U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

የHarvard Square KiOSK ዳግም ሕይወት

2026 ጃንዩወሪ 5, ሰኞ
" «ይህ ለውጥ የKiOSKን የበለጸገ ታሪክ የሚያከብር ሲሆን፣ በHarvard Square መሀል ለመሰብሰብ፣ ለፈጠራ እና ለሕዝባዊ ተሳትፎ አዳዲስ መልካም አጋጣሚዎችን ይፈጥራል።» "

ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል በHarvard Square መሀል የሚገኘው ትንሹ የጡብ ሕንጻ የግንኙነት ምልክት ሆኖ ቆይቷል። በ1927 ዓ.ም የምድር ውስጥ ባቡር መግቢያ ሆኖ የተገነባው እና በኋላም የታዋቂው Out of Town News መኖሪያ የነበረው KiOSK፣ ሁልጊዜም ከሕንጻ በላይ የሆነ ማንነት የነበረው፣ የመገናኛ ነጥብ፣ የባህል ምልክት እና የCambridge የማያቋርጥ ንቃት ምልክት ሆኖ ቆይቷል።

አሁን ለዓመታት የማኅበረሰብ አስተያየት ሲሰበስብ፣ በጥንቃቄ እቅድ ሲያወጣ እና አድካሚ የእድሳት ሥራ ሲሠራ ከቆየ በኋላ የCambridge ከተማ አስተዳደር ለዚህ ተወዳጅ ምልክት ጠንካራ ራዕይ ያነገበ አዲስ ምዕራፍ ይፋ አድርጓል። ሜይ ወር 2025 ዓ.ም ላይ ታሪካዊው KiOSK የCambridge KiOSK ተብሎ ዳግም ተከፈተ፤ ይህ ቦታ የከተማዋን ፈጠራ እና ልዩነት ታሳቢ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ የባህል ኢንኩቤተር፣ የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራ እና ለጎብኚዎች የመረጃ ማዕከል ነው።

የመክፈቻው ቀን ክብረ በዓል የቀጥታ ስርጭት የሙዚቃ ትዕይንት የነበረበት፣ ቀላል ምግቦች እና መጠጦች የቀረቡበት እንዲሁም ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች በእኩልነት የተቀየረውን ቦታ ለመጀመሪያ ጊዜ ገብተው እንዲመለከቱ ዕድል የተመቻቸበት ቀን ነበር።

ያለፈውን ማክበር፣ የወደፊቱን መቅረጽ

የመክፈቻው ኤግዚቢሽን የCambridgeን የኅትመት ሚዲያ ውርስ የሚያከብር ጊዜያዊ ጋዜጣ መሸጫን በማቅረብ፣ የKiOSKን ረዥም ታሪክ አክብሯል። ጎብኚዎች አብዮታዊ ጋዜጣዎች፣ የሙዚቃ ኅትመቶች እና ራሱ Out of Town News የከተማዋን ማንነት እንዴት መቅረጽ እንደቻሉ ተመልክተዋል። በየሳምንቱ የሚዘጋጁት የ«15 Minutes of Cambridge» ውይይቶች ለእነዚህ ታሪኮች ሕይወት የዘሩባቸው ሲሆን፣ በታሪክ እና በዛሬ ውይይቶች መካከል ድልድይ መሆንም ችለዋል።

ነገር ግን አዲሱ KiOSK ወደ ኋላ ስለመመልከት ብቻ አይደለም። ይልቁንም ለሥነ ጥበብ፣ ለትርዒቶች እንዲሁም ለማኅበረሰብ ግንኙነት ተለማጭ፣ ዘወትር እያደገ የሚሄድ ቦታን ስለመፍጠርም ጭምር ነው። ጎብኚዎች ሙሉ በሙሉ በCambridge ነዋሪዎች የተዘጋጁ የቀጥታ ስርጭት የሙዚቃ ትርዒቶችን፣ የግጥም ንባብን፣ የሥነ ጥበብ ወርክሾፖችን፣ የቀልድ ምሽቶችን እና ወቅቱን የጠበቁ ምርቶች የሚያቀርቡ ኤግዚቢሽኖችን ማግኘት ችለዋል።

City Manager የሆኑት Yi-An Huang Yi-An Huang «ይህ ለውጥ የKiOSKን የበለጸገ ታሪክ የሚያከብር ሲሆን፣ በHarvard Square መሃል ለመሰብሰብ፣ ለፈጠራ እና ለሕዝባዊ ተሳትፎ አዳዲስ መልካም አጋጣሚዎችን ይፈጥራል፤» ብለዋል። «ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች ተገኝተው፣ የCambridgeን የባህል ድምቀት የሚያከብሩበት እንግዳ ተቀባይ ማዕከል ሆኖ ሲያድግ እና ሲበለጽግ በማየታችን ደስ ብሎናል።»

ዓመታትን የወሰደ የማኅበረሰብ ራዕይ

KiOSKን በአዲስ መልኩ አስቦ የመሥራት ሥራው በአንድ ሌሊት አልመጣም። ዲዛይን የማውጣት ሂደቱ በሁለት ዓመት የማኅበረሰብ ተሳትፎ ተመርቶ፣ ቦታው ሁሉንም አካታች፣ ተለማጭ እና ለCambridge እውነተኛ እሴቶች የቆመ እንዲሆን የፈለጉትን የነዋሪዎች፣ የአካባቢው ድርጅቶች እና የሠዓሊዎች ድምፅ ያንጸባረቀ ነበር።

