U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የማኅበረሰብ ገጽታ፦ Andromeda Lisle

2026 ጃንዩወሪ 5, ሰኞ
" በአዲሱ Tobin Montessori እና Darby Vassall Upper Schools ውስጥ ካሉ የግድግዳ ላይ ሥዕሎች አንዱ የሆነው ኸምፕባክ በሚል ስያሜ ከሚታወቁት የአሳ ነባሪ ዝርያዎች ውስጥ እናት እና ግልገሏን የሚያሳየው ሞዛይክ ነው። "

Andromeda Lisle በአዲሱ Tobin Montessori እና Darby Vassall ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ካሉ ብዙ ገጽታዎች መካከል አንድ ግድግዳ ጎልቶ የሚታይ ገጽታ አለ፦ ፣ በCambridge ተወላጅ በሆኑት አርቲስት Andromeda (Annie) Lisle የተሠራው፣ ኸምፕባክ በሚል ስያሜ ከሚታወቁት የአሳ ነባሪ ዝርያዎች መካከል እናት እና ግልገሏን የሚያሳየው Tranquility የተሰኘው የሞዛይክ ሥዕል ደምቆ ይታያል። የCambridge Rindge and Latin School ተመራቂ የሆነችው Lisle፣ ለእንስሳት፣ ለባዮሎጂ እና ለአፈ ታሪክ ባላት ፍቅር ላይ የተመሠረተ ሥራ የሠራች ሲሆን፣ ለዚህም ከቼሮኪ፣ ጥቁር እና አይሪሽ የዘር ግንዳቸው የወረሱትን ባህላዊ ማንነት እንዲሁም ከኢስተርን ውድላን ነባር ሕዝቦች እስከ ሴልቲክ እና ምዕራብ አፍሪካ ድረስ የዘለቁ የሥነ ጥበብ ወጎችን ተጠቅመዋል። በሥራቸው ውስጥ የማኅበረሰብ፣ የተፈጥሮ እና በጋራ ተባብሮ የመሥራት ጭብጦችን ዳስሰዋል። ባደጉባቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ ዘላቂ አሻራ መተው ምን ማለት እንደሆነ፣ እንደ አርቲስት ያደረጓቸውን ጉዞዎች እንዲሁም ከሥራቸው ጋር በየቀኑ ለሚገናኙ ተማሪዎች ያላቸውን ተስፋ በተመለከተ ከLisle ጋር ተነጋግረናል።

ጥያቄ፦ በMontessori Vassall Upper Schools ውስጥ ስላለው የአሳ ነባሪው የግድግዳ ላይ ሥዕል የሐሳብ መነሻዎ ምን እንደነበር ሊነግሩን ይችላሉ?

AL፦ሦስት ክፍሎች አሉት። መጀመሪያ የሠራሁትን የግድግዳ ላይ ሥዕል ያሠራኝ የHarvard Ed ፖርታል የነበረ ሲሆን፣ ሥዕሉም የአሳ ነባሪ ሥዕል ቢሆንም መጠኑ ግን ከዚህ በጣም ያነሰ ነበር። ያነሳሳኝ ለአካባቢው ነባር ሕዝባቦች የባህላዊ ጀግና እንደሆነ የሚነገርለት እና ግዙፍ ቢሆንም ወደ አሳ ነባሪነት መቀየር ይችላል ተብሎ የሚወራለት Moshup የተሰኘው የሕዝብ ጀግና ታሪኮችን መስማት ሲሆን፣ እሱም በአካባቢው ባህል እና ቱፊት ውስጥ ዋና አካል በመሆኑ ለእሱ መታሰቢያነት ለመሥራት ያለኝ ፍላጎት ነው ያነሳሳኝ። ኸምፕባክ እየተባለ የሚጠራውን የአሳ ነባሪ ዝርያ የመረጥኩበት ምክንያት እዚህ አካባቢ፣ ኸምፕባክ አሳ ነባሪዎች ለብዙ ሰዎች ትልቅ ትርጉም ስላላቸው ነው። ለMassachusetts ብቻም ሳይሆን፣ ለመላው Northeast አካባቢ ትልቅ የባህል ምልክት ናቸው። ሰዎች እነሱን መመልከት እና ማጥናት ይወዳሉ፣ እኔ በግሌ ደግሞ ካሉት የአሳ ነባሪ ዝርያዎች መካከል እጅግ በጣም ውቦች ናቸው ብዬ አስባለሁ። ሦስተኛው ምክንያት አሳ ነባሪዎች እጅግ በጣም ለረጅም ጊዜ ልጆቻቸውን በመንከባከብ ከሚያሳልፉ ጥቂት እንስሳዎች መካከል የሚገኙ መሆናቸው ነው፤ ለአንድ ወይም ሁለት ግልገሎች ብቻ እንክብካቤ ለመስጠት ብዙ ኃይል ይሰጣሉ። ብዙ ዓመታትን በማሳደግ፣ በማስተማር እና በዓለማቸው ውስጥ እንዴት መኖር እንዳለባቸው በማሳየት ያሳልፋሉ። እኔም ይህ ልጆች በሕይወታቸው እጅግ በጣም ወሳኝ እና ለተለያዩ ነገሮች ተጋላጭ በሆኑበት ምዕራፋቸው ላይ ሳሉ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙት አዋቂዎች በመሪነት መንገድ የሚያመላክቱበት እና በዓለማችን ውስጥ ራሳቸውን ለመቻል የሚያግዟቸውን መሣሪያዎች የሚሰጡበት የትምህርት ቤት ጥሩ ተምሳሌት ነው ብዬ አሰብኩኝ። ለዚያም ነው አዋቂ መምህራንን እና ሠራተኞችን ጨምሮ ልጆች መልካም ሕይወት ለመኖር የሚያስችላቸውን ምርጥ የሕይወት ክህሎቶችን እንዲማሩ የሚያስችላቸውን ድጋፍ ሰጪ ቡድን በሙሉ እንዲወክል በማሰብ እና የሁለቱም ተምሳሌት እንዲሆን ንድፉን ስቀርጸው ግልገልዋን ከአሳ ነባሪዋ ጀርባ ያደረኳት።

