ዛሬ በRiver Street ሲራመዱ ወይም ሲነዱ ለውጥ እየተፈጠረ መሆኑን ማየት ቀላል ነው። ከግንባታ ምልክቶች እና በለውጥ ላይ ካሉ መንገዶቿ ባሻገር የCambridge ትልቅ ባለራዕይ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት የሆነው፣ የRiver Street እና የሚያገናኙት የሕዝብ ቦታዎች ሙሉ ዳግም ግንባታ ፕሮጀክት ይገኛል። ይህ ፕሮጀክት ለዓመታት ሲዘጋጅ የነበረ ሲሆን፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ደማቅ እና ችግሮችን ይበልጥ የሚቋቋም ሰፈር እና የከተማ መንገዶች ለመፍጠር ባለው ትብብር፣ ፈጠራ እና የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ ነው።
የRiver Street የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት የCarl Barron Plaza፣ Pleasant Street፣ Norman M. Tubman Square እና በአካባቢው ያሉ የሰፈር መንገዶችን ጨምሮ ከMemorial Drive እስከ Massachusetts Avenue ድረስ ያለውን መተላለፊያ መንገድ እየለወጠው ይገኛል። ከአንድ ክፍለ ዘመን ዕድሜ በላይ ያስቆጠሩትን ከመሬት በታች ላሉ መገልገያዎች አስፈላጊ ጥገናዎችን ለማከናወን ተብሎ ቢጀመርም፣ አሁን ላይ ግን እዚህ ለሚኖሩ፣ ለሚሠሩ እና ለሚጓጓዙ ሰዎች በሙሉ ይህ ወሳኝ ጎዳና የሚሰጠውን አገልግሎት ከእንደገና በአዲስ መልክጁ አሻሽሎ ለማሰብ የሚያስችል በትውልድ አንድ ጊዜ የሚያጋጥም አጋጣሚ ሆኖ ተገኝቷል።
«River Street ከመንገድ መስመር በላይ ነው» ይላሉ የDepartment of Public Works (የሕዝብ ሥራዎች መምሪያ) የከተማው መሐንዲስ የሆኑት Jim Wilcox። «አገናኝ ነው፤ በሰፈሮች መካከል፣ በንግድ ድርጅቶች መካከል እንዲሁም በሰዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት ያሳልጣል። በዚህ የዲዛይን ሂደት ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ውሳኔ ያንን የዕለት ተዕለት ተሞክሮ በማሻሻል ላይ የተመሠረተ ነው።»
ፕሮጀክቱ በ2022 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ግንባታ የጀመረ ሲሆን፣ ብዙዎቹ ክፍሎች ቀደም ብለው ተጠናቀውለት በ2026 ዓ.ም ፎል ወቅት በዋናነት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ጎዳናው ክፍት ሆኖ እንዲቆይ እና ነዋሪዎች፣ የንግድ ድርጅቶች እና የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች ሁልጊዜም ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ ሥራው አጭር፣ በጥንቃቄ በተያዙ ምዕራፎች ሲከናወን ቆይቷል።
ለወደፊቱ መገንባት
አብዛኛው ሥራ የሚጀምረው ከመሬት በታች ነው። River Street ከመሬት በታች ያሉት የመሠረተ ልማት ክፍሎች ከመቶ ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ በመሆናቸው፣ ፕሮጀክቱ ዘመናዊ የአገልግሎት ደረጃዎችን እና የአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም አቅምን ለመደገፍ ሙሉ በሙሉ አዳዲስ የፍሳሽ ማስወገጃዎችን፣ የዝናብ ውኃ ሥርዓቶችን እና ዋና ዋና የውኃ መስመሮችን አካትቷል።
ከመሬት በላይ ዳግም ዲዛይን የተሠራለት ክፍል ደግሞ በእግር ለሚሄዱ፣ በብስክሌት ለሚነዱ፣ አውቶብስ ለሚይዙ ወይም ተሽከርካሪ ለሚነዱ ሁሉ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ይበልጥ ምቹ ስፍራ ይሰጣል። ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች፣ የተሻሻሉ መሻገሪያዎች እና ተደራሽ የሕዝብ ቦታዎች በመተላለፊያ መንገዱ መጓዝን እና መደሰትን ቀላል ያደርጉታል።
