በBaby University በኩል ከአዲስ ወላጆች ጋር ይገናኙ
2025 ጁን 18, ረቡዕ
Baby University በዕድሜያቸው ሶስት ዓመት እና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ያሏቸው የCambridge ቤተሰቦችን የሚያገለግል አዲስ እና በነፃ የሚቀርብ የቤተሰብ ድጋፍ ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ ለ14 ሳምንታት የወላጅ ትምህርት፣ የጨዋታ ቡድኖች፣ አንድ ለአንድ ጉብኝቶች እና ጠቃሚ የማኅበረሰብ አጋዥ ግብዓቶችን በየሳምንቱ ቅዳሜ ጠዋት ላይ ያቀርባል።
Baby U ወላጆች የሚገናኙበት እና እንደ የአዕምሮ እድገት፣ የቤተሰብ የማንበብ እና መጻፍ ባህል እና አዎንታዊ የቅጣት ዘዴዎች ያሉ አስፈላጊ የልጅ አስተዳደግ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ተጨማሪ ማወቅ የሚችሉበት ዕድል በማቅረብ በተመሳሳይ ሰዓት የወላጅ/ልጅ ግንኙነቶቻቸውን እንዲያጠናክሩ ይረዳል። አባቶች እና እናቶች በአነስተኛ ቡድኖች ውስጥ ሃሳባቸውን እያጋሩ እና እርስ በእርስ እየተማማሩ በአንድ ላይ እና በተናጥል ተሳትፎ ያደርጋሉ።
ፕሮግራሙን ያጠናቀቁ ወላጆች የBaby U Alumni Associationን (የBaby U የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር) ይቀላቀላሉ። ይህም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለሚያቀርቡት እና ፕሮግራሙ ከቤተሰቦች ጋር ያለው ግንኙነት እንዲቀጥል ለሚያስችሉት Center for Families (የቤተሰቦች ማዕከል) የሚያቀርባቸው የቤተሰብ መዝናኛ ዝግጅቶች፣ ወርክሾፖች እና የወላጅ ውይይት ቡድኖች ተደራሽነት ይሰጣቸዋል።
Baby University በDepartment of Human Service Programs’ Community Engagement እና Family Support Division በኩል የሚቀርብ ነው
ለበለጠ መረጃ በBabyU@cambridgema.gov ያነጋግሩን ወይም ወደ 617-349-6204 ይደውሉ።
"
Baby U ለወላጆች መማር፣ መገናኘት እና አብረው ማደግ የሚችሉበትን ቦታ ይሰጣል።
"