በጥንቃቄ ታድሰው ከተሠሩት ጣሪያ እና የጡብ ዓምዶች ጀምሮ ሕንጻውን ወደ ፕላዛው ክፍት እስከሚያደርጉት ዘመናዊ መስኮቶች ድረስ እያንዳንዱ ዝርዝር ታሪክን በማክበር እና የወደፊቱን በመቀበል መካከል ያለውን ሚዛናዊነት ጠብቆ ይታያል።

Deputy City Manager የሆኑት Kathy Watkins «ይህ በእውነት በፍቅር የተሠራ ሥራ ነው፤» ብለዋል። «ጎብኚዎች ወደ ላይ እንዲመለከቱ፣ የታደሰውን የእንጨት ጣሪያ እና ታሪካዊ ዝርዝሮች እንዲያስተውሉ፣ ቦታውንም ዛሬ ላይ ተደራሽ እና ማራኪ እንዲሆን የሚያደርጉትን በጥንቃቄ የተሠሩ ዘመናዊ ዝርዝሮችን አስተውለው እንዲመለከቱ እናበረታታለን።»

ለጎብኚዎች መግቢያ፣ ለነዋሪዎች ደግሞ መድረክ

KiOSK በተጨማሪ ለCambridge Visitor Information Center (የCambridge ጎብኚዎች መረጃ ማዕከል) አዲስ መገኛ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፣ ከተማዋን በሚገባ የሚያውቁ አብዛኛዎቹ የቀድሞ Out of Town News ታማኝ ደንበኞች የነበሩ፣ የበጎ ፈቃደኞች ወዳጅነት፣ በጥንቃቄ የተመረጡ የጉዞ መርሀግብሮች እና የውስጥ አዋቂ ምክሮች የሚቀርቡበት ስፍራ ነው።

የCambridge Office for Tourism (የካምብሪጅ ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት) ዋና ዳይሬክተር Candice Beaulieu «ጎብኚዎች የሚያገኙት ካርታዎችን እና አቅጣጫዎችን ብቻ ሳይሆን አይደለም፤ የCambridgeን ምርጥ ሥነ ጥበብ፣ ባህል እና ታሪክ በግል ለመለማመድ የሚያስችሉ መንገዶችንም ጭምር ያገኛሉ።» ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በKiOSK የፕሮግራም አስተዳዳሪ የሆነው ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት CultureHouse፣ የአካባቢ ሠዓሊዎች፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና ንግዶች ፈጠራቸውን ወደ ቦታው እንዲያመጡ ግብዣ አቅርቧል። ዓላማው መርሀግብሩ ከትናንሽ ትርዒቶች እስከ የተግባር ወርክሾፖች ድረስ የያዘ እንደ ከተማው ብዝሃነት እና ድምቀት ያለው አድርጎ ማስቀጠል ነው።

የCultureHouse ዋና ዳይሬክተር የሆኑት Aaron Greiner «Out of Town News ቀደም ሲል ዓለም አቀፍ ውይይቶችን ወደ Harvard Square ያመጣ ነበር፤ ዛሬ፣ ትልቅ ቦታ ያላቸው፣ የአካባቢ ግንኙነቶች ናቸው፤ KiOSK በበሩ ውስጥ ለሚያልፍ ሁሉ የመገኘት እና የመተሳሰብ ስሜትን የሚፈጥሩ ጊዜያት ስለመፍጠር ነው፤» ብለዋል።

ከሕንጻ በላይ

የKiOSK ዳግም መከፈት የትልቅ ለውጥ አካል ነው። የከተማ አስተዳደሩ የHarvard Squareን ማዕከላዊ ፕላዛ የመልሶ ግንባታ ሥራ እያከናወነ ሲሆን፣ ይህም አዲስ የመሬት ገጽታ፣ የሕዝብ መቀመጫ እና የተሻሻለ ተደራሽነት እንዲኖር የማድረግ ሥራዎችን ያካትታል። The plaza እና KiOSK በአንድነት በCambridge ልብ ውስጥ እንግዳ ተቀባይ ቦታን ይፈጥራሉ።

ይህ ፕሮጀክት ስለ ሕንጻ እድሳት ብቻ ሳይሆን፣ ለማኅበረሰብ ያለውን ቁርጠኝነት የማጠናከር ማስታወሻም ጭምር ነው። የKiOSK አዲስ ሕይወት የሕዝብ ቦታዎች ተነሳሽነትን መጫር፣ አካታች መሆን እና ግንኙነት መፍጠር መቻል አለባቸው የሚለውን የከተማዋን እምነት ያንጸባርቃል።

በሮቹ እንደገና ሲከፈቱ፣ በHarvard Square የሚገኘው ትንሹ የጡብ ሕንጻ ለቀጣዩ ምዕራፍ ዝግጁ ሆኖ የሚቅም ሲሆን፣ ያለፈው ዘመን ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ ዛሬ ለCambridge ሕዝብ ሕያው እና ንቁ ስፍራም ጭምር ሆኖ ይታያል።

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here