U.S. flag

An official website of the United States government

Official websites use .gov
A .gov website belongs to an official government organization in the United States.

Secure .gov websites use HTTPS
A lock ( ) or https:// means you’ve safely connected to the .gov website. Share sensitive information only on official, secure websites.

Banner collage of photos of Cambridge residents

Rise Up Cambridge

Rise Up Cambridge ከ American Rescue Plan Act በከተማው የተቀበለውን ገንዘብ ተጠቅመው ልጆች ያሏቸውን ቤተሰቦች ለመርዳት የ Cambridge ከተማ የ $22 ሚሊዮን ቃል የገባው ነው። ዕድሜያቸው 21 ዓመት እና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ላሏቸው የ Cambridge ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰብ አባላት፣ ከፌዴራል የድኅነት ደረጃ 250 ፐርሰንት ወይም ከዚያ በታች ለሚያገኙ በቀጥታ ጥሬ ገንዘብ ይሰጣቸዋል።  Rise Up Cambridge እነዚያ የቤተሰብ አባላት በየወሩ $500 ለ 18 ወራት ያህል እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። 

በአገሪቱ ውስጥ እንደዚህ ያለ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ብቸኛ ከተማ-አቀፍ የሆነው ፕሮግራም፣ Rise Up Cambridge በ Cambridge ውስጥ እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚያዊ ክፍፍል እና የዘር መድሎን ለመፍታት የከተማችንን የተለያየ ህዝብ በመጠበቅ እና ሁሉም ቤተሰቦች የሚያድጉበት ቦታ ለማድረግ ያለመ ነው። ቀጥታ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ውጤታማ የሆነ የጸረ-ድህነት ስልት ሲሆን ነዋሪዎች በተሻለ ሁኔታ የገንዘብ ፍላጎታቸውን እና ግብዎቻቸውን እንዴት ማሳካት እንዳለባቸው እንዲወስኑ ዕድል ይሰጣቸዋል። በ COVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለኢኮኖሚ መረጋጋት፣ ለትምህርት እና ዕድል ተደራሽነት እና ለተሻለ ጤና እየጣሩ ላሉ Cambridge ይህንን አካሄድ አንዳንድ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦች ላይ በጎ ተጽእኖ ለማድረግ እየተጠቀመበት ነው።

ይህ ፕሮግራም በ Office of Mayor Siddiqui፣ Cambridge Economic Opportunity Committee (CEOC)፣ እና በ Cambridge Community Foundation ጋር በአጋርነት ይመራል።

 

Our Rise Up Cambridge team is available in person to answer your questions and help you fill out an application. Please find us at any of the times and locations listed here. No appointment is needed.

Location Day of Week
Monday Tuesday Wednesday Thursday Friday Saturday
CEOC
11 Inman St.
9am ‑ 5pm 9am ‑ 5pm 9am ‑ 7pm 9am ‑ 5pm 9am ‑ 12pm
Mayor's Office
795 Massachusetts Ave.
City Hall, 2nd floor
9am ‑ 8pm 9am ‑ 5pm 9am ‑ 5pm 9am ‑ 5pm 9am ‑ 12pm
Fresh Pond Apartments
362 Rindge Ave.
Community Room
4pm ‑ 7pm
12pm ‑ 3pm

የሚከተሉትን የሚያሟሉ ከሆነ ብቁ ኖት፦

 1. የ Cambridge ነዋሪ ከሆኑ፣ እና
 2. የእርስዎ ገቢ ከቤተሰብዎ መጠን ጋር ከፌዴራል የድኅነት መስመር ከተቀመጠው ከ 250% በታች ከሆነ፣ እና
 3. በቤተሰብዎ ውስጥ 21 ዓመት እና ከዚያ በታች ዕድሜ ያለው ልጅ ካልዎት፣ እና
 4. እድሜዎ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ከሆነ ነው።

ማሳሰቢያ፦ ብቁ የሆነ ቤተሰብ የሚከተሉትን ያካትታል፦

 • ባለአንድ ወላጅ ቤተሰቦች
 • ባለሁለት ወላጅ ቤተሰቦች
 • የተለመደው የቤተሰብ አባል ያልሆነ ማለትም ልጆቹን የሚያሳድጉ እንደ አያቶች ወይም ዘመዶች

