በከተማ አስተዳደሩ Budget Office ምክትል የበጀት ዳይሬክተር የሆኑት Angela Alfred የከተማ አስተዳደሩ በጀት ከተማ አስተዳደሩ በአግባቡ እየሠራ እና ማኅበረሰቡን እያገለገለ እንዲቀጥል ማድረግ የሚቻልበት ዕቅድ መሆኑን የCambridge ነዋሪዎች እንዲገነዘቡ ይፈልጋሉ።
"በጀቱ ማኅበረሰቡን እና የማኅበረሰቡን የዕለተ ዕለት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያሳተፈ ነው" ሲሉ Alfred ተናግረዋል። "ግብሮችን በተቻለ መጠን ዝቅተኛ አድርገን እያስቀጠልን ለከተማችን ነዋሪዎች የምናቀርባቸውን አገልግሎቶች በሙሉ ማቅረብ በምንችልበት ከፍተኛው ጥራት የምንሰጥበትን መንገድ የሚያሳይ ዕቅድ ነው።"
ለ24 ዓመታት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የቆዩት Alfred በBudget Office ሥራቸውን ሲጀምሩ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ኢንተርን ነበሩ። የኮሌጅ ትምህርታቸውን ተመርቀው ከጨረሱ በኋላ በAuditing Department (የኦዲት መምሪያ) መሥራት የጀመሩ ሲሆን፣ በዚህም ከበጀት ሂሳብ መዝገቡ ጋር እርስ በእርስ የሚደጋገፍ የከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ሌላኛው ገጽታ የሆነው አጠቃላይ የሂሳብ መዝገብ ላይ ልምድ እንዳገኙበት ይናገራሉ። ብዙም ሳይቆይ እስካሁን ድረስ እየሠሩ ወዳሉበት Budget Office ተመልሰዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ budget office ሲመለሱ፣ በዋነኝነት የጀማሪ ደረጃ የሥራ ሚናዎች ውስጥ ከአነስተኛ መምሪያዎች ጋር ይሠሩ ነበር። ይህ ተሞክሮ የከተማ አስተዳደሩን በጀት በተመለተ እስካሁን ድረስ በሥራቸው ላይ ጠቃሚ የሆነ መሠረታዊ ግንዛቤ እንደሰጣቸው ይናገራሉ።
"በዚህ የበጀት መዝገብ ውስጥ ምን ያህል በርካታ ክፍሎች እንዳሉ እና የበጀት መዝገቡ ከተዘጋጀ በኋላም በመላው ዓመት ውስጥ የከተማ አስተዳደሩን ፋይናንስ ለማስተዳደር ጥቅም ላይ ሊውል ወደሚችል ዕቅድ እንዴት ሊተረጎም እንደሚችል ስላሳየኝ ከታች ወደላይ መማር መቻሌ እጅግ በጣም አመስጋኝ የሆንኩበት ነገር ነው" ብለዋል።
Alfred ዛሬ በያዙት ምክትል የበጀት ዳይሬክተር ሚናቸው እንደ Fire Department (የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያ) እና Department of Public Works ያሉ ትላልቅ መምሪያዎችን ጨምሮ ከተለያዩ መምሪያዎች ጋር ይህን ሥራ ቀጥለዋል። የበጀት መዝገቡን በማሰናዳት እና የከተማ አስተዳደሩ እንከን የለሽ እና የተረጋጋ በሆነ መልኩ እየሠራ እንዲቀጥል በሚያደርግ መልኩ ዕቅዱ የሚቀናጅበትን መንገድ በመተንተን ረገድም ሰፋ ያለ ሚና ይጫወታሉ።
ከመምሪያዎች ጋር መሥራት እያንዳንዱ መምሪያ የCambridgeን ማኅበረሰብ የሚያገለግልባቸው በርካታ መንገዶች ዙሪያ ልዩ እይታ እንደሚሰጥ Alfred ገልጸዋል። የፖሊስ መኮንኖችን ሥራ ለዚህ አንድ ምሳሌ አድርገው ይጠቅሳሉ፤ ነዋሪዎች በመላው ሕይወታቸው ውስጥ ማኅበረሰቦቻቸው ዘንድ ሲንቀሳቀሱ ቢያዩም፣ የሚሠሯቸውን ሥራዎች ሁሉ እና የከተማ አስተዳደሩ ሥራ ማስኬጃ በጀት ይህን ሥራ የሚደግፍበትን መንገድ ላይገነዘቡ ይችላሉ።
“[ፖሊስ መኮንኖች] ከመዞር እና የደኅንነት ጥበቃ ከማቅረብ የበለጠ ጠቃሚ ሚና ይጫወታሉ። በማኅበረሰቡ እና ከትምህርት ቤቶቻችን እና ከFire Department ጋር በሚሠሩ የማኅበረሰብ አጋሮች ውስጥም በጥልቅ የተዋሃዱ ናቸው” ሲሉ Alfred ተናግረዋል። “አየህ በልጅነቴ፣ ሌሎች ነገሮችን ሲሠሩ እንደነበር ፈጽሞ አላወቅኩም ነበር…. እነዚህ በጀቱን ስታዋቅር የምታያቸው ነገሮች ናቸው።”