ከማኅበረሰቡ ጋር፣ ለማኅበረሰቡ የተነደፈ
ፕሮጀክቱ ሲጀመር አንስቶ የRiver Street ፕሮጀክት ቅርጽ እንዲይዝ ያገዙት ጠንቅቀው የሚያውቁት ሰዎች ናቸው። ፕሮጀክቱ ሲጀመር የከተማው አስተዳደር በዲዛይን ሂደቱ እያንዳንዱ ደረጃ ላይ ግብረመልስ እና ሐሳቦች እንዲሰጡ በመጠየቅ፣ ጠንካራ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሂደት እንዲፈጠር አመቻችቷል።
ይሄ ሂደት የሚከተሉትን ያካተተ ነበር፦
- 12 ጊዜ የተገናኙ የነዋሪዎች፣ የንግድ ድርጅቶች እና የሰፈር ተወካዮች የሥራ ቡድን
- ሰዎች በቦታው ላይ በቀጥታ አሰተያየት እንዲያካፍሉ ያደረጉ የማኅበረሰብ ስብሰባዎች፣ የፕሮጀክት ጉብኝቶች እና ለሁሉም ክፍት የተደረጉ ውጭ ላይ የተዘጋጁ ስብሰባዎች
- የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችን ለመረዳት ከአካባቢው የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ጋር የተደረጉ ጉብኝቶች
- ሁሉም ሰው መረጃ እንዲያገኝ እና እንዲሳተፍ የፕሮጀክት ድረ-ገጽ፣ ተለዋዋጭ ካርታዎች እና ምናባዊ ክፍት ስብሰባዎች ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች የኢንተርኔት መሣሪያዎችን መጠቀም
ይህ ወጥ እና ግልጽ አቀራረብ የማኅበረሰቡ ዋነኛ እሴቶች የሆኑትን ደኅንነት፣ ተደራሽነት፣ ውበት እና ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲዛይን እንዲተገበር ረድቷል።
በማኅበረሰብ ላይ ኢንቨስት ማድረግ
የከተማው አስተዳደር ባነገበው ቀጣይነት ያለው የFive-Year Sidewalk and Street Reconstruction Plan (የአምስት ዓመት የእግረኛ መንገድና የጎዳና መልሶ ግንባታ ዕቅድ) መሠረት ከRiver Street ባሻገር፣ Fairmont Avenue፣ Rockwell Street፣ Laurel Street እና ሌሎችንም ጨምሮ በአቅራቢያው ያሉ የማኅበረሰቡ መንገዶች ግንባታ የሚካሄድባቸው ወይም ተገንብተው ያለቁ ቦታዎች ናቸው።
Fairmont Avenue በሁሉም ዕድሜ እና ችሎታ ላይ ያሉ ሰዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያገለግሉ መንገዶችን በመንደፍ ላይ ባተኮረው Shared Street (የጋራ ጎዳና) ተብሎ የተጠራው ፕሮግራም ከእንደገና በአዲስ መልክ ተሠርቷል። አንዳንድ ጊዜ «የጫወታ ጎዳናዎች» ወይም «የሳሎን ጎዳናዎች» በመባል የሚታወቁት እነዚህ የጋራ ጎዳናዎች በዝቅተኛ ፍጥነት የሚጓዙ ተሽከርካሪዎችን እና ብስክሌተኞችን እያስተናገዱ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ለእገረኞች ቅድሚያ በመስጠታቸው በሰፊው ይታወቃሉ።
በአጠቃላይ እነዚህ ማሻሻያዎች በሰፈሩ የረጅም ጊዜ ሕያውነት እና ለእግር ተስማሚነት ላይ የተደረገ ዋና ኢንቨስትመንትን ይወክላሉ።
ወደፊት መመልከት
ግንባታው እየቀጠለ ሲሄድ፣ የከተማው አስተዳደር እና አጋሮቹ የግንኙነት ሥራዎችን ክፍት እና ቶሎ ምላሽ የሚሰጥባቸው በማድረግ፣ መስተጓጎልን መቀነስ ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
በመጨረሻም የRiver Street የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት አዲስ ቧንቧዎች ስለመዘርጋት፣ ንጣፍ ወይም ፕላዛዎች ስለመገንባት ብቻ ሳይሆን፣ አንድ ቦታ ላይ ማኅበረሰቡ የሚሰማውን የባለቤትነት ስሜት ስለማደስም ጭምር ነው። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ፣ ይህ በአዲስ መልኩ ተሻሽሎ የተሠራው መተላለፊያ መንገድ የCambridgeን ምርጥ ገጽታዎች የሚያንጸባርቅ፣ አንድ ብሎኬት ከመደርደር አንስቶ በአንድ ላይ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን የሚገነባ ማኅበረሰብ እንዳለ የሚያሳዩ እሴቶቿን የሚያንጸባርቅ ነው።