ማሳሰቢያ፦ በቤተሰብዎ ውስጥ እርስዎ ወይም ሌላ አዋቂ ሰው የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እየተከታተሉ ከሆነ፣ የሙሉ-ጊዜ የሙያ ድግሪ የሚፈልግ (የሚከተለውን የሚያካትት ነገር ግን በዚህ ብቻ የማይወሰን MD፣ MBA፣ ወይም JD) ወይም የ PhD ዕጩ ከሆኑ፣ ምንም እንኳን ሌሎች የብቃት መመሪያዎችን የሚያሟሉ ቢሆንም እንኳን ለ Rise Up Cambridge ብቁ አይደሉም።

ማሳሰቢያ፦ ዜግነት ግዴታ አይደለም።

250% የፌዴራል የደህንነት መስመር በቤተሰብ መጠን

የቤተሰብ መጠን ዓመታዊው ገቢ ወርሃዊ ገቢ ሳምንታዊ ገቢ
2 $49,300 $4,108 $948
3 $62,150 $5,179 $1,195
4 $75,000 $6,250 $1,442
5 $87,850 $7,321 $1,689
6 $100,700 $8,392 $1,937
7 $113,550 $9,463 $2,183
8 $126,400 $10,533 $2,431
ለእያንዳንዱ ጭማሪ +$12,850 +$1,071 +$247

Rise Up Cambridge የ Cambridge RISE ስኬት ላይ (ለስኬት እና ለማበረታት ተደጋጋሚ የገቢ ምንጭ)፣ በ Cambridge ውስጥ በነጠላ ተንከባካቢዎች የሚመራ 130 ቤተሰቦችን የሚያገለግል መሰረታዊ የገቢ ማሳያ በ2021 ተጀመረ። ማሳያው የገንዘብ ድጋፍ እንዴት በድህነት ውስጥ ላሉት ቤተሰቦች መልካም ተጽእኖ እንደሚያሳድር፣ እና ነዋሪዎች በተሻለ ሁኔታ እንዴት የገንዘብ ፍላጎቶቻቸውን እና ግብዎቻቸውን መምታት እንደሚችሉ ለመወሰን እንዴት ሊያበቃቸው እንደሚችል አሳይቷል።

የገንዘብ ድጋፍ፦ $22 ሚሊዮን የሚሆነው ከፌዴራል የ American Rescue Plan Act (ARPA) የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም የተገኘ ነው።

የ Rise Up Cambridge መልካም ተጽእኖ መለካት፦ የ Cambridge Community Foundation በፕሮግራሙ ወቅት ተሳታፊዎች የበጎ ፈቃድ ዳሰሳዎችን ማጠናቀቅ እና/ወይም ታሪኮቻቸውን እና ልምዶቻቸውን መመዝገብ የሚችሉበት የመማሪያ አጀንዳ ለማካሄድ ከከተማው ጋር በቅርበት ይሰራል። እንደ ፕሮግራሙ አካል፣ የጥሬ ገንዘብ ጥቅማ ጥቅሞች ያላቸውን ዋጋ በበጎ ፈቃድ የዳሰሳ ጥናት ውስጥ በመሳተፍ ጥልቅ መረዳት እንዲኖራቸው ለመርዳት እና/ወይም እንደ የትምህርት አጀንዳ አካል አድርጎ ታሪካቸውን እና ተሞክሮዎቻቸውን በመሰነድ ለተሳታፊዎች ዕድል ይሰጣቸዋል። በዳሰሳ ጥናቶቹ ውስጥ መሳተፍ ወይም በሌሎች የትምህርት አጀንዳ በሆኑ ተግባራት ውስጥ መሳተፍ በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ግዴታ አይደለም። ሆኖም ግን፣ በዳሰሳ ጥናቶቹ ወይም በጆርናሎቹ ውስጥ የተሳተፉት እነዚህ ላጠፉት ጊዜ ካሳ እንደሚከፈላቸው ይጠበቃል።

የሚዲያ ጥያቄዎች፦ የመገናኛ ዳይሬክተር የሆነውን Lee Gianetti የተባለ ግለሰብ በሚከተለው ላይ ማግኘት ይችላሉ፤ 795 Massachusetts Avenue, Cambridge, MA 02139, lgianetti@cambridgema.gov, 617-349-3317።

News

Questions About Eligibility

እኔ ለ Rise Up Cambridge ብቁ ነኝ?

