U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መተግበር

2026 ሴፕቴምበር 3, ሐሙስ
" በCity Council የተቀመጡት እነዚህ አምስት ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፣ የሕዝብ ኢንቨስትመንቶች የCambridge ማኅበረሰብን ፍላጎቶች፣ እሴቶች እና የረጅም ጊዜ ግቦች እንዲያንፀባርቁ ለማረጋገጥ ያግዛሉ። "
ማንኛውም በጀት የሚጀምረው በአንድ ቀላል ጥያቄ ነው፦ ማኅበረሰባችን ከሁሉ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ምንድን ነው? 

Cambridge ውስጥ የዚህ ጥያቄ መልስ ከተለያዩ ምንጮች ይገኛል። ነዋሪዎች በሕዝብ ስብሰባዎች፣ በዳሰሳ ጥናቶች እና Participatory Budgeting (ነዋሪዎች በበጀት ውሳኔ ላይ የሚሳተፉበት የበጀት ሂደት) በመሳሰሉ መርሃ ግብሮች አማካኝነት ሐሳቦቻቸውን ያካፍላሉ። የከተማው መሥሪያ ቤቶች ወቅታዊ ፍላጎቶችንና ዕድሎችን ይለያሉ። በሌላ በኩል፣ City Council የከተማዋን ሥራ የሚመሩና የሥራ ማስኬጃና የካፒታል በጀቶች አቅጣጫን የሚወስኑ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አጀንዳዎችን ይነድፋል። 

ፌብርዋሪ 2026 ላይ City Council ለFY27 በጀት ዝግጅት እንደ መመሪያ የሚያገለግሉ የተሻሻሉ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች አፅድቋል። በአምስት ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ዙሪያ የተቀረጹት እነዚህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አጀንዳዎች፣ የሕዝብ ኢንቨስትመንቶች የCambridge ማኅበረሰብን ፍላጎቶች፣ እሴቶች እና የረጅም ጊዜ ግቦች እንዲያንፀባርቁ ለማረጋገጥ ያግዛሉ። 

እነዚህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አጀንዳዎች በዘንድሮው በጀት ውስጥ በተግባር የሚተረጎሙት በሚከተለው መልኩ ነው። 


መኖሪያ ቤት እና የቦታ አጠቃቀም/ዞኒንግ 

የመኖሪያ ቤት እድሎችን ማስፋት 

የቤት አቅርቦት አሁንም የCambridge ዋነኛ ፈተና ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፣ የFY27 በጀት ነዋሪዎች መኖሪያቸው በሆነችው ከተማ ውስጥ ተረጋግተው እንዲኖሩ ከማስቻሉም በላይ፣ የመኖሪያ ቤት ዕድሎችን ለማስፋፋት ከተማዋ ያላትን የቆየ ቁርጠኝነት አጠናክሮ ይቀጥላል። 

ይህ በጀት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የሚጠበቁ ቤቶችን፣ የቤት አልባነት መከላከያ ስራዎችን እና ነዋሪዎች ቋሚ መኖሪያ አግኝተው እንዲቆዩ የሚያግዙ ፕሮግራሞችን ይደግፋል። እንዲሁም በጀቱ አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ አረጋውያንን እና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመኖሪያ ቤት ልማት ኢንቨስትመንቶችን አጠናክሮ ይቀጥላል። 

ከዚህም በተጨማሪም ይህ ዓመት አስፈላጊ ተቋማዊ ለውጥ የተደረገበት ዓመት ነው። ቀደም ሲል በሦስት የተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ሥር ይመሩ የነበሩት የመኖሪያ ቤት እና የቤት አልባነት ፕሮግራሞች፣ አሁን በአንድ በተዋሐደ Housing Department (የቤቶች መምሪያ) ሥር እንዲጠቃለሉ ተደርጓል። እነዚህን አገልግሎቶች በማጠቃለል፣ ከተማዋ የሥራ ቅንጅትን ለማሻሻል፣ ነዋሪዎች አገልግሎቶቹን በቀላሉ እንዲያገኙ ለማድረግ እና ለመኖሪያ ቤት ፍላጎቶች ምላሽ የመስጠት አቅሟን ለማጠናከር ትሠራለች። 

ከተማዋ የዞኒንግ/የቦታ አጠቃቀም ማሻሻያዎችን፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ሕጎች ማሻሻልን፣ እንዲሁም በተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ የሚጣሉ መስፈርቶችንና የፈቃድ አሰጣጥ ሂደቶችን ለማሻሻል ሥራዋን ቀጥላለች። እነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች የከተማዋን የመኖሪያ ቤት ልማት እንቅስቃሴ ለማሳደግ እና ሰዎች በCambridge ከተማ ውስጥ እንዲኖሩ ተጨማሪ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለሙ ናቸው። 


