዎች ላይ በግጭት ጊዜ ተሽከርካሪው ሥር ምንም ነገር እንዳይገባ የሚከላከሉ የጎን መከላከያዎች፣ ሰፋ ያለ አካባቢ የሚያሳዩ (ኮንቬክስ) መስታዎቶች፣ የጭነት መኪናውን ፊት ለፊት የሚያሳዩ (ክሮስ-ኦቨር) መስታዎቶች እና አንፀባራቂ የደህንነት ተለጣፊዎች እንዲገጠሙ የሚያስገድደው የCambridge Truck Safety Ordinance (የCambridge የጭነት መኪናዎች ደኅንነት አዋጅ) ተግባራዊ ተደርጓል።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here