የሚከተሉትን የሚያሟሉ ከሆነ ብቁ ኖት፦

 1. የ Cambridge ነዋሪ ከሆኑ፣ እና
 2. የእርስዎ ገቢ ከቤተሰብዎ መጠን ጋር ከፌዴራል የድኅነት መስመር ከተቀመጠው ከ 250% በታች ከሆነ፣ እና
 3. በቤተሰብዎ ውስጥ 21 ዓመት እና ከዚያ በታች ዕድሜ ያለው ልጅ ካልዎት፣ እና
 4. እድሜዎ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ከሆነ ነው።

ለማመልከት ዜጋ መሆን አይጠበቅብዎትም።

ማሳሰቢያ፦ እርስዎ ወይም በቤተሰቡ ውስጥ የሚኖር አዋቂ ሰው የሚከተለው ከሆነ፦

 • በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ ሙሉ-ጊዜ የሚከታተል ከሆነ፣ ወይም
 • የሙሉ-ጊዜ የሙያ ድግሪ የሚከታተል ተማሪ ከሆነ (የሚከተለው ያካትታል ነገር ግን በዚህ ብቻ የማይወሰን አይሆንም የ MD፣ MBA፣ ወይም JD)፣ ወይም
 • የ PhD እጩ ከሆነ፣ ከዚያም

ምንም እንኳን ሌሎች የብቃት መመሪያዎችን ቢያሟሉም እንኳን፣ ለ Rise Up Cambridge ብቁ አይሆኑም።

የቤተሰብ አባልን እንዴት ይገልጻሉ?

የቤተሰብ አባል እርስዎን፣ የእርስዎን የትዳር ጓደኛ ወይም አጋርን፣ እና ለአብዛኛው ወጪያቸው የእርስዎ ገቢ ላይ ጥገኛ የሆኑ ማንኛውንም ሌላ የቤተሰብ አባላትን (ለምሳሌ፦ ዕድሜያቸው ከ 21 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች፣ ተማሪዎች፣ ወይም ያረጁ፣ የታመሙ፣ ወይም የአካል ጉዳተኛ የሆነ የቤተሰብ አባልን) ያካትታል።  
(1) ተመሳሳይ ልጆች በሁለት የተለያዩ የማመልከቻ ጥያቄዎችን ማቅረብ አይችሉም። ሁለቱም የልጁ ወላጆች በ Cambridge ነዋሪዎች ከሆኑ፣ ልጁ በዚያ ዓመት ውስጥ ከፌዴራል የገቢ ግብር ተመላሽ በሆነ ገቢ ላይ ጥገኛ እንደሆነ ወላጆቹ ባመለከቱት የማመልከቻ ጥያቄ ላይ ብቻ ማመልከት ይችላሉ።
(2) የክፍል ተጋሪዎች ወይም ተከራዮች እንደ ቤተሰብ አካል ተደርገው ሊቆጠሩ አይችሉም።
(3) በገንዘብ ራሱን ከቻለ ከሌላ ቤተሰብ ጋር ቤት ወይም አፓርታማ እየተጋሩ ከሆነ፣ እርስዎ እንደ ተለያዩ ቤተሰቦች ተደርገው ይቆጠራሉ።

እኔ እያመለከተ ካለ ከሌላ/ቤተሰብ ጋር አፓርታማ እጋራለሁ። ማመልከት እችላለሁ? ነዋሪ መሆኔን ለማረጋገጥ ምን ዓይነት ሰነድ ማቅረብ ይኖርብኛል?

በገንዘብ ራሱን ከቻለ ከሌላ ቤተሰብ ጋር ቤት ወይም አፓርታማ እየተጋሩ ከሆነ፣ እርስዎ እንደ ተለያዩ ቤተሰቦች ተደርገው ይቆጠራሉ።

 • እያንዳንዱ ቤተሰብ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል።
 • እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አድራሻውን የሚያረጋግጠውን ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል።

እኔ ወይም በቤተሰብ አባል መካከል አንዱ ሰነድ የሌለው ስደተኛ ከሆነ፣ ማመልከት እችላለሁ?