የኢኮኖሚ ዕድልና ፍትሃዊነት 

የአካባቢ ንግዶችን መደገፍና ሁሉን ያሳተፈ ኢኮኖሚን ማጠናከር 

አነስተኛ ንግዶች Cambridgeን ልዩና ማራኪ ከሚያደርጓት ዋና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ናቸው። እነዚህ ተቋማት የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር አቅራቢያቸውን በማነቃቃት፣ ለከተማዋ የኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። 

የFY27 በጀት የሱቅ ፊት ገጽታ ማሻሻያ ድጋፎችን፣ የቴክኒክ እገዛዎችን፣ የኦንላይን ንግድ ድጋፎችን፣ የግብይት ማስተዋወቂያ እርዳታዎችን፣ እንዲሁም እንደ Cambridge Plays እና NITES ያሉ የማኅበረሰብ እንቅስቃሴ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ሥራ ፈጣሪዎች ንግዳቸውን እንዲጀምሩ፣ እንዲያሳድጉና እንዲያሻሽሉ ይደግፋል። 

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በሴቶች የሚመሩና ከዚህ ቀደም ድጋፎች ያልደረሷቸውን የንግድ ተቋማት ለማጠናከር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እያሰፋ ይገኛል። የግዥ ሥልጠናዎች፣ የአቅራቢዎችን ተሳትፎ ለማስፋት የሚደረጉ መርሃ ግብሮች እና ዓላማ ተኮር የማስተዋወቂያ ሥራዎች፣ የንግድ ተቋማት ለከተማ አስተዳደሩ ውሎች እንዲወዳደሩና በረጅም ጊዜ እንዲያድጉ ተጨማሪ ዕድሎችን እየፈጠሩ ነው። 

በተመሳሳይ ጊዜ Cambridge እየተለወጠና እያደገ ለሚሄደው ኢኮኖሚ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች። የንግድ ልማት መቀዛቀዝ፣ በህይወት ሳይንስ ዘርፍ የሚታዩ ለውጦች፣ የፌደራል ፖሊሲዎች አለመረጋጋት እንዲሁም የሥራ ገበያው መዋዠቅ በአንድነት አዳዲስ ፈተናዎችን ይዘው መጥተዋል። የከተማ አስተዳደሩ ከአሠሪዎችና ከንግዱ ዘርፍ መሪዎች ጋር በቅርበት በመሥራት የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ጥንካሬን ለማረጋገጥ እና Cambridge በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ግንባር ቀደም የፈጠራ ማዕከላት ተመራጭነቷን ለማስጠበቅ እየሠራ ይገኛል። 


የትራንስፖርት አገልግሎት 

ደህንነቱ የተጠበቀና የተቀናጀ ከተማ መገንባት 

ነዋሪዎች የእግር መንገድ፣ የብስክሌት፣ የሕዝብ ትራንስፖርት ወይም የግል መኪና ቢጠቀሙም፣ የትራንስፖርት ዘርፍ በዕለት ተዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ ላይ የጎላ ተጽዕኖ አለው። 

የFY27 በጀት ደህንነትን ለማሻሻል፣ የመጓጓዣ አማራጮችን ለማስፋት እና በከተማዋ ውስጥ ያለውን ትስስር ለማጠናከር በሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ላይ ትኩረቱን ይቀጥላል። 

ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል በLinear Park እና በGrand Junction Multiuse Path ላይ የሚደረጉ ቀጣይ ማሻሻያዎች እንዲሁም የRindge Avenue አካባቢን ከDanehy Park እና ከአቅራቢያው የንግድ ማዕከላት ጋር የሚያገናኝ የእግረኞችና የብስክሌት ድልድይ ዲዛይን ሥራ ይገኙበታል። 

የከተማ አስተዳደሩ በተጨማሪም በBetter Bus Network ዳግም ዲዛይን በኩል የአውቶቡስ አገልግሎትን ለማሻሻል ከMBTA ጋር በቅርበት እየሠራ ሲሆን፣ የሻትል አገልግሎትን ለማሻሻልና የአውቶቡስ መዘግየቶችን ለመቀነስ የሚቻልባቸውን መንገዶችም እያጠና ይገኛል። የአውቶቡስ ማቆሚያዎችን ለማሻሻል የታቀዱት ሥራዎች ተደራሽነትን እና የተሳፋሪዎችን ምቾት የሚጨምሩ ሲሆን፣ በRed Line (ሬድ ላይን) መስመር ላይ የሚደረጉ የMBTA ኢንቨስትመንቶችም የአገልግሎቱን አስተማማኝነት የበለጠ ያሳድጋሉ። 