ጥያቄ፦ በCambridge ባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚቀር ነገር መፍጠር በግል ደረጃ ለእርስዎ ምን ትርጉም አለው?

AL፦ ትልቅ ትርጉም አለው። አካል ጉዳተኛ ነኝ፤ Social Security (ማኅበራዊ ዋስትና) ይሰጠኛል፤ እንዲሁም ብዙ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን እጠቀማለሁ። በመሆኑም መደበኛ ሰው መሥራት የሚችለውን ያህል መሥራት ባልችልም፣ ለዚህ ሁሉ ጊዜ ሲደግፈኝ የነበረውን ማኅበረሰቤን ለማመስገን ግን ሁልጊዜ በሆነ መንገድ መልሼ መስጠት እፈልግ ነበር። ሞዛይኩ ለእኔ ይህን ለማድረግ ጥሩ መንገድ ነበር። ይህ አጋጣሚ እኔን የሚጠቅም ውብ ዕድል የነበረ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ እኔን ያሳደገኝን ማኅበረሰብም የሚጠቅም ነበር። ይህንን የተደረገልኝን መልካም ነገር መልሶ መስጠት ያስቻለኝ ደስ የሚል መልካም ዑደት የነበረ ሲሆን፣ መልሰን የመስጠት ግዴታ እንዴሌለብን ባውቅም፣ ይህን ማድረግ ግን ጥሩ መንፈስ መሰነቅን ያመላክታል። እናም ሁልጊዜም ቢሆን ለሚደረግልን መልካም ነገሮች አድናቆትን እና ምስጋናን ማሳየት አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማኛል።

ጥያቄ፦ ይህን ፕሮጀክት በCambridge ውስጥ ስላለው ውክልና፣ ማኅበረሰብ፣ ወይም የባህል ማንነት ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም ጭምር እንደ ትልቅ የታሪክ አካል አድርገው ይመለከቱታል?

AL፦ ኦ አዎ፣ ሙሉ በሙሉ። እናም ቀደም ሲል እንደገለጽኩት፣ የማኅበረሰብ ስሜትን መፍጠር እና በተለይ ለልጆቹ በዚህ ዓለም ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ ማሳየት ፈልጌ ነበር። የሚረዷችሁ ሰዎች በዙሪያችሁ ያሉት ሰዎች ናቸው፣ እናም በእነሱ መተማመን ይቻላል። አጋዥ ከፈለጋችኋቸው እዚሁ ያሉት እውነተኛ ሰዎች ለእናንተ አሉላችሁ። አንዳንድ ጊዜ እርዳታ ለመጠየቅ በጣም ከባድ ቢሆንም፣ ይህን ማድረግ ግን የሕይወት አንድ አካል ነው።


Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here