አዎን፤ ይህ ፕሮግራም የዜግነታቸው ሁኔታ ወይም የስደተኛነት ሁኔታቸው ምንም ሆነ ምን ለሁሉም ነዋሪዎችን ክፍት ነው። ማመልከቻው የእርስዎን ሕጋዊ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ምን ዓይነት ጥያቄዎችን አይጠይቅም።
እንደ ዩናይትድ ስቴት የዜግነት እና የስደተኝነት አገልግሎቶች መሰረት፣ ከ COVID-19 ጋር የተያያዙ ጥቅማ ጥቅሞች፣ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍን ጨምሮ፣ ግለሰቡ የሕዝባዊ ቅጣት ይኑርበት ወይም አይኑርብት ለይቶ ለማወቅ ጥቅም ላይ አይውልም።
 

እንደ የገቢ ምንጭ ተደርጎ የሚቆጠረው ምንድ ነው? የሕዝባዊ ጥቅማ ጥቅሞቼ በቤተሰብ አባል ገቢየ ላይ ተደምሮ ይቆጠራል?

የቤተሰብዎ ገቢ እርስዎ ወይም ሌሎች ከ21 አመት በላይ የሆኑትን ሌሎች አዋቂዎች ከሚከተሉት የሚቀበሉትን ገንዘብ ያጠቃልላል፦
(1) ደሞዝ
(2) ሥራዎች 
(3) የጥሪት ገቢ 
(4) የጡረታ የሂሳብ ቁጥር/ጡረታ 
(5) የሥራ አጥ መድኅን
(6) የአካል ጉዳተኛ የመድኅን 
(7) የማኅበራዊ ደኅንነት
የእርስዎ የሕዝባዊ ጥቅማ ጥቅሞች ከቤተሰብዎ ገቢ ጋር በአንድ ላይ ተደምሮ አይቆጠርም። አንዳንድ የህዝብ ጥቅማ ጥቅሞች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ ተጨማሪ የአመጋገብ እርዳታ ፕሮግራም (SNAP)፣ ለሴቶች፣ ጨቅላ ህጻናት እና ህፃናት ልዩ ተጨማሪ የአመጋገብ ፕሮግራም (WIC)፣ እና ለችግረኛ ቤተሰቦች ጊዜያዊ እርዳታ (TANF)።
የሚከተሉትን ከሆኑ እባክዎን ገቢዎን ለማስላት እርዳታን ለማግኘት በአካል በሚደረግ ስብሰባ ላይ ይካፈሉ፦
(1) ቋሚ የሆነ ገቢ (ሳምንታዊ ወይም ወርኃዊ) ከሌልዎት፣ ወይም 
(2) የራስን ሥራ በመስራት የሚገኝ ገቢ ከአልዎት (ለምሳሌ፦ የ Uber ወይም የ Lyft ሹፌሮች)።

 

ቤተሰቦቼ ቤት አልባ ናቸው፣ እና ቋሚ አድራሻ የለኝም። ማመልከት እችላለሁ? ምን ዓይነት ሰነድ ያስፈልገኛል?

አዎን፣ ማመልከት ይችላሉ። ሰነድ ለማግኘት፣ እርስዎ የ Cambridge ቤተሰብ መሆንን የሚገልጽ) ዕውቅና ያለው ደብዳቤ ለማግኘት ከ CEOC ሠራተኛ ጋር መስራት ይኖርብዎታል።

እኔ ወይም ከቤተሰቤ ውስጥ አንድ ሰው ከታሰረ፣ በአመክሮ ላይ ከሆነ፣ ወይም በይቅርታ ላይ ከተገኘ፣ ማመልከት እችላለሁ?

አዎ። እርስዎ ወይም ከቤተሰብ ውስጥ አንድ ሰው ከታሰረ፣ በአመክሮ ላይ ከሆነ፣ ወይም በይቅርታ ላይ ከተገኘ፣ ማመልከት ይችላሉ።

Questions About Application Process and Timeline

የቤተሰብ አባላት ለተሳትፎ የሚመረጡት እንዴት ነው?

ማመልከቻችዎች ተቀባይነት የሚያገኙት እንደአገባባቸው መሰረት ይሆናል። የብቃት መመዘኛ የሚያሟሉ እና ማመምልከቻ የሞሉ ሁሉም የቤተሰብ አባላት በዚህ ፕሮግራም ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ። 

እንዴት እና መቼ ማመልከት እችላለሁ?

