Cambridge ውስጥ ይበልጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ማድረግ የሚያስችል እና ጠንካራ ግንኙነት የሚፈጥር አንድ አዲስ እርምጃ እየመጣ ነው የFitchburg Crossing Project በMBTA Fitchburg Commuter Rail Line ላይ የተዘጋጀ ማቋረጫ በመፍጠር፣ በባቡር ሐዲዱ የተከፋፈሉ አካባቢዎችን የሚያገናኝ ሲሆን፣ ወደ Danehy Park፣ Fresh Pond Mall እና ከዚያም አልፈው የሚሄዱ መንገዶችንም ይከፍታል።
ይህ ፕሮጀክት የባቡር ሐዲዱን ማቋረጥ ይበልጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ቀላል እና አመቺ ያደርገዋል። የከተማው አስተዳደር በAlewife Station አቅራቢያ ከሚገኘው Steel Place ጀምሮ እስከ Sherman Street ድረስ ከሐዲዱ ጎን ለጎን የሚዘረጋ አዲስ ባለብዙ አገልግሎት መንገድ እየገነባ ሲሆን፣ እንከን የለሽ ግንኙነቶችን ለተራማጆች እና ለብስክሌተኞች ይፈጥራል።
ለዲዛይን የሚሆነው የገንዘብ ድጋፍ መገኘቱ ስለተረጋገጠ፣ የከተማው አስተዳደር በዚህ ፎል ወቅት የዲዛይን ቡድን መርጦ፣ የዲዛይን ሥራውን ብዙም ሳይቆይ የሚጀምረው ይሆናል። አስደሳች መረጃዎችን ለማግኘት ይጠባበቁ!
ይህ ፕሮጀክት በDanehy New Street Connector Path (ማገናኛ መንገድ) ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ Danehy Parkን፣ Fresh Pondን እና Cambridge Watertown Greenwayን በማገናኘት፣ Cambridge ውስጥ ንቁ የትራንስፖርት ሥርዓት እንዲኖር የሚያመቻች የወደፊት ሁኔታን ይፈጥራል።