U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ከመሬት በታች የመቋቋም አቅምን መገንባት፦ The Port ፕሮጀክት ቅርጹን እየያዘ ነው

2026 ጃንዩወሪ 5, ሰኞ
" «እዚህ ያደረግነው ኢንቨስትመንት ቧንቧዎች ስለመዘርጋት እና አስፋልት ስለመገንባት ብቻ አይደለም። ችግር የመቋቋም አቅምን ስለመገንባት እና የCambridge ልብ የሆነውን ማኅበረሰብ ስለመጠበቅም ጭምር ነው።» "

በThe Port አካባቢ የተደረገው ጥልቅ ኢንቨስትመንት ያለፉትን ትምህርቶች ወደፊታችን ይበልጥ ጠንካራ እንዲሆን የሚያስችል ንድፍ እየሰጠን ይገኛል።

Cambridge ውስጥ በሚገኘው The Port አካባቢ ለውጥ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን፣ ለውጡም የሚካሄደው በአብዛኛው ከመሬት በታች ነው። በተለመዱ ጎዳናዎች እና የእግረኛ መንገዶች ስር፣ የከተማው አስተዳደር እስካሁን ካደረገው ትላልቅ የመሠረተ ልማት ማሻሻያ ጥረቶች መካከል አንዱ የሆነው The Port Infrastructure Project (የThe Port የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት) እየተካሄደ ይገኛል። ይህ የበርካታ ዓመታት ተነሳሽነት ቤቶችን፣ ጎዳናዎችን እና የሕዝብ ቦታዎችን እየጨመረ ከመጣው የጎርፍ ስጋት የሚከላከል ሲሆን፣ በተመሳሳይ ሁኔታም ከመሬት በላይ ይበልጥ አረንጓዴ፣ ይበልጥ የተሰባጠረ እና ተደራሽ የሆነ አካባቢን ይፈጥራል።

የሚለዋወጠውን የአየር ንብረት ፈተና መጋፈጥ

The Port ከጥንት ጀምሮ ለጎርፍ እጅግ ተጋላጭ ከሆኑ የCambridge አካባቢዎች መካከል አንዱ ነው። ብዙ ሕንጻዎች ዝቅተኛ ከፍታ ላይ በመሆናቸው፣ ከጥንት ጀምሮ መካከለኛ ዝናብ እንኳ ሲኖር ወደ ምድር ቤታቸው እና ወደ ጎዳናዎቻቸው ውኃ እንዲሰበሰብ ያደርግ ነበር። የአየር ንብረት ለውጥ እነዚህን ፈተናዎች በይበልጥ ያባባሰ ሲሆን፣ ወደ አካባቢው ይበልጥ ተደጋጋሚ እና ኃይለኛ ዝናብ እንዲመጣ አድርጓል።

የCambridge Public Works ሱፐርቫይዘር መሐንዲስ የሆኑት Jerry Friedman እንዳሉት፦ «መረጃው ነዋሪዎቹ ከጥንት ጀምሮ የሚያውቁትን ያሳያል፣ The Port ጎርፍ የሚከስተውን ጉዳት ጠንቅቆ ያውቃል።» «እዚህ ያደረግነው ኢንቨስትመንት ቧንቧዎች ስለመዘርጋት እና አስፋልት ስለመገንባት ብቻ አይደለም። ችግር የመቋቋም አቅምን ስለመገንባት እና የCambridge ልብ የሆነውን ማኅበረሰብ ስለመጠበቅም ጭምር ነው።»

በማኅበረሰቡ ችግር የመቋቋም አቅም ግንባታ ላይ የተደረገ የከተማው አስተዳደር ትልቅ ኢንቨስትመንት

በዚህ 2015 ዓ.ም ላይ መደበኛ ዲዛይን በመንደፍ እና የማኅበረሰብ ተሳትፎ በማነቃቃት በተጀመረው ፕሮጀክት ላይ Cambridge ከ35 ሚሊዮን ዶላር በላይ The Port ውስጥ ኢንቨስት የምታደርግ ሲሆን፣ ይህም አዳዲስ የውኃ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ እና የውኃ ማስተላለፊያ ሥርዓቶች፣ እንደ አዲስ የተገነቡ ጎዳናዎች እና የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም የተስፋፋ የዛፍ ሽፋን እና ክፍት ቦታ ግንባታን ይሸፍናል።

የዚህ ሥራ ዋና አካል የሚሆኑት ከመሬት በታች ያለው የዝናብ ውኃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፣ የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ገንዳ እና የፓምፕ ጣቢያዎቹ ይሆናሉ።

በBishop Allen Drive በሚገኘው Parking Lot 6 ስር የሚገኘው የዝናብ ውኃ ማጠራቀሚያ ገንዳው በ2021 ዓ.ም ላይ ተጠናቅቋል። ከMBTA Red Line (የMBTA ሬድ ላይን) ስር ተሻግሮ ከMassachusetts Avenue የዝናብ ውኃ ማስወገጃ ጋር በሚገናኘው አዲስ የፓምፕ ጣቢያ እና የመገልገያ መሿለኪያ ድጋፍ እስከ 390,000 gallons (ጋሎን) የዝናብ ውኃ መያዝ ይችላል። ሁለተኛው ገንዳ በ2030ዎቹ ውስጥ በሚመጀመረው ምዕራፍ ከWindsor Street አጠገብ ይገነባል።