ማመልከቻዎች ከጁን 1፣ 2023 ጀምሮ በኢንተርኔት ቀጥታ መሰመር ላይ ይገኛሉ። በጁን 1፣ 2023 እና ጁላይ 31፣ 2023 መካከል ባሉት ጊዜያት በማንኛውም ጊዜ ማመልከት ይችላሉ። በአንድ ቤተሰብ አንድ መመልከቻ ብቻ ይፈቀዳል። ማመልከቻዎች እንደየ አገባባቸው መሰረት ተቀባይነት የሚያገኙ ይሆናል (በተቀበልናቸው መሰረት)። 
የማኅበረሰብ ተደራሽ ጣቢያ ሠራተኞች ማመልከቻውን በመሙላት ይረዱዋችኋል።
 

የትኛው ወላጅ/የቤተሰብ አባል ማመልከቻውን ምውሙላቱ ልዩነት ያመጣል?

ማንኛውም ብቁ የሆነ ወላጅ ወይም የቤተሰቡ አባል የሆነ አዋቂ ሰው ማመልከት ይችላል።
የትኛው ወላጅ/የቤተሰብ አባል ማመልከቱ ምንም ዓይነት ለውጥ አያመጣም። ክፍያዎች ላመለከተው ወላጅ/ለቤተሰብ አባል ይላካሉ።
እያንዳንዱ ቤተሰብ ወደ ፕሮግራም ውስጥ መግባት የሚችለው አንዴ ብቻ ነው። ልጆች አንድ ግዜ ብቻ ይቆጠራሉ።
 

እኔ ትዳሬን የፈታሁ ወይም የልጆቼን ድርሻ በአደራነት የማስተዳደር ቢሆንስ?

አንዱ ወላጅ ወይም አሳዳጊ በ Cambridge የሚኖሩ ከሆነ፣ እና ሌላው ደግሞ የማይኖር ከሆነ፣ ጥቅማ ጥቅሙ በ Cambridge ወደ ሚኖረው ወላጅ ወይም አሳዳጊ ይላካል። ሁለቱም የልጅ ወላጆች የ Cambridge ነዋሪዎች ከሆኑ፣ ልጁ ቢያንስ ለግማሽ ዓመት ያህል አብሮት የኖረው የልጅ ወላጅ ብቻ የዚያን ልጅ ጥቅም መጠየቅ ይችላል።

ለማመልከት እና ክፍያዎችን ለመቀበል የጊዜ ሰሌዳው ምንድ ነው?

ማመልከቻው የሚጀምረው — ጁን 1፣ 2023 እስከ ጁላይ 31፣ 2023።
ምርጫ — ተሳታፊዎች ተቀባይነት የሚያገኙት እንደየአገባባቸው መሰረት ነው። የብቃት መመዘኛውን የሚያሟሉ ሁሉም አመልካቾች ይመረጣሉ።
ጠቃሚ የምክር አገልግሎት — በማመልከቻዎ ሂደት ጊዜ፣ ጠቃሚ የምክር አገልግሎት የሚፈልጉ ከሆነ እንለያለን። የ CEOC ሠራተኛ ማንኛውንም ሊያጡ የሚችሉ ጥቅማ ጥቅሞችን በማስረዳት ሊረዱዎት ይችላሉ።
የማመልከቻዬን ሂደት ደረጃን ማየት — ማመልከቻዎን በሚያስረክቡበት ጊዜ የኢንተርኔት ማስፈንጠሪያ በኢሜይል ወይም በአጭሩ የጹሑፍ መልእክት ይላክልዎታል። በዚያ የኢንተርኔት ማስፈንጠሪያ በኩል የእርስዎን ማመልከቻ ደረጃ ማየት ይችላሉ።
ማረጋገጫ— እንዴ የእርስዎ ማመልከቻ ተቀባይነት ካገኘ፣ የማረጋገጫ ማስታወቂያ በአጭር የጹሑፍ መልእክት ወይም በኢሜይል ይቀበላሉ።
የጥቅማ ጥቅም ክፍያ፦ ተቀባይነት ያገኙ አመልካቾች ለ18 ወራት ያህል በየወሩ የ $500 ክፍያ ያገኛሉ።
ቀጣይነት ያለው ድጋፍ — ድጋፍ ከፈለጉ ወይም ክፍያዎች እየተቀበሉ ካልሆነ፣ እባክዎን የግንኙነት ቡድናችንን በ +13127577267 ወይም support@riseupcambridge.aidkit.org ያግኙ።

 

ለሌላ ሰው ማመልከቻ መሙላት እችላለሁ?

አዎን፣ አመልካቹ ፍቃድ ከሰጥዎት ይችላሉ።

አንድ ሰው እንዲያመለክት ረድቸው ነበር፤ እንዴት የደረሰበትን ሁኔታ ማየት እችላለሁ?