የከተማ አስተዳደሩን ሥራ ማስኬጃ በጀት ለማዘጋጀት ከመምሪያዎች እና ከበጀት ፋይናንስ ቡድኖች ጋር ከመሥራት ባሻገር Alfred እና የBudget Office የከተማዋን መሠረተ ልማት በሚደግፈው ካፒታል በጀት ላይም ይሠራሉ። የግብር ተመኖችን ለማስቀመጥም ከAssessing Office (ገምጋሚ ጽሕፈት ቤት) ጋር የሚሠሩ ሲሆን፣ የPB ጥረቶች ላይም የParticipatory Budgeting (PB) አስተባባሪውን ለመደገፍ ያግዛሉ።
ከዚህ በተጨማሪ የBudget Office የከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ለሚችሉ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ለመዘጋጀት ጥረት ያደርጋል። Alfred የበጀት ሂደቱ በተቻለ መጠን በርካታ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እያቀረበ በሚቻልበት ጊዜ ደግሞ ለወደፊቱ ገንዘብ ለመቆጠብ የሚያልም መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል። ይህ የመጠባበቂያ ዕቅድ አወጣጥ አቀራረብ የከተማ አስተዳደሩ የCOVID-19 ወረርሽኝን ተቋቁሞ እንዲያልፍ አስችሎታል። በተጨማሪም የbudget office በአሁኑ ወቅት በመጠኑ የተቀዛቀዘው ኢኮኖሚ እንዴት ሊያገግም ይችላል የሚለው ዙሪያ ያሉ ምልከታዎችን ጨምሮ ያለማቋረጥ ለወደፊቱ ትንበያዎችን እያደረገ ነው።
"ትንበያዎቹ በየዓመቱ የሚሻሻሉ መሆኑን ብናውቅም፣ ለወደፊቱ አምስት ዓመታት ትንበያዎች እናደርግ እና ለቀጣዩ ዓመት እና ከዚያ ወዲያ ለሚመጣው ዓመት ምን ማየት እንደምንፈልግ እንወያያለን" በማለት ተናግረዋል። "ስለዚህ ሊፈጠሩ የሚችሉ የከፉ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ እያስገባን እና ጥሩውን ተስፋ እያደረግን ነው። ብዙ ዕቅድ አወጣጥ አለ እና ይሄ የሚከናወነው በጀቱ ውስጥ ከመግባታችን በፊት ነው።"
ከዚህ ዕቅድ አወጣጥ ጋር የበጀት ሂደቱ በራሱ መላው ዓመቱን የሚፈጅ ጥረት ነው፤ የCambridge ነዋሪዎች ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን ይህን ነገር ላይረዱ ይችላሉ።
"በጀቱን ለማዋቀር የሚያስፈልገውን ሥራ ለመሥራት ወደ ስድስት ወራት አካባቢ የሚፈጅብን ቢሆንም፣ እሱን ሥራ ከጨረስን በኋላ ግን ያንን በጀት ወስደን በውስጡ ያስቀመጥነውን ዕቅድ በጥብቅ መከታተል አለብን" ሲሉ Alfred ተናግረዋል። "በዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙት ነዋሪዎች የበጀት መዝገቡን እኛ እንደምንረዳው ለከተማው እና እያንዳንዱ መምሪያ ለሚሠራው ሥራ የሚወጣ ዕቅድ አድርገው ይገነዘባሉ ብዬ አስባለሁ።"
በCambridge ማኅበረሰብ ውስጥ ይህ ሥራ የሚጫወተው ወሳኝ ሚና Cambridge ውስጥ ላደጉት Alfred ትልቅ ትርጉም አለው።
"ከሥራዬ በጣም የምወደው ነገር በዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ ያደግኩ እንደመሆኔ መጠን በሆነ መልኩ መልሼ ለማኅበረሰቤ አስተዋጽዖ እያበረከትኩ መሆኑን ማወቁ ነው" ሲሉ ይናገራሉ። “የትውልድ ከተማዬ በመሆኑ ከፍተኛ እርካታ የሚሰጠኝ ሙያ ነው…. የከተማ አስተዳደሩ የሚሠራው ሥራ እና እንደ ሌሎች ያልታደሉትን እየረዳ ያለበት መንገድ እንዲሁም የሰፈነው የማኅበረሰባዊነት ስሜት ይታየኛል። ሰዎች ለሰዎች ያስባሉ።"