ከመሠረተ ልማት ያለፈ፦ ጎዳናዎች፣ ፓርኮች እና የዕለት ተዕለት ተደራሽነት

ከዝናብ ውኃ አያያዝን ከማሻሻል በተጨማሪ፣ የThe Port ፕሮጀክት በአካባቢው እንደገና ኢንቨስት ለማድረግ የፈጠረ መልካም አጋጣሚ ነው። በBishop Allen Drive፣ Columbia Street፣ Cherry Street፣ Washington Street፣ Eaton Street እና Pine Street ያሉት ጎዳናዎች እና የእግረኛ መንገዶች የተሻለ ተደራሽነት፣ ደኅንነት እና ምቾት እንዲኖራቸው የመልሶ ግንባታ ሥራ ይከናወንባቸዋል።

የዲዛይን ማሻሻያዎቹ ለእግረኞች ቅድሚያ የሚሰጡ የጋራ ጎዳናዎችን መሥራት፣ ለዛፎች እና ለመትከያ የሚሆን ቦታ መፍጠር እንዲሁም ባህላዊ የድንበር ማቆሚያዎች በነበሩበት ቦታዎች ላይ አረንጓዴ ቦታ የመጨመር ሥራዎችን ያካትታሉ። ከተማው በአካባቢው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢቪ) ባትሪ መሙያ መሠረተ ልማትን ያስፋፋ ሲሆን፣ ይህም የCambridgeን የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት የመቀነስ ግብ ለማሳካት ያግዛል።

ለታደሰ አካባቢ የሚስማማ የታደሰ መናፈሻ

በThe Port ውስጥ ወሳኝ የማኅበረሰብ ቦታ የሆነው Clement G. Morgan Park እና Anthony Paolillo Tot Lot በአዲስ መልክ ተሻሽለው ሊሠሩ ነው። አዲሱ ዲዛይን የቆዩ ዛፎችን እና የላይላክ ቁጥቋጦዎችን ጠብቆ የሚያቆይ ሲሆን፣ በነዋሪዎች አስተያየት የተቀረጹ አዳዲስ ቦታዎችንም ያስተዋውቃል። ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው የቅርጫት ኳስ ሜዳ ተጨማሪ የተመልካች ቦታ፣ አዲስ መብራት እና ወለል እንዲኖረው ተደርጎ እንደገና እየተገነባ ይገኛል። ሙሉ በሙሉ አዲስ የሆኑት ገጽታዎች «ለታዳጊዎች ተብሎ የተሠራው ቦታ/የመወጣጫ ጫወታ ስፍራ» እንዲሁም ለትንንሽ ውሻዎች የሚሆነው አነስተኛ የመሮጫ ስፍራ ይካተቱበታል።

የCambridge ከተማ አስተዳደር Deputy City Manager የሆኑት Kathy Watkins «ነዋሪዎች ማሻሻያዎቹ ሰዎች መናፈሻውን የሚጠቀሙበትን ትክክለኛ መንገድ እንዲያንጸባርቁ ጠይቀውን ነበር፤ ይህ አዲስ የተሠራው ዲዛይን ማኅበረሰቡ የሚወደውን የጠበቀ፣ ማሻሻያ የሚያስፈልገወን ያሻሻለ፣ መናፈሻውንም ለወደፊቱ ያዘጋጀ ሥራ ታይቶበታል፤» በለዋል።

ለወደፊቱ የጋራ ቁርጠኝነት

የጋዝ ዋና መስመሮችን የመተካት ሥር አንስቶ የውኃ መስመሮችን እስከማሻሻል ሥራ የሚሠራበት የThe Port መሠረተ ልማት እያንዳንዱ ክፍል መልሶ እየለማ የሚገኝ ሲሆን፣ አንዳንዱ የአካባቢው ክፍል ደግሞ ልማትን በአንድ ክፍለ ዘመን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እያጣጣመው ይገኛል። በከተማ አስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች፣ በEversource እና በማኅበረሰቡ መካከል ያለው ትብብር Cambridge ለዘላቂ ልማት፣ እኩልነት እና ተደራሽነት ያላትን የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነት ያጎላል።

በ2030ዎቹ መጀመሪያ ላይ ተሠርቶ ሲጠናቀቅ፣ ይህ ጠንካራ ፕሮጀክት ከአዳዲስ ቧንቧዎች እና አስፋልቶች የላቀ ነገር አስቀምጦ ያልፋል። The Port ወደፊት ሊከሰቱ ለሚችሉ አውሎ ንፋሶች በተሻለ ሁኔታ መዘጋጀቱን፣ የከተማው አስተዳደርም በእያንዳንዱ አካባቢ ደኅንነት ዙሪያ በጥልቀት ኢንቨስት ማድረግ መቀጠሉን ማወቅ የአእምሮ ሰላም ይሰጣል።

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here