አንዴ አመልካች ማመልከቻውን ካስረከበ፣ የማረጋገጫ ጽሁፍ ወይም ኢሜል ወደ ስልኩ ወይም ኢሜል አድራሻቸው በማመልከቻው ውስጥ የተካተተውን የማመልከቻ ሁኔታቸውን ለመከታተል ማስፈንጠሪያ ይደርሳቸዋል። 

What documents do I need to provide?

In the application, you need to prove:

 1. your identity; (2)
 2. that you live in Cambridge;
 3. that your household income is at or below 250% of the federal poverty level;
 4. that you have at least one child at or under 21 years old living in your household.

To prove your identity, you will need to provide a selfie and a photo ID. A selfie is a clear photo of your face. A photo ID can be any of the following:

 • Driver’s license
 • State ID
 • US Passport
 • Non-United States Passport
 • Military ID
 • Green Card
 • Certification of naturalization (form N-550 or N-570)
 • Certificate of citizenship (form N-560 or N-561)
 • Permanent resident card (1-551)
 • Native American tribal photo ID
 • Consular ID Card
 • (Foreign) Voter ID Card
 • US Employment Authorization
 • Learner’s Permit
 • Temporary Visitor Driver’s License
 • Other government issued photo ID

To prove that you live in Cambridge, you can provide any of the following documents:

 • Current (valid/non-expired) government issued photo ID with home address
 • Utility bill, landline phone bill, internet bill, or cable bill in the applicant’s name within the last 90 days with service address.
 • Mortgage or lease documents with home address, indicating current residency.
 • House deed with full address and individual’s name.
 • Certified school record for the current year verifying children’s enrollment and home address.

If you do not have access to any of those documents, you can provide one of the following:

 • Tax return or receipt with home address from tax year 2022 (Form 1040, Schedule C, or other filed tax form)
 • Government benefits document/confirmation letter dated after September 2022 (e.g. benefits confirmation letter for the Supplemental Nutrition Assistance Program (“SNAP”))
 • Property tax bill with home address, indicating current residency
 • Letter from an official third-party business/commercial enterprise with home address, delivered by the U.S. Post Office within the last 90 days.

 
To prove your household is at or below 250% of the federal poverty line, you can provide any of the following documents:

 • Enrollment or eligibility confirmation letter from any of the following programs:
  • Supplemental Nutrition Assistance Program (“SNAP”) – dated September 2022 or later.
  • Temporary Assistance for Needy Families (“TANF”) – dated September 2022 or later.
  • Special Supplemental Nutrition Program for Women, Infants, and Children (“WIC”) – dated September 2022 or later.
 • A paystub along with an attestation/certification that the submitted paystub is reflective of the applicant’s typical income.

If you do not have access to any of those documents, you can provide one of the following:

 • Wage documents from 2022 for all adults over 21 years old in the household that earn income:
  • W2 or 1099s
  • Unemployment award letter (last 12 months)
 • Tax return or receipt with home address from tax year 2022 (Form 1040, Schedule C, or other filed tax form). 

To prove you have at least one child at or under 21 years old living in your household, you can provide any of the following documents:

 • Certified school record for the current year that include the child’s name, DOB, name of parent/guardian, home address.
 • Medical or health records that includes the child’s name, DOB, name of parent/guardian, home address.
 • Tax transcript from Internal Revenue Service (IRS) listing the names of the dependents in the household.
 • Birth certificate for one child in your household (if available) AND an attestation from CEOC staff that the child lives with that parent/guardian at least half of the year.
 • Court documentation that includes the child’s name, DOB, name of parent/guardian, and home address, including but not limited to probate and family court documents

Questions About Payments

ማመልከቻዬ ተቀባይነት ካገኘ፣ ምን ያህል ገንዘብ አገኛለሁ ደግሞስ ለምን ያህል ጊዜ የሚሆን?

ከተመረጡ፣ ለ18 ወራት ያህል በየወሩ $500 ያገኛሉ። ይህ በድምሩ እስከ $9,000 ነው።

ይህን ገንዘብ በግብሬ ላይ እንደገቢ አድርጌ ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅብኛል?

አይ፣ ይህን ገንዘብ ግብር እንደሚከፈልበት አድርገው ሪፖርት ማድረግ አይጠበቅብዎትም። ይህ ገንዘብ እንደ "ብቁ የሆነ የአደጋ ጊዜ እፎይታ" ተደርጎ ይቆጠራል።  የ IRS መመሪያን እዚህ ይመልከቱ። 

ይህ ገንዘብ ለምን መጠቀም እችላለሁ? ይህን ገንዘብ መጠቀም የማልችለው ለምን ለምን ነው?

