U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ከCity Manager የተላለፈ መልዕክት፦

2026 ጃንዩወሪ 5, ሰኞ
" በሁሉም ዲፓርትመንቶች ውስጥ እያንዳንዱ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት የተለያዩ ጥቅሞችን እንዲያስገኝ አብረን እየሠራን እንገኛለን። "

ታላላቅ ከተሞች የተገነቡት በታሪካቸው ብቻ ሳይሆን፣ በመለወጥ ችሎታቸውም ጭምር ነው። ኅብረተሰብ፣ ፈጠራ እና ለወደፊቱ የምንሰንቀው የጋራ ቁርጠኝነት የከተማችን መገለጫዎች ሆነው ቆይተዋል። ይህ መንፈስ Cambridge ውስጥ በሁሉም ማዕዘናት ተጽንጸባርቆ የሚታይ ሲሆን፣ በተለይ ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ለማድረግ ተብለው በተገነቡ አዳዲስ ጎዳናዎች፣ ከፍተኛ የመማር ማስተማር እና የዘላቂ ልማት ጥራት ደረጃዎችን አሟልተው በተገነቡ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲጫወቱና እንዲገናኙ በሚጋብዙ ታድሰው በተዘጋጁ መናፈሻዎችና የሕዝብ ቦታዎች ላይ ይታያል።

ይህ የCambridge Life እትም በሰፈሮቻችን ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ለውጥ ያቀርባል። እነዚህ ትላልቅና ትናንሽ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የምንንቀሳቀስበትን፣ የምንማርበትን፣ የምንኖርበትን እና የምንሠራበትን መንገድ እየቀየሩ ይገኛሉ። እነዚህም ፕሮጀክቶች ለዓመታት ታስቦ የተነደፈ ዕቅድ መኖሩን፣ ጠንካራ የማኅበረሰብ ተሳትፎ መፈጥሩን፣ ፍትሐዊ እና ብርቱ ማኅበረሰብ እንዲጎለብት ለማድረግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ያመለክታሉ።

የመሠረተ ልማት ሥራዎች ሁልጊዜ ማራኪ ላይሆኑ፣ አንዳንዴም በቀን ተቀን እንቅስቃሴዎቻችን ላይ እክል ሊፈጥሩ የሚችሉ ቢሆንም፣ የሕይወታችንን እያንዳንዱን ገጽታ የሚነኩ መሆናቸው ግን እርግጥ ነው። አንድን ጎዳና ድጋሚ ስናነጥፍ ወይም ያረጁ መገልገያዎችን ስንለውጥ፣ የከተማችን ሥርዓቶች እየተለወጠ ያለውን የአየር ንብረት ፈተናዎች መቋቋም እንዲችሉ አቅም እየገነባን፣ በአዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ላይ ኢንቨስት እያደረግን፣ የአካባቢን የንግድ ሕይወት እየደገፍን እና ሌሎች ሥራዎችንም እየሠራን ነው። አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን ስንገነባ፣ ለሚመጡት ትውልዶች የማወቅ ጉጉትን እና ትብብርን የሚጭሩ ቦታዎችን እየፈጠርን ነው። አንድን መናፈሻ ስናድስ፣ ከተማችን ለመኖር ምቹ ቦታ የሚያደርጋትን ማኅበራዊ ትስስር እያጠናከርን ነው።

በተጨማሪ እነዚህ ፕሮጀክቶች የከተማዋ አስተዳደር፣ ነዋሪዎቿ እና የማኅበረሰቡ አጋሮች አብረው ሲሠሩ ምን ሊሳካ እንደሚችልም ያሳያሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በሕዝባዊ ስብሰባዎች፣ ንድፍ ወርክሾፖች፣ ዳሰሳ ጥናቶች እና ፖፕ-አፕ ዝግጅቶች አማካኝነት ሁሉንም ነገር መልክ ለማስያዝ ያገዙንን፣ አዳዲስ ዛፎች እና ወንበሮች የት መተከል እንዳለባቸው ከመግለጽ አንስቶ መስቀለኛ መንገዶች እና የዝናብ ውኃ ፍሳሽ ሥርዓቶች ንድፍ ምን መምሰል እንዳለበትም ጭምር የገለጹልንን ሐሳቦች ሲያካፍሉን ቆይተዋል። ውጤቱም እዚህ የሚኖሩ ሰዎች ያነገቧቸውን እሴቶች በትክክል የሚያንጸባርቅ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽ፣ ሁሉን ያካተተ እና ወደፊት ተስፋ ያለው መሠረተ ልማት ነው።