ዘላቂነትና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም 

ለተለዋዋጩ የአየር ንብረት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ 

የFY27 በጀት የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ የሚደረጉ ሥራዎች እንዲቀጥሉ የሚያደርግ ሲሆን፣ Cambridge በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች ዝግጁ እንዲሆንም ያግዛል። 

ይህ ዓመት የማዘጋጃ ቤት ሥራዎች 100 በመቶ በታዳሽ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩበት የመጀመሪያው ሙሉ ዓመት ሲሆን፣ ይህም ለNet Zero Action Plan ትልቅ ስኬት ነው። 

ከዚህ በተጨማሪ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች የህዝብ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀሮችን ማስፋፋት፣ የማዘጋጃ ቤቱን የአገልግሎት ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሰሩ ማድረግ እና  እና የኃይል መሠረተ ልማትን ማሻሻልን ያካትታሉ። 

በጀቱ በተጨማሪም የጎርፍ ስጋትን የሚቀንሱ፣ የውሃ ጥራትን የሚያሻሽሉ እና ከተማዋ ከባድ የአየር ንብረት ሁኔታዎችን በተሻለ ሁኔታ እንድትቋቋም አቅሟን የሚያጎለብቱ ከፍተኛ የፍሳሽና የዝናብ ውሃ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን አካትቷል። ከSomerville እና ከMassachusetts Water Resources Authority (የSomerville እና ከMassachusetts የውኃ ሀብት ባለሥልጣን) ጋር የሚደረገው ቀጣይነት ያለው ትብብር፣ ከማህበረሰቡ ተሳትፎ ጋር ተደማምሮ፣ የወደፊት የዝናብ እና Combined Sewer Overflow (የተቀናጀ የፍሳሽ ማስወገጃ ፍሰት) ማሻሻያዎችን ለመምራት ይረዳል። 


የመንግሥትና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ አፈጻጸም 

የበለጠ ግልጽና ተሳትፎን የሚያበረታታ ከተማ መገንባት 

ውጤታማ መንግሥት የሚገነባው ተገቢ በሆነ የፋይናንስ አስተዳደር ብቻ አይደለም። በተጨማሪም ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና እውነተኛ የህዝብ ተሳትፎን ይፈልጋል። 

በFY27 የበጀት ዝግጅት ወቅት የCity Council በኢኮኖሚ ሁኔታዎች፣ በሥራ ማስኬጃና ካፒታል በጀቶች፣ በፌዴራል ድጋፎች፣ በመሥሪያ ቤቶች ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮችና በረጅም ጊዜ የፋይናንስ እቅዶች ላይ ያተኮሩ ተከታታይ የሕዝብ ውይይቶችን አድርጓል። እነዚህ ውይይቶች ነዋሪዎች የመንግሥትን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደትና የሕዝብ በጀት አጠቃቀምን በግልጽ እንዲረዱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። 

በዚህ ዓመትም Budget Office የBudget Walk Through ውይይቶችን አስተዋውቋል። እነዚህ ውይይቶች ነዋሪዎች የበጀት ዝግጅት ሂደቱን እንዲረዱ፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች የከተማዋን ወጪ አመዳደብ እንዴት እንደሚወስኑ እንዲገነዘቡ እና ጥያቄዎቻቸውን በቀጥታ ለከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች እንዲያቀርቡ ዕድል ሰጥተዋል። 

እነዚህ ጥረቶች Cambridge በParticipatory Budgeting አማካኝነት ሕዝቡን በበጀት ዝግጅት ሂደት ውስጥ ለማሳተፍ ለረጅም ጊዜ ስትሠራ የቆየችውን ሥራ የበለጠ ያጠናክራሉ። ከ2014 ጀምሮ የከተማዋ ነዋሪዎች አዳዲስ ሀሳቦችን በማንሳት፣ የፕሮጀክት እቅዶችን በማዘጋጀት እና ድምጽ በመስጠት በመላው ከተማ ለተተገበሩ ከ80 በላይ የማህበረሰብ ፕሮጀክቶች ከ$11 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን በጀት እንዲመደብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። 

እነዚህ ተግባራት በአንድነት ነዋሪዎች ስለከተማዋ ውሳኔዎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር፣ በውሳኔዎቹ ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ዕድል ይፈጥራሉ።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here