Rise Up Cambridge በ COVID-19 ወረርሽኝ ለተጎሳቆሉ እና ላገገሙ ቤተሰቦች ይረዳል። ገንዘቡን ለየትኛው የቤተሰብ ወጪ ለምሳሌ እንደ ለምግብ፣ ለቤት ኪራይ፣ ለልብስ፣ ወይም ለፍጆታ አግልግሎት መጠቀም ይችላሉ።
ገንዘቡን ለሚከተሉት ተግባራት መጠቀም አይችሉም፦
የፕሮጀክት ተቀባዮችን እና/ወይም ሌሎች የማህበረሰብ አባላትን ደህንነት የሚጎዳ ማንኛውንም ነገር ለመግዛት ወይም ለመደገፍ።
ለማጭበርበር ወይም ለጉቦ
ማንኛውንም ወንጀል ነክ የሆኑ ተግባራትን ለማስፈጸም
 

ይህን ገንዘብ እንዴት ወጪ ማድረግ እንዳለብኝ ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅብኛል?

አይ፣ ይህን ገንዘብ እንዴት ወጪ ማድረግ እንዳለብዎት ሪፖርት ማድረግ አይጠበቅብዎትም።

 

ክፍያዎችን የማገኘው መቼ ነው?

ክፍያዎች በየወሩ በመጀመሪያው ቀን ላይ ይከፈላሉ። የወሩ የመጀመሪያው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ፣ ክፍያው ቀደም ብሎ አርብ ለት ይከፈላል። በቀጥታ በባንክ እንዲገባልዎት የሚፈልጉ ከሆነ፣ የእርስዎ ባንክ ገንዘቡን ወደ ሂሳብዎ ገቢ ለማድረግ ከ 1-2 የሥራ ቀናትን ሊወስድበት ይችላል። የክፍያዎ የመጀመሪያው ቀን መቼ እንደሚሆነ ማመልከቻዎ ተቀባይነት በሚያገኝበት ጊዜ በማረጋገጫው ማስታወቂያ ላይ ይዘረዘራል።

Questions About Post Enrollment

ከተዘዋወርኩ ወይም የመኖሪያ ቦታዬ ከተለወጠ ምን ይከሰታል?

በ Cambridge ከተማ ውስጥ ቦታ ከቀየሩ፣ ለ CEOC በ support@riseupcambridge.aidkit.org ወይም 617-812-5124 ላይ ሪፖርት ማድረግ አለብዎት። ይህ የእርስዎ ብቁነት ላይ ምንም አይነት ለውጥ አያመጣም። የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ በማግኘት ላይ ይቀጥላሉ።  
ከ Cambridge ከተማ ውጪ ቦታ ከቀየሩ፣ ለ CEOC በ support@riseupcambridge.aidkit.org ወይም 617-812-5124 ላይ ሪፖርት ማድረግ አለብዎ። ከአሁን በኋላ የገንዘብ እርዳታ ለመቀበል ብቁ አይሆኑም። 
 

ገቢዬ ላይ ለውጦች ከመጡ ምን ይከሰታል?

ፕሮግራሙ ከተቀላቀሉ በኋላ ገቢዎ ከተለወጠ፣ ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅብዎትም። የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መቀበልን ይቀጥላሉ። ማመልከቻ ሲያስገቡ የገቢ ብቁነት ተረጋግጧል።

የቤተሰቤ ቅንብር ቢለወጥን ምን ይሆናል?

የቤተስብዎ ቅንብር በፕሮግራሙ ውስጥ ከተቀላቀሉ በኋላ ከተለወጠ፣ ሪፖርት ማድረግ አይጠበቅብዎትም። የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መቀበልን ይቀጥላሉ። የቤተሰብ ብቁነት በሚያመለክቱበት ጊዜ ተረጋግጧል። 

Contact Us

How can we help?

Please provide as much detail below as possible so City staff can respond to your inquiry:

As a governmental entity, the Massachusetts Public Records Law applies to records made or received by the City. Any information received through use of this site is subject to the same provisions as information provided on paper.

Read our complete privacy statement


Service Requests

Enter a service request via SeeClickFix for things like missed trash pickups, potholes, etc., click here