በሁሉም ዲፓርትመንቶች ውስጥ እያንዳንዱ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት የተለያዩ ጥቅሞችን እንዲያስገኝ አብረን እየሠራን ሲሆን፣ ከእነዚህም ጥቅሞች መካከል ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት ግቦችን ማሳካት፣ አካባቢውን ማሻሻል፣ አረንጓዴ ቦታዎችን ማስፋፋት እና ተደራሽነትን ለሁሉም ማጎልበት ይገኙበታል። ብዙዎቹ ፕሮጀክቶቻችን ዘላቂ የንድፍ ባህሪያትን የተላበሱ ሲሆኑ፣ ለአብነት ያህል የጎርፍ መጥለቅለቅን የሚቀንሱ እና የውኃ ጥራትን የሚያሻሽሉ በኤሌክትሪክ ብቻ የሚሠሩ የግንባታ ሥርዓቶች እንዲሁም የዝናብ ውኃ የሚጠቀሙ የአትክልት ቦታዎች ይገኙባቸዋል። እነዚህ እርምጃዎች በጋራ ከተማችን ወዳስቀመጠችው የአየር ንብረት ለውጥ እና የመቋቋም አቅም ጉልበታ ግቦች ይበልጥ እንድንቀርብ የሚያደርጉን ሲሆን፣ የዛሬው እድገት ነገን እንደማያጨልምም ያረጋግጡልናል።

ከተማችንን የሚያንቀሳቅሱት ታታሪ ሠራተኞች ባይኖሩ ኖሮ ይህ ሁሉ ሥራ ፈጽሞ ሊሳካ የማይችል ሲሆን፣ ሠራተኞቻችን፣ መሐንዲሶቻችን፣ እቅድ አውጪዎቻችን፣ አስተማሪዎቻችን፣ የጥገና ሠራተኞቻችን እና የሕዝብ ደኅንነት ሠራተኞቻችን እነዚህ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። የእነሱ ሙያዊ ብቃት እና ኩራት በሚገነቡት እና ይዘው በእንክብካቤ በሚያቆዩት እያንዳንዱ አዲስ የእግረኛ መንገድ፣ መጫወቻ ሜዳ፣ የመማሪያ ክፍል እና የመንገድ መብራት ላይ ይንጸባረቃል።

ለነዋሪዎቻችን፣ ስለ ትዕግስታችሁ እና አጋርነታችሁ እናመሰግናለን። የግንባታ ሥራ ፈታኝ ቢሆንም ግን የእድሳት እና የእድገት ምልክት ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች ቅርጽ ሲይዙ፣ ለጋራ የወደፊታችን ጠንካራ መሠረት ይፈጥራሉ፤ ይህም ለሚመጡት ዐሥርት ዓመታት ዕድል ፈጠራን፣ ፍትሐዊነትን እና የማኅበረሰብ ትስስርን ለማጎልበት ይደግፋል።

ያከናወንናቸውን እና ወደፊት የታቀዱትን ሥራዎች ለማየት ይህንን እትም እንዲመለከቱ እጋብዛለሁ። እነዚህ ታሪኮች በዋናነት በሰዎች፣ በራዕይ እና የአንዲት ከተማ ምርጥ ቀናት ሁልጊዜም ወደፊት ናቸው በሚለው እምነት ዙሪያ ያተኩራሉ።

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here