U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

ላልተረጋጋ የኢኮኖሚ ሁኔታ የሚደረግ ዝግጅት

2026 ሴፕቴምበር 3, ሐሙስ
" የCambridge አስተዳደር ማድረግ የሚችለው በጥንቃቄ ማቀዱን፣ በጥሞና የፋይናንስ ውሳኔዎችን ማሳለፉን እና ስልታዊ በሆነ መንገድ ኢንቨስት ማድረጉን መቀጠል ሲሆን፣ ይህም ወደፊት ለሚፈጠሩ ሁኔታዎች በቂ ዝግጅት እንዲያደርግ ያስችለዋል። "
የCambridge ጠንካራ ኢኮኖሚ ከተማዋ ለረጅም ጊዜ እንድታድግና እንድትበለጽግ ረድቷታል። 

ይህም ላፉት አሥርተ ዓመታት በKendall Square እና በከተማዋ የንግድ ማዕከላት ለታየው የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት፣ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት እና የመኖሪያ ቤት ግብር ከሚጠበቀው በላይ እንዳይጨምር ለማድረግ አስተዋጽኦ አድርጓል። እነዚያ የኢኮኖሚ ስኬቶች Cambridge በትምህርት ቤቶች፣ በተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት፣ በሕዝብ ፓርኮች፣ በመጓጓዣ፣ በአየር ንብረት ጥበቃ ተግባራት እና ማኅበረሰቡን በሚያጠናክሩ ፕሮግራሞች ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንድታደርግ አስችሏታል። 

ዛሬ ግን የኢኮኖሚው ሁኔታ እየተቀየረ ነው። 

Cambridgeም እንደ በርካታ ማኅበረሰቦች የንግድ ልማት መቀዛቀዝ፣ የወለድ ተመኖች መጨመር፣ በፌዴራል ደረጃ ያለው አለመረጋጋት እና በሕይወት ሳይንስና በቢሮ ንብረት ገበያዎች ላይ የሚታዩ ለውጦች የሚያስከትሏቸውን ተጽዕኖዎች እያስተናገደች ትገኛለች። Kendall Square አሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠቀሱ ግንባር ቀደም የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ ማዕከላት አንዱ እንደሆነ ቢቀጥልም፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ለላቦራቶሪዎች እና ለቢሮ ቦታዎች ያለው ፍላጎት ቅናሽ አሳይቷል። 

እነዚህ የኢኮኖሚ ለውጦች Cambridge የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ መግባቷን አያሳዩም።ሆኖም ግን፣ የታሰበበትና ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ ማውጣት ከምንጊዜውም በላይ አስፈላጊ መሆኑን ያረጋግጣሉ። 

Kendall Square ላይ ትኩረት ማድረግ ለምን አስፈለገ 

Kendall Square የምርምርና የፈጠራ ማዕከል ብቻ አይደለም። ለCambridge ኢኮኖሚ እድገት ዋና አስተዋጽኦ የሚያደርግ ማዕከል ነው። 

ከንግድ ልማት የሚገኘው የንብረት ግብር ገቢ እንደ ትምህርት፣ የሕዝብ ደህንነት፣ ፓርኮች፣ የመጓጓዣ ማሻሻያዎች እና ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት ልማት ያሉ ወሳኝ የከተማ አገልግሎቶችን ለመደገፍ ይውላል። ከንግድ ዘርፉ የሚገኘው ከፍተኛ የግብር ገቢ፣ የመኖሪያ ቤት ግብር ተመጣጣኝ እንዲሆን ያደርጋል። 

የንግድ ዕድገት በሚቀዛቀዝበት ወቅት፣ የከተማ አስተዳደሩ የልማት ኢንቨስትመንቶችን ከዘላቂ የፋይናንስ እቅድ ጋር አጣጥሞ ማስኬድ ይኖርበታል። 

ከአሁኑ የበጀት ዓመት ባሻገር ማቀድ 

Cambridge ካላት ታላላቅ ጥንካሬዎች አንዱ ከአንድ የበጀት ዓመት በላይ የሚዘልቅ ዕቅድ ማዘጋጀቷ ነው። 

ዓመቱን በሙሉ የBudget Office ቢያንስ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚያገለግሉ የፋይናንስ ትንበያዎችን የመቅረጽ እና የማሻሻል ሥራዎችን ያከናውናል። እነዚህ ትንበያዎች የከተማ አስተዳደሩ በኢኮኖሚው ላይ የሚከሰቱ ለውጦችን እንዲገመግም፣ ወደፊት ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ችግሮች አስቀድሞ ዝግጅት እንዲያደርግ እና ችግሮቹ ከመባባሳቸው በፊት በቂ መረጃ ላይ ተመስርቶ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ያግዛሉ። 

አስቀድሞ ማቀድ ለከተማ አስተዳደሩ የተሻሉ አማራጮችን ይሰጣል። የኢኮኖሚ ለውጦች ከተከሰቱ በኋላ አጣዳፊ እርምጃዎችን ከመውሰድ ይልቅ፣ የCambridge አስተዳደር ነዋሪዎች የሚተማመኑባቸውን አገልግሎቶች ሳያቋርጥ ወጪዎችን ማስተካከል፣ ለኢንቨስትመንቶች ቅድሚያ መስጠት እና ለተለያዩ የኢኮኖሚ ሁኔታዎች አስቀድሞ መዘጋጀት ይችላል። 

የፋይናንስ ጥንካሬ የተለያዩ አማራጮችን ይፈጥራል

Cambridge ዛሬ የደረሰችበት የኢኮኖሚ መረጋጋት፣ ለብዙ አሥርተ ዓመታት በጥንቃቄ በተዘጋጀ የፋይናንስ ዕቅድ እና ኃላፊነት ባለው የፋይናንስ አስተዳደር የተገኘ ነው። 

ጠንካራ የፋይናንስ ፖሊሲዎች፣ በቂ የመጠባበቂያ በጀት፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የበጀት አስተዳደር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ አስተዳደሩ በተለዋዋጭ የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ላይ ተገቢውን ምላሽ እየሰጠ ለማኅበረሰቡ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ኢንቨስት ማድረጉን እንዲቀጥል አስችለውታል። 

ይህ ጥንቃቄ የተሞላበት አሠራር የCambrdige አስተዳደር እንደሁኔታው ራሱን እንዲያስተካክል፣ የታሰበባቸውን ኢንቨስትመንቶች እንዲያከናውን እና በአካባቢው ዝቅተኛ የሚባለውን የመኖሪያ ቤት ግብር አስጠብቃ እንድትቀጥል ያስችለዋል። 

የወደፊቱ ጉዞ 

የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ወደፊትም መለዋወጣቸው የሚቀጥል ሲሆን፣ ወደፊት ምን እንደሚከሰት በትክክል ማወቅ አይቻልም። 

የCambridge አስተዳደር ማድረግ የሚችለው በጥንቃቄ ማቀዱን፣ በጥሞና የፋይናንስ ውሳኔዎችን ማሳለፉን እና ስልታዊ በሆነ መንገድ ኢንቨስት ማድረጉን መቀጠል ሲሆን፣ ይህም ወደፊት ለሚፈጠሩ ሁኔታዎች በቂ ዝግጅት እንዲያደርግ ያስችለዋል። 

ይህ አሠራር በFY27 በጀት ውስጥ በግልጽ የተንጸባረቀ ሲሆን፣ ነዋሪዎች የሚጠብቁትን የፋይናንስ ጥንካሬ በመጠበቅ የዛሬን ፍላጎቶች ከወደፊት እድሎች ጋር በማጣጣም የተዘጋጀ ነው።
Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here